1
ትንቢተ ኢሳይያስ 46:10-11
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
በመጨረሻ የሚሆነውን ነገር ከመጀመሪያው ጀምሬ ተናግሬአለሁ፤ ወደፊት ምን እንደሚሆን ከጥንት ጀምሬ ገልጬአለሁ፤ ዓላማዬ የጸና ይሆናል፤ የምፈቅደውንም አደርጋለሁ። ከወደ ምሥራቅ እንደ ነጣቂ ጭልፊት ያለውን እጠራለሁ፤ እርሱም ዓላማዬን የሚፈጽም፥ ከሩቅ አገር የሚመጣ ሰው ነው፤ የተናገርኩትን አደርጋለሁ፤ ያቀድኩትንም እፈጽማለሁ።
Compare
Explore ትንቢተ ኢሳይያስ 46:10-11
2
ትንቢተ ኢሳይያስ 46:4
አርጅታችሁ ጠጒራችሁ እስከሚሸብትበት ጊዜ ድረስ፥ የምጠብቃችሁ እኔ ነኝ፤ ፈጥሬአችኋለሁ፤ እንከባከባችኋለሁም፤ እረዳችኋለሁ፤ ከክፉ ነገርም እጠብቃችኋለሁ።
Explore ትንቢተ ኢሳይያስ 46:4
3
ትንቢተ ኢሳይያስ 46:9
እኔ ብቻ አምላክ መሆኔንና ከእኔም በቀር ሌላ አምላክ እንደሌለ ዕወቁ፤ በቀድሞ ዘመን የተደረጉትን የጥንቱን ነገሮች አስታውሱ፤ እኔ አምላክ ነኝ፤ እኔንም የሚመስል ሌላ የለም።
Explore ትንቢተ ኢሳይያስ 46:9
4
ትንቢተ ኢሳይያስ 46:3
“ከማሕፀን ጀምሬ የጠበቅኋችሁና ከልደት ጀምሬ የረዳኋችሁ የያዕቆብ ልጆች የሆናችሁ፥ የእስራኤል ቅሪቶች! አድምጡኝ።
Explore ትንቢተ ኢሳይያስ 46:3
Home
Bible
Plans
Videos