1
ዘፍጥረት 25:23
አዲሱ መደበኛ ትርጒም
እግዚአብሔርም (ያህዌ) እንዲህ አላት፤ “ወገኖች በማሕፀንሽ አሉ፤ ሁለትም ሕዝቦች ከውስጥሽ ተለያይተው ይወጣሉ፤ አንደኛው ከሌላው ይበረታል፤ ታላቁም ለታናሹ አገልጋይ ይሆናል” አላት።
Compare
Explore ዘፍጥረት 25:23
2
ዘፍጥረት 25:30
ዔሳውም ያዕቆብን፣ “ቶሎ በል፤ በጣም ርቦኛልና ከዚህ ቀይ ወጥ አብላኝ” አለው። ስለዚህም ስሙ ኤዶም ተባለ።
Explore ዘፍጥረት 25:30
3
ዘፍጥረት 25:21
ይስሐቅ፣ ርብቃ መካን ስለ ነበረች ስለ እርሷ ወደ እግዚአብሔር (ያህዌ) ጸለየ፤ እግዚአብሔርም (ያህዌ) ጸሎቱን ሰማ፤ ርብቃም ፀነሰች።
Explore ዘፍጥረት 25:21
4
ዘፍጥረት 25:32-33
ዔሳውም፣ “እነሆ፤ ልሞት ደርሻለሁ፤ ታዲያ ብኵርናው ምን ያደርግልኛል!” አለ። ያዕቆብም ዔሳውን፣ “እንግዲያማ፣ አስቀድመህ ማልልኝ” አለው፤ ስለዚህም ማለለት፤ ብኵርናውንም ለያዕቆብ ሸጠለት።
Explore ዘፍጥረት 25:32-33
5
ዘፍጥረት 25:26
ከዚያም ወንድሙ ተወለደ፤ በእጁም የዔሳውን ተረከዝ ይዞ ወጣ፤ ከዚህም የተነሣ ስሙ ያዕቆብ ተባለ። ርብቃ ልጆቿን ስትወልድ፣ ይስሐቅ የስድሳ ዓመት ሰው ነበር።
Explore ዘፍጥረት 25:26
6
ዘፍጥረት 25:28
ይስሐቅ ከዐደን የመጣ ሥጋ ደስ ይለው ስለ ነበር፣ ዔሳውን ይወድደው ነበር፤ ርብቃ ግን ያዕቆብን ትወድደው ነበር።
Explore ዘፍጥረት 25:28
Home
Bible
Plans
Videos