1
የሉቃስ ወንጌል 3:21-22
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
ሰዎች ሁሉ ከተጠመቁ በኋላ ኢየሱስም ተጠመቀ፤ እርሱ ሲጸልይ ሳለ ሰማይ ተከፈተ፤ መንፈስ ቅዱስም በርግብ አምሳል ሆኖ በእርሱ ላይ ወረደ፤ በዚያኑ ጊዜ “አንተ የተወደድክ ልጄ ነህ፤ በአንተ ደስ ይለኛል” የሚል ድምፅ ከሰማይ መጣ።
Compare
Explore የሉቃስ ወንጌል 3:21-22
2
የሉቃስ ወንጌል 3:16
ዮሐንስ ግን ለሁሉም እንዲህ አላቸው፦ “እኔ በውሃ አጠምቃችኋለሁ፤ ነገር ግን ሌላ ከእኔ የሚበረታ ይመጣል፤ እኔ የእርሱን ጫማ ማሰሪያ ለመፍታት እንኳ የበቃሁ አይደለሁም፤ እርሱ በመንፈስ ቅዱስና በእሳት ያጠምቃችኋል።
Explore የሉቃስ ወንጌል 3:16
3
የሉቃስ ወንጌል 3:8
ይልቁንስ ንስሓ መግባታችሁን የሚያመለክት ሥራ ሥሩ እንጂ እኛ የአብርሃም ልጆች ነን እያላችሁ በልባችሁ አትመኩ። እግዚአብሔር ከእነዚህ ድንጋዮች ለአብርሃም ልጆች ሊያስነሣለት እንደሚችል እነግራችኋለሁ።
Explore የሉቃስ ወንጌል 3:8
4
የሉቃስ ወንጌል 3:9
አሁን መጥረቢያ በዛፎቹ ሥር ተቀምጦአል። ስለዚህ መልካም ፍሬ የማያፈራ ዛፍ ሁሉ ይቈረጣል ወደ እሳትም ይጣላል።”
Explore የሉቃስ ወንጌል 3:9
5
የሉቃስ ወንጌል 3:4-6
ይህም የሆነው፦ ነቢዩ ኢሳይያስ ስለ ዮሐንስ አስቀድሞ እንዲህ ሲል በጻፈው መሠረት ነው፦ “እነሆ! ይህ በበረሓ እንዲህ እያለ የሚጮኽ ሰው ድምፅ ነው፤ ‘የጌታን መንገድ አዘጋጁ! ጥርጊያውንም አቅኑ! ጐድጓዳው ቦታ ሁሉ ይደልደል! ተራራና ኰረብታውም ሁሉ ዝቅ ይበል! ጠማማው መንገድ ይቅና! ሻካራውም መንገድ ይስተካከል! ሰውም ሁሉ የእግዚአብሔርን ማዳን ይይ!’ ”
Explore የሉቃስ ወንጌል 3:4-6
Home
Bible
Plans
Videos