አምላኬ ሆይ፤ ንጹሕ ልብ ፍጠርልኝ፤
ቀና የሆነውንም መንፈስ በውስጤ አድስ።
ከፊትህ አትጣለኝ፤
ቅዱስ መንፈስህንም ከእኔ ላይ አትውሰድ።
የማዳንህን ደስታ መልስልኝ፤
በእሽታ መንፈስም ደግፈህ ያዘኝ።
እኔም ለሕግ ተላላፊዎች መንገድህን አስተምራለሁ፤
ኀጢአተኞችም ወደ አንተ ይመለሳሉ።
የድነቴ አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፤
ደም ከማፍሰስ አድነኝ፤
አንደበቴም ስለ ጽድቅህ በእልልታ ይዘምራል።
ጌታ ሆይ ከንፈሮቼን ክፈት፤
አፌም ምስጋናህን ያውጃል።