1
ራእይ 9:20-21
አዲሱ መደበኛ ትርጒም
በእነዚህ መቅሠፍቶች ሳይገደሉ የቀሩት ሰዎች አሁንም ከእጃቸው ሥራ ንስሓ አልገቡም፤ አጋንንትን እንዲሁም ማየት ወይም መስማት ወይም መሄድ የማይችሉትን፣ ከወርቅ፣ ከብር፣ ከናስ፣ ከድንጋይና ከዕንጨት የተሠሩትን ጣዖቶች ማምለክ አልተዉም፤ ደግሞም ከነፍስ ግድያቸው፣ ከጥንቈላ ሥራቸው፣ ከዝሙት ርኩሰታቸው ወይም ከስርቆት ተግባራቸው ንስሓ አልገቡም።
Compare
Explore ራእይ 9:20-21
2
ራእይ 9:3-4
ከጢሱም አንበጦች ወጥተው በምድር ላይ ወረዱ፤ እንደ ምድር ጊንጦች ሥልጣን ያለ ሥልጣን ተሰጣቸው። እነርሱም የምድርን ሣር ወይም ማናቸውንም የለመለመ ተክል ወይም ዛፍ እንዳይጐዱ፣ ነገር ግን የእግዚአብሔር ማኅተም በግምባራቸው ላይ የሌለባቸውን ሰዎች ብቻ እንዲጐዱ ተነገራቸው።
Explore ራእይ 9:3-4
3
ራእይ 9:1
አምስተኛው መልአክ መለከቱን ነፋ፤ ከሰማይ ወደ ምድር የወደቀውንም ኮከብ አየሁ፤ ኮከቡም የጥልቁ ጕድጓድ መክፈቻ ተሰጠው።
Explore ራእይ 9:1
4
ራእይ 9:5
እነርሱንም አምስት ወር ብቻ እንዲያሠቃዩአቸው እንጂ እንዲገድሏቸው ሥልጣን አልተሰጣቸውም፤ የሚሠቃዩትም ሥቃይ ጊንጥ ሰውን ሲነድፍ እንደሚሰማው ዐይነት ሥቃይ ነው።
Explore ራእይ 9:5
5
ራእይ 9:11
በላያቸው ንጉሥ ነበራቸው፤ እርሱም የጥልቁ ጕድጓድ መልአክ ነው፤ ስሙም በዕብራይስጥ “አብዶን”፣ በግሪክ ደግሞ “አጶልዮን” ይባላል።
Explore ራእይ 9:11
Home
Bible
Plans
Videos