1
ዘፍጥረት 27:28-29
አዲሱ መደበኛ ትርጒም
እግዚአብሔር (ኤሎሂም) የሰማይን ጠል፣ የምድርንም በረከት፣ የተትረፈረፈ እህልና የወይን ጠጅ ይስጥህ። መንግሥታት ይገዙልህ፤ ሕዝቦችም ተደፍተው እጅ ይንሡህ፤ የወንድሞችህ ጌታ ሁን፤ የእናትህም ልጆች ተደፍተው እጅ ይንሡህ፤ የሚረግሙህ የተረገሙ ይሁኑ፤ የሚባርኩህ የተባረኩ ይሁኑ።”
Compare
Explore ዘፍጥረት 27:28-29
2
ዘፍጥረት 27:36
ዔሳውም፣ “ይህ ሰው ያዕቆብ መባሉ ትክክል አይደለምን? እኔን ሲያታልለኝ ይህ ሁለተኛ ጊዜው ነው፤ መጀመሪያ ብኵርናዬን ወሰደብኝ፤ አሁን ደግሞ ምርቃቴን ቀማኝ” አለ። ቀጥሎም፣ “ታዲያ ለእኔ ያስቀረኸው ምንም ምርቃት የለም?” ብሎ ጠየቀ።
Explore ዘፍጥረት 27:36
3
ዘፍጥረት 27:39-40
አባቱ ይስሐቅም እንዲህ ሲል መለሰለት፤ “መኖሪያህ ከምድር በረከት፣ ከላይም ከሰማይ ጠል የራቀ ይሆናል፤ በሰይፍ ትኖራለህ፤ የወንድምህም አገልጋይ ትሆናለህ። አምርረህ በተነሣህ ጊዜ ግን፣ ቀንበሩን ከጫንቃህ ላይ፣ ወዲያ ትጥላለህ።”
Explore ዘፍጥረት 27:39-40
4
ዘፍጥረት 27:38
ዔሳውም አባቱን፣ “አባቴ ሆይ፤ ምርቃትህ ይህችው ብቻ ናትን? እባክህ አባቴ፣ እኔንም መርቀኝ” አለው፤ ድምፁንም ከፍ አድርጎ አለቀሰ።
Explore ዘፍጥረት 27:38
Home
Bible
Plans
Videos