1
ምሳሌ 15:1
አዲሱ መደበኛ ትርጒም
የለዘበ መልስ ቍጣን ያበርዳል፤ ክፉ ቃል ግን ቍጣን ይጭራል።
Compare
Explore ምሳሌ 15:1
2
ምሳሌ 15:33
እግዚአብሔርን መፍራት ጥበብን መማር ነው፤ ትሕትናም ክብርን ትቀድማለች።
Explore ምሳሌ 15:33
3
ምሳሌ 15:4
ፈውስ የምታመጣ ምላስ የሕይወት ዛፍ ናት፤ አታላይ ምላስ ግን መንፈስን ትሰብራለች።
Explore ምሳሌ 15:4
4
ምሳሌ 15:22
ምክር ሲጓደል ዕቅድ ይፋለሳል፤ በብዙ አማካሪዎች ግን ይሳካል።
Explore ምሳሌ 15:22
5
ምሳሌ 15:13
ደስተኛ ልብ ፊትን ያፈካል፤ የልብ ሐዘን ግን መንፈስን ይሰብራል።
Explore ምሳሌ 15:13
6
ምሳሌ 15:3
የእግዚአብሔር ዐይኖች በሁሉም ስፍራ ናቸው፤ ክፉዎችንም ደጎችንም ነቅተው ይመለከታሉ።
Explore ምሳሌ 15:3
7
ምሳሌ 15:16
እግዚአብሔርን ከመፍራት ጋር ያለ ጥቂት ነገር፣ ሁከት ካለበት ትልቅ ሀብት ይበልጣል።
Explore ምሳሌ 15:16
8
ምሳሌ 15:18
ግልፍተኛ ሰው ጠብ ያነሣሣል፤ ታጋሽ ሰው ግን ጠብን ያበርዳል።
Explore ምሳሌ 15:18
9
ምሳሌ 15:28
የጻድቅ ሰው ልብ የሚሰጠውን መልስ ያመዛዝናል፤ የክፉ ሰው አፍ ግን ክፋትን ያጐርፋል።
Explore ምሳሌ 15:28
Home
Bible
Plans
Videos