1
1ኛ የዮሐንስ መልእክት 4:18
መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)
በፍቅር ፍርሃት የለም፥ ነገር ግን ፍጹም ፍቅር ፍርሃትን አውጥቶ ይጥላል፤ ፍርሃት ቅጣት አለው፥ የሚፈራ ሰው በፍቅር ፍጹም አልሆነም።
Compare
Explore 1ኛ የዮሐንስ መልእክት 4:18
2
1ኛ የዮሐንስ መልእክት 4:4
ልጆች ሆይ፥ እናንተ ከእግዚአብሔር ናችሁ፥ አሸንፋችኋቸዋልም፥ በእናንተ ያለው በዓለም ካለው ይበልጣልና።
Explore 1ኛ የዮሐንስ መልእክት 4:4
3
1ኛ የዮሐንስ መልእክት 4:19
እርሱ አስቀድሞ ስለወደደን፥ እንወዳለን።
Explore 1ኛ የዮሐንስ መልእክት 4:19
4
1ኛ የዮሐንስ መልእክት 4:7
ወዳጆች ሆይ፥ ፍቅር ከእግዚአብሔር ስለ ሆነ፥ እርስ በርሳችን እንዋደድ፤ የሚያፈቅር ሁሉ ከእግዚአብሔር የተወለደ ነው፥ እግዚአብሔርንም ያውቃል።
Explore 1ኛ የዮሐንስ መልእክት 4:7
5
1ኛ የዮሐንስ መልእክት 4:8
የማያፈቅር እግዚአብሔርን አያውቅም፥ እግዚአብሔር ፍቅር ነውና።
Explore 1ኛ የዮሐንስ መልእክት 4:8
6
1ኛ የዮሐንስ መልእክት 4:10
ፍቅር በዚህ ነው፥ እኛ እግዚአብሔርን እንደ ወደድነው ሳይሆን ነገር ግን እርሱ እንደ ወደደን እና ለኃጢአታችንም ማስተስሪያ እንዲሆን ልጁን ስለላከልን ነው።
Explore 1ኛ የዮሐንስ መልእክት 4:10
7
1ኛ የዮሐንስ መልእክት 4:11
ወዳጆች ሆይ፥ እግዚአብሔር እንዲህ ከወደደን፥ እኛ ደግሞ እርስ በርሳችን ልንዋደድ ይገባናል።
Explore 1ኛ የዮሐንስ መልእክት 4:11
8
1ኛ የዮሐንስ መልእክት 4:9
በዚህም የእግዚአብሔር ፍቅር በእኛ ተገለጠ፥ በእርሱ በኩል እንድንኖር እግዚአብሔር አንድያ ልጁን ወደ ዓለም ልኮታልና።
Explore 1ኛ የዮሐንስ መልእክት 4:9
9
1ኛ የዮሐንስ መልእክት 4:20
ማንም፦ “እግዚአብሔርን እወደዋለሁ” ቢል ወንድሙን ግን ቢጠላ ሐሰተኛ ነው፤ ያየውን ወንድሙን የማይወድ ያላየውን እግዚአብሔርን ሊወድ አይችልምና።
Explore 1ኛ የዮሐንስ መልእክት 4:20
10
1ኛ የዮሐንስ መልእክት 4:15
ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ የሚመሰክር ሁሉ፥ እግዚአብሔር በእርሱ ይኖራል እርሱም በእግዚአብሔር ይኖራል።
Explore 1ኛ የዮሐንስ መልእክት 4:15
11
1ኛ የዮሐንስ መልእክት 4:21
ከእርሱ የተሰጠን ትእዛዝ ይህ ነው፥ እግዚአብሔርን የሚወድ ወንድሙን ደግሞ ይውደድ።
Explore 1ኛ የዮሐንስ መልእክት 4:21
12
1ኛ የዮሐንስ መልእክት 4:1-2
ወዳጆች ሆይ፥ መንፈስን ሁሉ አትመኑ፥ ነገር ግን መንፈሶች ከእግዚአብሔር መሆናቸውን መርምሩ፤ ብዙ ሐሰተኞች ነቢያት ወደ ዓለም መጥተዋልና። የእግዚአብሔርን መንፈስ በዚህ ታውቃላችሁ፤ ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ እንደመጣ የሚያምን መንፈስ ሁሉ ከእግዚአብሔር ነው፥
Explore 1ኛ የዮሐንስ መልእክት 4:1-2
13
1ኛ የዮሐንስ መልእክት 4:3
ኢየሱስ ክርስቶስም በሥጋ እንደመጣ የማያምን መንፈስ ሁሉ ከእግዚአብሔር አይደለም፤ ይህም ይመጣል ሲባል የሰማችሁት የክርስቶስ ተቃዋሚ መንፈስ ነው፥ አሁንም እንኳ በዓለም ውስጥ አለ።
Explore 1ኛ የዮሐንስ መልእክት 4:3
Home
Bible
Plans
Videos