1
1 ቆሮንቶስ 10:13
አዲሱ መደበኛ ትርጒም
በሰዎች ሁሉ ላይ ከደረሰው የተለየ ፈተና አልደረሰባችሁም፤ እግዚአብሔር ታማኝ ነው፤ ስለዚህ ከምትችሉት በላይ እንድትፈተኑ አይተዋችሁም፤ ነገር ግን በምትፈተኑበት ጊዜ ፈተናውን መታገሥ እንድትችሉ፣ መውጫ መንገዱን ያዘጋጅላችኋል።
Compare
Explore 1 ቆሮንቶስ 10:13
2
1 ቆሮንቶስ 10:31
እንግዲህ ስትበሉም ሆነ ስትጠጡ፣ ወይም ማንኛውንም ነገር ስታደርጉ፣ ሁሉንም ነገር ለእግዚአብሔር ክብር አድርጉት።
Explore 1 ቆሮንቶስ 10:31
3
1 ቆሮንቶስ 10:12
ስለዚህ ተደላድዬ ቆሜአለሁ የሚል ቢኖር እንዳይወድቅ ይጠንቀቅ።
Explore 1 ቆሮንቶስ 10:12
4
1 ቆሮንቶስ 10:23
“ሁሉ ነገር ተፈቅዷል”፤ ነገር ግን ሁሉም ነገር አይጠቅምም፤ “ሁሉም ነገር ተፈቅዷል”፤ ነገር ግን ሁሉም ነገር አያንጽም።
Explore 1 ቆሮንቶስ 10:23
5
1 ቆሮንቶስ 10:24
እያንዳንዱ ሰው የባልንጀራውን ጥቅም እንጂ የራሱን ብቻ አይፈልግ።
Explore 1 ቆሮንቶስ 10:24
Home
Bible
Plans
Videos