ከዚያም ወደ ኢየሩሳሌም ወስዶ በቤተ መቅደስ ጕልላት ላይ አቆመውና እንዲህ አለው፤ “የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንህ፣ እስቲ ራስህን ከዚህ ወደ ታች ወርውር፤ ምክንያቱም እንዲህ ተብሎ ተጽፏል፤
“ ‘ይጠብቁህ ዘንድ፣
መላእክቱን ስለ አንተ ያዝዛቸዋል፤
እግርህም ከድንጋይ ጋር እንዳይጋጭ፣
በእጆቻቸው ወደ ላይ አንሥተው ይይዙሃል።’ ”
ኢየሱስም፣ “ ‘ጌታ አምላክህን አትፈታተነው’ ተብሏል” ብሎ መለሰለት።