1
የሉቃስ ወንጌል 8:15
የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)
በመልካም ምድር የወደቀው ግን ቃሉን በበጎና በንጹሕ ልብ የሚሰሙና የሚጠብቁት፥ ታግሠውና ጨክነውም የሚያፈሩ ናቸው።
Сравни
Разгледайте የሉቃስ ወንጌል 8:15
2
የሉቃስ ወንጌል 8:14
በእሾህም መካከል የወደቀው ቃሉን ሰምተው የባለጠግነት ዐሳብ፥ የኑሮም መቈርቈር የተድላና የደስታ መጣፈጥም የሚአስጨንቃቸውና ፍሬ የማያፈሩ ናቸው።
Разгледайте የሉቃስ ወንጌል 8:14
3
የሉቃስ ወንጌል 8:13
በጭንጫም ላይ የወደቀው ሰምተው ነገሩን በደስታ የሚቀበሉት ናቸው፤ ነገር ግን ለጊዜው ያምናሉ እንጂ ሥር የላቸውም፤ መከራም በአገኛቸው ጊዜ ይክዳሉ።
Разгледайте የሉቃስ ወንጌል 8:13
4
የሉቃስ ወንጌል 8:25
እርሱም “እምነታችሁ ወዴት አለ?” አላቸው፤ እነርሱም ፈርተው ተደነቁ፤ እርስ በርሳቸውም፥ “ውኃም ነፋስም የሚታዘዙለት ይህ ማነው?” አሉ።
Разгледайте የሉቃስ ወንጌል 8:25
5
የሉቃስ ወንጌል 8:12
በመንገድ የወደቀው ቃሉን የሚሰሙ ናቸው፤ አምነውም እንዳይድኑ ሰይጣን መጥቶ ቃሉን ከልባቸው ይወስድባቸዋል።
Разгледайте የሉቃስ ወንጌል 8:12
6
የሉቃስ ወንጌል 8:17
የማይገለጥ የተሰወረ የለምና፤ የማይታይም ወደ ግልጥም የማይመጣ የተከደነ የለም፤
Разгледайте የሉቃስ ወንጌል 8:17
7
የሉቃስ ወንጌል 8:47-48
ሴቲቱም እንዳልተሰወረላት ባየች ጊዜ እየተንቀጠቀጠች ሄዳ ሰገደችለት፤ በሕዝቡም ሁሉ ፊት በምን ምክንያት ወደ እርሱ እንደ ቀረበችና የልብሱን ጫፍ እንደ ዳሰሰች ወዲያውም እንደ ዳነች ተናገረች። እርሱም፥ “ልጄ ሆይ፥ እምነትሽ አዳነችሽ፤ በሰላም ሂጂ” አላት።
Разгледайте የሉቃስ ወንጌል 8:47-48
8
የሉቃስ ወንጌል 8:24
ቀርበውም፥ “መምህር ሆይ፥ መምህር ሆይ፥ ልንጠፋ ነው” ብለው ቀሰቀሱት፤ ተነሥቶም ነፋሱንና የውኃዉን ማዕበል ገሠጻቸው፤ እነርሱም ዝም አሉ፤ ታላቅ ፀጥታም ሆነ።
Разгледайте የሉቃስ ወንጌል 8:24
Начало
Библия
Планове
Видеа