1
ወደ ኤፌሶን ሰዎች 2:10
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
እኛ እግዚአብሔር አስቀድሞ ያዘጋጃቸውን መልካም ሥራዎች እንድንሠራ በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት እንደገና የተፈጠርን የእግዚአብሔር ፍጡሮች ነን።
Compare
Explore ወደ ኤፌሶን ሰዎች 2:10
2
ወደ ኤፌሶን ሰዎች 2:8-9
እናንተ የዳናችሁት በእምነት አማካይነት በጸጋው ነው፤ ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ በእናንተ ሥራ የተገኘ አይደለም። ማንም ሰው እንዳይመካ፥ የመዳን ጸጋ የተገኘው በሥራ አይደለም፤
Explore ወደ ኤፌሶን ሰዎች 2:8-9
3
ወደ ኤፌሶን ሰዎች 2:4-5
ነገር ግን የእግዚአብሔር ምሕረቱ ብዙ ከመሆኑና ለእኛም ያለው ፍቅር ታላቅ ከመሆኑ የተነሣ በበደላችን የሞትን ብንሆንም እንኳ እግዚአብሔር ከክርስቶስ ጋር እንድንኖር አድርጎናል፤ እናንተም የዳናችሁት በጸጋው ነው።
Explore ወደ ኤፌሶን ሰዎች 2:4-5
4
ወደ ኤፌሶን ሰዎች 2:6
እግዚአብሔር በክርስቶስ ኢየሱስ አማካይነት ከእርሱው ጋር ከሞት አስነሥቶ በሰማያዊ ስፍራ ከእርሱ ጋር አስቀመጠን።
Explore ወደ ኤፌሶን ሰዎች 2:6
5
ወደ ኤፌሶን ሰዎች 2:19-20
ስለዚህ እናንተ ከቅዱሳን ጋር የአንድ አገር ዜጎችና የእግዚአብሔር ቤተሰቦች ናችሁ እንጂ ከእንግዲህ ወዲህ እንግዶችና መጻተኞች አይደላችሁም። በሐዋርያትና በነቢያትም መሠረት ላይ ታንጻችኋል፤ የማእዘኑም ራስ ድንጋይ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።
Explore ወደ ኤፌሶን ሰዎች 2:19-20
Home
Bible
Plans
Videos