የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝሙር 18:1-15

መዝሙር 18:1-15 - ጕልበቴ እግዚአብሔር ሆይ፤ እወድድሃለሁ።

እግዚአብሔር ዐለቴ፣ መጠጊያዬና ታዳጊዬ ነው፤
አምላኬ የምሸሸግበት ዐለቴ፤
እርሱ ጋሻዬ፣ የድነቴ ቀንድና ዐምባዬ ነው።

ምስጋና የሚገባውን እግዚአብሔርን እጠራለሁ፤
ከጠላቶቼም እድናለሁ።

የሞት ገመድ ዐነቀኝ፤
ምናምንቴ ነገርም አጥለቀለቀኝ።
የሲኦል ገመድ ተጠመጠመብኝ፤
የሞት ወጥመድም ተጋረጠብኝ።

በተጨነቅሁ ጊዜ እግዚአብሔርን ጠራሁት፤
እንዲረዳኝም ወደ አምላኬ ጮኽሁ፤
እርሱም ከመቅደሱ ድምፄን ሰማ፤
ጩኸቴም በፊቱ ከጆሮው ደረሰ።
ምድር ተንቀጠቀጠች፤ ተናወጠችም፤
የተራሮችም መሠረቶች ተናጉ፤
እርሱ ተቈጥቷልና ተንቀጠቀጡ።
ከአፍንጫው ጢስ ወጣ፤
ከአፉ የሚባላ እሳት ነደደ፤
ከውስጡም ፍሙ ጋለ።
ሰማያትን ሰንጥቆ ወረደ፤
ከእግሩም በታች ጥቅጥቅ ያለ ደመና ነበረ።
በኪሩቤል ላይ ተቀምጦ በረረ፤
በነፋስም ክንፍ መጠቀ።
ጨለማን መሰወሪያው፣ በዙሪያውም አጐበሩ አደረገው፤
በዝናብ ዐዘል ጥቍር ደመናም ተሸፈነ።
በፊቱ ካለው ብርሃን የተነሣ፣
ደመናት፣ የበረዶ ድንጋይና መብረቅ ወጡ።
እግዚአብሔር ከሰማያት አንጐደጐደ፤
የልዑልም ድምፅ አስተጋባ።
ፍላጻውን ሰድዶ በተናቸው፤
ታላቅ መብረቆቹንም ልኮ አወካቸው።
እግዚአብሔር ሆይ፤ ከተግሣጽህ የተነሣ፣
ከአፍንጫህም እስትንፋስ የተነሣ፣
የባሕር ወለል ታየ፤
የምድር መሠረቶችም ተገለጡ።

ጕልበቴ እግዚአብሔር ሆይ፤ እወድድሃለሁ። እግዚአብሔር ዐለቴ፣ መጠጊያዬና ታዳጊዬ ነው፤ አምላኬ የምሸሸግበት ዐለቴ፤ እርሱ ጋሻዬ፣ የድነቴ ቀንድና ዐምባዬ ነው። ምስጋና የሚገባውን እግዚአብሔርን እጠራለሁ፤ ከጠላቶቼም እድናለሁ። የሞት ገመድ ዐነቀኝ፤ ምናምንቴ ነገርም አጥለቀለቀኝ። የሲኦል ገመድ ተጠመጠመብኝ፤ የሞት ወጥመድም ተጋረጠብኝ። በተጨነቅሁ ጊዜ እግዚአብሔርን ጠራሁት፤ እንዲረዳኝም ወደ አምላኬ ጮኽሁ፤ እርሱም ከመቅደሱ ድምፄን ሰማ፤ ጩኸቴም በፊቱ ከጆሮው ደረሰ። ምድር ተንቀጠቀጠች፤ ተናወጠችም፤ የተራሮችም መሠረቶች ተናጉ፤ እርሱ ተቈጥቷልና ተንቀጠቀጡ። ከአፍንጫው ጢስ ወጣ፤ ከአፉ የሚባላ እሳት ነደደ፤ ከውስጡም ፍሙ ጋለ። ሰማያትን ሰንጥቆ ወረደ፤ ከእግሩም በታች ጥቅጥቅ ያለ ደመና ነበረ። በኪሩቤል ላይ ተቀምጦ በረረ፤ በነፋስም ክንፍ መጠቀ። ጨለማን መሰወሪያው፣ በዙሪያውም አጐበሩ አደረገው፤ በዝናብ ዐዘል ጥቍር ደመናም ተሸፈነ። በፊቱ ካለው ብርሃን የተነሣ፣ ደመናት፣ የበረዶ ድንጋይና መብረቅ ወጡ። እግዚአብሔር ከሰማያት አንጐደጐደ፤ የልዑልም ድምፅ አስተጋባ። ፍላጻውን ሰድዶ በተናቸው፤ ታላቅ መብረቆቹንም ልኮ አወካቸው። እግዚአብሔር ሆይ፤ ከተግሣጽህ የተነሣ፣ ከአፍንጫህም እስትንፋስ የተነሣ፣ የባሕር ወለል ታየ፤ የምድር መሠረቶችም ተገለጡ።

መዝሙር 18:1-15