1
ዘሌዋውያን 26:12
አዲሱ መደበኛ ትርጒም
በመካከላችሁ እመላለሳለሁ፤ አምላካችሁ (ኤሎሂም) እሆናለሁ፤ እናንተም ሕዝቤ ትሆናላችሁ።
Compare
Explore ዘሌዋውያን 26:12
2
ዘሌዋውያን 26:4
ዝናብን በወቅቱ እሰጣችኋለሁ፤ ምድሪቱ እህሏን፣ የሜዳ ዛፎችም ፍሬያቸውን ይሰጣሉ።
Explore ዘሌዋውያን 26:4
3
ዘሌዋውያን 26:3
“ ‘በሥርዐቴ ብትሄዱ፣ ትእዛዜንም በጥንቃቄ ብትጠብቁ፣
Explore ዘሌዋውያን 26:3
4
ዘሌዋውያን 26:6
“ ‘በምድሪቱ ላይ ሰላምን እሰጣለሁ፤ ትተኛላችሁ፤ ማንም አያስፈራችሁም። ክፉ አራዊትን ከምድሪቱ አስወግዳለሁ፤ ሰይፍም በምድራችሁ ላይ አያልፍም።
Explore ዘሌዋውያን 26:6
5
ዘሌዋውያን 26:9
“ ‘ፊቴን ወደ እናንተ እመልሳለሁ፤ እንድታፈሩና እንድትበዙም አደርጋችኋለሁ፤ ቃል ኪዳኔንም ከእናንተ ጋር አጸናለሁ።
Explore ዘሌዋውያን 26:9
6
ዘሌዋውያን 26:13
ለግብፃውያን ባሪያዎች እንዳትሆኑ ከግብፅ ምድር ያወጣኋችሁ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ (ያህዌ ኤሎሂም) ነኝ፤ የባርነት ቀንበራችሁን ሰብሬ ቀና ብላችሁ እንድትሄዱ አድርጌአችኋለሁ።
Explore ዘሌዋውያን 26:13
7
ዘሌዋውያን 26:11
ማደሪያዬን በመካከላችሁ አደርጋለሁ፤ ነፍሴም አትጸየፋችሁም።
Explore ዘሌዋውያን 26:11
8
ዘሌዋውያን 26:1
“ ‘ትሰግዱላቸው ዘንድ ጣዖታትን አታብጁ፤ ምስል ወይም የማምለኪያ ዐምድ አታቁሙ፤ በምድራችሁም ላይ የተቀረጸ ድንጋይ አታኑሩ፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ (ያህዌ ኤሎሂም) ነኝ።
Explore ዘሌዋውያን 26:1
9
ዘሌዋውያን 26:10
የዓምናውን እህል እየበላችሁ ከጐተራው ሳያልቅ ለዘንድሮው እህል ደግሞ ቦታ ታስለቅቃላችሁ።
Explore ዘሌዋውያን 26:10
10
ዘሌዋውያን 26:8
ከእናንተ አምስቱ መቶውን፣ መቶውም ዐሥሩን ሺሕ ያሳድዳሉ፤ ጠላቶቻችሁም በፊታችሁ በሰይፍ ይወድቃሉ።
Explore ዘሌዋውያን 26:8
11
ዘሌዋውያን 26:5
የምትወቁት እህል፣ የወይን ዘለላ እስከምትቈርጡበት ጊዜ፣ የምትቈርጡትም የወይን ዘለላ፣ እህል እስከምትዘሩበት ጊዜ ያደርሷችኋል፤ ምግባችሁን እስክትጠግቡ ትበላላችሁ፤ በምድራችሁም ላይ በጸጥታ ትኖራላችሁ።
Explore ዘሌዋውያን 26:5
12
ዘሌዋውያን 26:7
ጠላቶቻችሁን ታሳድዳላችሁ፤ እነርሱም በፊታችሁ በሰይፍ ይወድቃሉ።
Explore ዘሌዋውያን 26:7
13
ዘሌዋውያን 26:2
“ ‘ሰንበታቴን ጠብቁ፤ መቅደሴን አክብሩ፤ እኔ እግዚአብሔር (ያህዌ) ነኝ።
Explore ዘሌዋውያን 26:2
Home
Bible
Plans
Videos