1
ሁለተኛ መጽሐፈ ነገሥት 4:2
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
ኤልሳዕም “ታዲያ ምን እንዳደርግልሽ ትፈልጊያለሽ? በቤትሽም ምን እንዳለሽ ንገሪኝ” ሲል ጠየቃት። እርስዋም “በትንሽ ማሰሮ ከሚገኝ የወይራ ዘይት በቀር ሌላ ምንም የለኝም” ስትል መለሰች።
Compare
Explore ሁለተኛ መጽሐፈ ነገሥት 4:2
2
ሁለተኛ መጽሐፈ ነገሥት 4:1
የነቢያት ጉባኤ አባል የነበረ ባልዋ የሞተባት አንዲት ሴት ወደ ኤልሳዕ መጥታ “ጌታዬ ሆይ! ባሌ ሞቶብኛል! እርሱም አንተ እንደምታውቀው እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው ነበር፤ ነገር ግን እነሆ ለባሌ ገንዘብ አበድሮት የነበረ አንድ ሰው በባሌ ዕዳ ፈንታ ሁለት ወንዶች ልጆቼን ወስዶ ባሪያ አድርጎ ሊገዛቸው ፈልጎአል” አለችው።
Explore ሁለተኛ መጽሐፈ ነገሥት 4:1
3
ሁለተኛ መጽሐፈ ነገሥት 4:3
ኤልሳዕም እንዲህ አላት፦ “ወደ ጐረቤቶችሽ ሄደሽ ማግኘት የምትችዪውን ያኽል ባዶ ማድጋ ለምኚ፤
Explore ሁለተኛ መጽሐፈ ነገሥት 4:3
4
ሁለተኛ መጽሐፈ ነገሥት 4:4
ከዚህም በኋላ አንቺና ልጆችሽ ወደ ቤት ገብታችሁ መዝጊያውን ዝጉ፤ የማሰሮውንም ዘይት ወደ ማድጋዎቹ ማንቈርቈር ጀምሩ፤ እያንዳንዱ ማድጋ በሚሞላበት ጊዜ ለብቻው በማግለል አኑሩት።”
Explore ሁለተኛ መጽሐፈ ነገሥት 4:4
5
ሁለተኛ መጽሐፈ ነገሥት 4:6
ማድጋዎቹንም ሁሉ ከሞሉ በኋላ “ሌላ ትርፍ የለም ወይ?” ስትል ጠየቀች፤ ከልጆችዋም አንዱ “ሌላ ማድጋ የለም” ሲል መለሰላት። ከዚያም በኋላ ዘይቱ መውረዱን አቆመ፤
Explore ሁለተኛ መጽሐፈ ነገሥት 4:6
6
ሁለተኛ መጽሐፈ ነገሥት 4:7
እርስዋም ተመልሳ ወደ ነቢዩ ኤልሳዕ ሄደች፤ እርሱም “እንግዲህ ዘይቱን ሸጠሽ ዕዳሽን በሙሉ ክፈይ፤ ለአንቺና ለልጆችሽ መተዳደሪያ የሚሆንም ብዙ ገንዘብ ይተርፍሻል” አላት።
Explore ሁለተኛ መጽሐፈ ነገሥት 4:7
7
ሁለተኛ መጽሐፈ ነገሥት 4:5
ስለዚህም ሴትዮዋ ወደ ቤትዋ ሄዳ ከልጆችዋ ጋር በሩን ዘጋች፤ ዘይት የነበረበትን ትንሽ ማሰሮ አንሥታ ልጆችዋ እያቀረቡላት በማንቈርቈር በየማድጋዎቹ ሞላች።
Explore ሁለተኛ መጽሐፈ ነገሥት 4:5
8
ሁለተኛ መጽሐፈ ነገሥት 4:34
ከዚህም በኋላ አፉን ከአፉ፥ ዐይኖቹን ከዐይኖቹ፥ እጆቹን ከእጆቹ ጋር ገጥሞ በልጁ ሬሳ ላይ ተጋደመ፤ ኤልሳዕም ተዘርግቶ እንደ ተጋደመበት የልጁ ሰውነት መሞቅ ጀመረ።
Explore ሁለተኛ መጽሐፈ ነገሥት 4:34
Home
Bible
Plans
Videos