1
ትንቢተ ዳንኤል 6:10
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
ዳንኤል ዐዋጁ ተፈርሞበት እንደ ጸና ቢያውቅም እንኳ ወደሚኖርበት ሰገነት ወጣ፤ የሚኖርበትም ሰገነት በኢየሩሳሌም ትይዩ የተከፈቱ መስኮቶች ነበሩት፤ ከዚህ በፊት ያደርገው እንደ ነበረም በጒልበቱ በመንበርከክ አምላኩን እያመሰገነ በቀን ሦስት ጊዜ ይጸልይ ነበር።
Compare
Explore ትንቢተ ዳንኤል 6:10
2
ትንቢተ ዳንኤል 6:22
አንበሶቹ እንዳይጐዱኝ እግዚአብሔር መልአኩን ልኮ አፋቸውን ዘጋ፤ ይህንንም ያደረገው እኔ በእርሱ ዘንድ ንጹሕ መሆኔንና አንተንም አለመበደሌን ስላወቀ ነው።”
Explore ትንቢተ ዳንኤል 6:22
3
ትንቢተ ዳንኤል 6:26-27
በመንግሥቴ የሚኖር ሕዝብ ሁሉ የዳንኤልን አምላክ እንዲፈራና እንዲያከብር በዐዋጅ አዝዤአለሁ፤ “እርሱ ሕያውና ዘለዓለማዊ አምላክ ነው፤ መንግሥቱም የማይጠፋ ነው፤ ለመንግሥቱም ፍጻሜ የለውም፤ እርሱ ያድናል ይታደግማል፤ እርሱ በሰማይና በምድር ድንቅ ነገሮችንና ተአምራትን ያደርጋል፤ እርሱ ዳንኤልን ከአንበሶች አፍ አድኖአል።”
Explore ትንቢተ ዳንኤል 6:26-27
4
ትንቢተ ዳንኤል 6:16
ስለዚህ ዳንኤል ተይዞ መጥቶ ወደ አንበሶች ጒድጓድ እንዲጣል ንጉሡ አዘዘ፤ ዳንኤልንም “ሁልጊዜ በታማኝነት የምታገለግለው አምላክህ ያድንህ” አለው።
Explore ትንቢተ ዳንኤል 6:16
Home
Bible
Plans
Videos