1
ዘዳግም 10:12-13
አዲሱ መደበኛ ትርጒም
አሁንም እስራኤል ሆይ፤ አምላክህ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) ከአንተ የሚፈልገው ምንድን ነው? አምላክህን እግዚአብሔርን (ኤሎሂም ያህዌ) እንድትፈራው፣ በመንገዶቹ ሁሉ እንድትሄድ፣ እንድትወድደው፣ በፍጹም ልብህ፣ በፍጹም ነፍስህ እንድታገለግለው፣ መልካም እንዲሆንልህና ዛሬ እኔ የምሰጥህን ትእዛዞችና ሥርዐቶች እንድትጠብቅ አይደለምን?
Compare
Explore ዘዳግም 10:12-13
2
ዘዳግም 10:17
አምላካችሁ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) የአማልክት አምላክ (ኤሎሂም)፣ የጌቶች ጌታ (አዶናይ) ታላቅ አምላክ (ኤሎሂም)፣ ኀያልና የሚያስፈራ፣ አድልዎ የማያደርግ፣ መማለጃም የማይቀበል ነውና።
Explore ዘዳግም 10:17
3
ዘዳግም 10:16
ስለዚህ የልባችሁን ሸለፈት ግረዙት፤ ከእንግዲህም ወዲያ ዐንገተ ደንዳና አትሁኑ።
Explore ዘዳግም 10:16
4
ዘዳግም 10:18
እርሱ አባት ለሌላቸውና ለመበለቶች ይፈርዳል፤ መጻተኛውንም ምግብና ልብስ በመስጠት ይወድዳል።
Explore ዘዳግም 10:18
5
ዘዳግም 10:21
እርሱ ውዳሴህ ነው፤ በገዛ ዐይኖችህ ያየሃቸውን፣ እነዚያን ታላላቅና አስፈሪ ነገሮች ያደረገልህ አምላክህ (ኤሎሂም) ነው።
Explore ዘዳግም 10:21
6
ዘዳግም 10:20
አምላክህን እግዚአብሔርን (ኤሎሂም ያህዌ) ፍራ፤ አምልከውም፤ ከእርሱም ጋር ተጣበቅ፤ በስሙም ማል።
Explore ዘዳግም 10:20
7
ዘዳግም 10:14
ሰማያት፣ ሰማየ ሰማያት፣ ምድርና በእርሷም ያለው ሁሉ የአምላክህ የእግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) ነው።
Explore ዘዳግም 10:14
8
ዘዳግም 10:19
ስለዚህ እናንተም በግብፅ ምድር መጻተኞች ነበራችሁና መጻተኛን ውደዱ።
Explore ዘዳግም 10:19
Home
Bible
Plans
Videos