1
መሳፍንት 7:2
አዲሱ መደበኛ ትርጒም
እግዚአብሔር ጌዴዎንን እንዲህ አለው፤ “ምድያማውያንን በእጃቸው አሳልፌ እንዳልሰጥ አብረውህ ያሉት ሰዎች በጣም ብዙ ናቸው፤ እስራኤላውያን የገዛ ኀይላቸው እንዳዳናቸው በመቍጠር እንዳይታበዩብኝ፣
Compare
Explore መሳፍንት 7:2
2
መሳፍንት 7:7
እግዚአብሔርም ጌዴዎንን፣ “ውሃውን በእጃቸው እያፈሱ በጠጡት ሦስት መቶ ሰዎች አድናችኋለሁ፤ ምድያማውያንንም በእጃችሁ አሳልፌ እሰጣችኋለሁ፤ የቀሩት በሙሉ ወደየመጡበት ይመለሱ” አለው።
Explore መሳፍንት 7:7
3
መሳፍንት 7:3
‘ማንም የፈራ ቢኖር የገለዓድን ተራራ ትቶ ወደ መጣበት ይመለስ’ ብለህ ለሕዝቡ ዐውጅ።” ስለዚህ ሃያ ሁለቱ ሺሕ ሲመለሱ ዐሥሩ ሺሕ ብቻ ቀሩ።
Explore መሳፍንት 7:3
4
መሳፍንት 7:4
እግዚአብሔር ጌዴዎንን እንዲህ አለው፤ “አሁንም ሰዎቹ ብዙ ናቸው፤ ወደ ወንዝ ይዘሃቸው ውረድ፤ በዚያም እለይልሃለሁ። ‘ይህ ከአንተ ጋር ይሂድ’ የምለው፣ ከአንተ ጋር ይሄዳል፤ ነገር ግን፣ ‘ይህ ከአንተ ጋር አይሂድ’ የምለው፣ ከአንተ ጋር አይሄድም።”
Explore መሳፍንት 7:4
5
መሳፍንት 7:5-6
ስለዚህ ጌዴዎን ሰዎቹን ወደ ወንዝ ይዟቸው ወረደ፤ እዚያም እግዚአብሔር፤ “ውሻ በምላሱ እየጨለፈ እንደሚጠጣ ሁሉ፣ በምላሳቸው የሚጠጡትን፣ በጕልበታቸው ተንበርክከው ከሚጠጡት ለይ” አለው። ሦስት መቶ ሰዎች ውሃውን በእጃቸው እያፈሱ ጠጡ፤ የቀሩት ሁሉ ግን ለመጠጣት በጕልበታቸው ተንበረከኩ።
Explore መሳፍንት 7:5-6
Home
Bible
Plans
Videos