1
2 ተሰሎንቄ ሰዎች 2:3
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
ማንም ሰው በምንም ዐይነት አያታላችሁ፤ አስቀድሞ ክሕደት ሳይመጣ፥ ገሃነም የሚገባው የዐመፅ ሰው የሆነውም ሳይገለጥ፥ ያ ቀን አይመጣም።
Compare
Explore 2 ተሰሎንቄ ሰዎች 2:3
2
2 ተሰሎንቄ ሰዎች 2:13
በጌታ የተወደዳችሁ ወንድሞች ሆይ! እኛ ግን በእናንተ ምክንያት እግዚአብሔርን ሁልጊዜ ማመስገን ይገባናል፤ የምናመሰግነውም እናንተ በመንፈስ ቅዱስ በመቀደሳችሁና እውነትን በማመናችሁ እንድትድኑ እግዚአብሔር በመጀመሪያ ስለ መረጣችሁ ነው።
Explore 2 ተሰሎንቄ ሰዎች 2:13
3
2 ተሰሎንቄ ሰዎች 2:4
ይህ የዐመፅ ሰው አማልክት ተብለው ከሚመለኩት ሁሉ በላይ ራሱን ከፍ ያደርጋል፤ “እግዚአብሔር ነኝ” እያለም በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እንኳ ለመቀመጥ ይደፍራል።
Explore 2 ተሰሎንቄ ሰዎች 2:4
4
2 ተሰሎንቄ ሰዎች 2:16-17
ራሱ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስና የወደደን፥ በጸጋውም የዘለዓለም መጽናናትን፥ መልካም ተስፋንም የሰጠን እግዚአብሔር አባታችን መልካም የሆነውን ሁሉ እንድታደርጉና እንድትናገሩ ልባችሁን ያጽናናው፤ መልካሙን ነገር ሁሉ እንድታደርጉና እንድትናገሩ ያበርታችሁ።
Explore 2 ተሰሎንቄ ሰዎች 2:16-17
5
2 ተሰሎንቄ ሰዎች 2:11
በዚህ ምክንያት በሐሰት እንዲያምኑ እግዚአብሔር የሚያሳስት ኀይልን ይልክባቸዋል።
Explore 2 ተሰሎንቄ ሰዎች 2:11
6
2 ተሰሎንቄ ሰዎች 2:9-10
የዐመፅ ሰው የሚመጣው በሰይጣን ኀይል አሳሳች ተአምራትንና ምልክቶችን አስደናቂ ነገሮችንም በማድረግ ነው፤ እንዲሁም የሚጠፉትን ሰዎች የሚያታልሉት ማናቸውንም ክፉ ነገሮችን በማድረግ ነው። እነዚህ ሰዎች የሚጠፉትም ለመዳን የሚያበቃቸውን እውነት ወደው ስላልተቀበሉ ነው።
Explore 2 ተሰሎንቄ ሰዎች 2:9-10
7
2 ተሰሎንቄ ሰዎች 2:7
ምሥጢራዊው የዐመፅ ኀይል አሁንም በመሥራት ላይ ነው፤ ሆኖም አሁን የሚከለከለው አለ፤ ይህም የሚሆነው ያ የሚከለክለው እስኪወገድ ድረስ ነው።
Explore 2 ተሰሎንቄ ሰዎች 2:7
Home
Bible
Plans
Videos