1
ኢሳይያስ 60:1
አዲሱ መደበኛ ትርጒም
“ብርሃንሽ መጥቷልና ተነሺ አብሪ፤ የእግዚአብሔርም ክብር ወጥቶልሻል።
Compare
Explore ኢሳይያስ 60:1
2
ኢሳይያስ 60:3
ሕዝቦች ወደ ብርሃንሽ፣ ነገሥታትም ወደ ንጋትሽ ጸዳል ይመጣሉ።
Explore ኢሳይያስ 60:3
3
ኢሳይያስ 60:2
እነሆ፤ ጨለማ ምድርን፣ ድቅድቅ ጨለማም ሕዝቦችን ይሸፍናል፤ ነገር ግን እግዚአብሔር ወጥቶልሻል፤ ክብሩንም ይገልጥልሻል።
Explore ኢሳይያስ 60:2
4
ኢሳይያስ 60:22
ከአንቺ ታናሽ የሆነው ሺሕ፣ ከሁሉም የመጨረሻው ታናሽ ኀያል መንግሥት ይሆናል፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤ ጊዜውም ሲደርስ ይህን በፍጥነት አደርጋለሁ።”
Explore ኢሳይያስ 60:22
5
ኢሳይያስ 60:19
ከእንግዲህ በቀን የፀሓይ ብርሃን አያስፈልግሽም፤ በሌሊትም የጨረቃ ብርሃን አያበራልሽም፤ እግዚአብሔር የዘላለም ብርሃን፣ አምላክሽም ክብርሽ ይሆናልና።
Explore ኢሳይያስ 60:19
6
ኢሳይያስ 60:20
ፀሓይሽ ከእንግዲህ አትጠልቅም፤ ጨረቃሽም ብርሃን መስጠቷን አታቋርጥም፤ እግዚአብሔር የዘላለም ብርሃንሽ ይሆናል፤ የሐዘንሽም ቀን ያከትማል።
Explore ኢሳይያስ 60:20
7
ኢሳይያስ 60:5
ከዚያም ታያለሽ፤ ታብረቀርቂያለሽ፤ ልብሽ ይዘልላል፤ በደስታም ይሞላል። በባሕሮች ያለው ሀብት ወደ አንቺ ይመጣል፤ የነገሥታትም ብልጽግና የአንቺ ይሆናል።
Explore ኢሳይያስ 60:5
8
ኢሳይያስ 60:4
“ቀና በዪ፤ ዙሪያሽን ተመልከቺ፤ ሁሉም ተሰብስበው ወደ አንቺ ይመጣሉ፤ ወንዶች ልጆችሽ ከሩቅ፣ ሴቶች ልጆችሽም በዕቅፍ ወደ አንቺ ይመጣሉ።
Explore ኢሳይያስ 60:4
9
ኢሳይያስ 60:21
ሕዝብሽም ሁሉ ጻድቃን ይሆናሉ፤ ምድሪቱንም ለዘላለም ይወርሳሉ፤ ለክብሬ መግለጫ ይሆኑ ዘንድ፣ የእጆቼ ሥራ፣ እኔ የተከልኋቸው ቍጥቋጦች ናቸው።
Explore ኢሳይያስ 60:21
10
ኢሳይያስ 60:18
ከእንግዲህ በምድርሽ ሁከት፣ በጠረፎችሽም ጥፋትና መፈራረስ አይሰማም፤ ነገር ግን ቅጥሮችሽን ድነት፣ በሮችሽንም ምስጋና ብለሽ ትጠሪያቸዋለሽ።
Explore ኢሳይያስ 60:18
11
ኢሳይያስ 60:11
በሮችሽ ምንጊዜም የተከፈቱ ይሆናሉ፤ ቀንም ሆነ ሌሊት ከቶ አይዘጉም፤ ይህም ሰዎች የመንግሥታትን ብልጽግና ወደ አንቺ እንዲያመጡ፣ ነገሥታታቸውም በድል ወደ አንቺ እንዲገቡ ነው።
Explore ኢሳይያስ 60:11
12
ኢሳይያስ 60:6
የግመል መንጋ፣ የምድያምና የጌፌር ግልገል ግመሎች ምድርሽን ይሞላሉ፤ ወርቅና ዕጣን ይዘው፣ የእግዚአብሔርን ምስጋና እያወጁ፣ ሁሉም ከሳባ ይመጣሉ።
Explore ኢሳይያስ 60:6
13
ኢሳይያስ 60:10
“ባዕዳን ቅጥሮችሽን ይሠራሉ፤ ነገሥታቶቻቸው ያገለግሉሻል፤ በቍጣዬ ብመታሽም፣ ርኅራኄዬን በፍቅር አሳይሻለሁ።
Explore ኢሳይያስ 60:10
14
ኢሳይያስ 60:15
“የተተውሽና የተጠላሽ፣ ማንም ሰው የማያልፍብሽ ብትሆኝም እንኳ፣ እኔ የዘላለም ትምክሕት፣ የትውልድም ሁሉ ደስታ አደርግሻለሁ።
Explore ኢሳይያስ 60:15
15
ኢሳይያስ 60:16
የመንግሥታትን ወተት ትጠጪያለሽ፤ የነገሥታትንም ጡት ትጠቢያለሽ፤ ከዚያም እኔ እግዚአብሔር አዳኝሽ፣ ቤዛሽም እኔ የያዕቆብ ኀያል እንደ ሆንሁ ታውቂያለሽ።
Explore ኢሳይያስ 60:16
Home
Bible
Plans
Videos