የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝሙር 119:1-56

መዝሙር 119:1-56 - መንገዳቸው ነቀፋ የሌለበት፣
በእግዚአብሔርም ሕግ የሚሄዱ የተባረኩ ናቸው።
ምስክርነቱን የሚጠብቁ፣
በፍጹምም ልብ የሚሹት የተባረኩ ናቸው፤
ዐመፅን አያደርጉም፤
ነገር ግን በመንገዱ ይሄዳሉ።
ጠንቅቀን እንጠብቃት ዘንድ፣
አንተ ሥርዐትን አዝዘሃል።
ሥርዐትህን እጠብቅ ዘንድ፣
ምነው መንገዴ ጽኑ በሆነልኝ ኖሮ!
ወደ ትእዛዞችህ ስመለከት፣
በዚያን ጊዜ አላፍርም።
የጽድቅ ፍርድህን ስማር፣
በቅን ልብ ምስጋና አቀርብልሃለሁ።
ሥርዐትህን እጠብቃለሁ፤
ፈጽመህ አትተወኝ።

ጕልማሳ መንገዱን እንዴት ያነጻል?
በቃልህ መሠረት በመኖር ነው።
በሙሉ ልቤ ፈለግሁህ፤
ከትእዛዞችህ ፈቀቅ እንዳልል አድርገኝ።
አንተን እንዳልበድል፣
ቃልህን በልቤ ሰወርሁ።
እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ ቡሩክ ነህ፤
ሥርዐትህን አስተምረኝ።
ከአንደበትህ የሚወጣውን ደንብ ሁሉ፣
በከንፈሬ እናገራለሁ።
ሰው በሀብቱ ብዛት ደስ እንደሚለው፣
ምስክርነትህን በመከተል ደስ ይለኛል።
ድንጋጌህን አሰላስላለሁ፤
ልቤን በመንገድህ ላይ ጥያለሁ።
በሥርዐትህ ደስ ይለኛል፤
ቃልህንም አልዘነጋም።

ሕያው እንድሆን፣ ቃልህንም እንድጠብቅ፣
ለአገልጋይህ መልካም አድርግ።
ከሕግህ ድንቅ ነገርን እንዳይ፣
ዐይኖቼን ክፈት።
እኔ በምድር ላይ መጻተኛ ነኝ፤
ትእዛዞችህን ከእኔ አትሰውር።
ዘወትር ደንብህን በመናፈቅ፣
ነፍሴ እጅግ ዛለች።
ከትእዛዞችህ የሳቱትን፣
እብሪተኞችንና ርጉሞችን ትገሥጻለህ።
ምስክርነትህን ጠብቄአለሁና፣
ስድብንና ንቀትን ከእኔ አርቅ።
ገዦች ተቀምጠው ቢዶልቱብኝ እንኳ፣
አገልጋይህ ሥርዐትህን ያሰላስላል።
ምስክርነትህ ለእኔ ደስታዬ ነው፤
መካሪዬም ነው።

ነፍሴ ከዐፈር ተጣበቀች፤
እንደ ቃልህ መልሰህ ሕያው አድርገኝ።
ስለ መንገዴ ገልጬ ነገርሁህ፤ አንተም መለስህልኝ፤
ሥርዐትህን አስተምረኝ።
የድንጋጌህን መንገድ እንዳስተውል አድርገኝ፤
እኔም ድንቅ ሥራህን አሰላስላለሁ።
ነፍሴ በሐዘን ተዝለፈለፈች፤
እንደ ቃልህ አበርታኝ።
የሽንገላን መንገድ ከእኔ አርቅ፤
ሕግህን በጸጋህ ስጠኝ።
የእውነትን መንገድ መርጫለሁ፤
ሕግህንም ፊት ለፊቴ አድርጌአለሁ።
እግዚአብሔር ሆይ፤ ከምስክርነትህ ጋር ተጣብቄአለሁ፤
አሳልፈህ ለውርደት አትስጠኝ።
ልቤን አስፍተህልኛልና፣
በትእዛዞችህ መንገድ እሮጣለሁ።

እግዚአብሔር ሆይ፤ የሥርዐትህን መንገድ አስተምረኝ፤
እኔም እስከ መጨረሻው እጠብቀዋለሁ።
ሕግህን እንድጠብቅ፣ በፍጹም ልቤም እንድታዘዘው፣ ማስተዋልን ስጠኝ።
በእርሷ ደስ ይለኛልና፣
በትእዛዝህ መንገድ ምራኝ።
ከራስ ጥቅም ይልቅ፣
ልቤን ወደ ምስክርነትህ አዘንብል።
ከንቱ ነገር ከማየት ዐይኖቼን መልስ፤
በራስህ መንገድ እንደ ገና ሕያው አድርገኝ።
ትፈራ ዘንድ፣
ለአገልጋይህ የገባኸውን ቃል ፈጽም።
የምፈራውን መዋረድ ከእኔ አርቅ፤
ደንብህ መልካም ነውና።
እነሆ፤ ድንጋጌህን ናፈቅሁ፤
በጽድቅህ ሕያው አድርገኝ።

እግዚአብሔር ሆይ፤ ምሕረትህ ወደ እኔ ይምጣ፤
ማዳንህም እንደ ቃልህ ይላክልኝ።
በቃልህ ታምኛለሁና፣
ለሚሰድቡኝ መልስ እሰጣለሁ።
ሕግህን ተስፋ አድርጌአለሁና፣
የእውነትን ቃል ከአፌ ፈጽመህ አታርቅ።
ከዘላለም እስከ ዘላለም፣
ሕግህን ዘወትር እጠብቃለሁ።
ሥርዐትህን እሻለሁና፣
እንደ ልቤ ወዲያ ወዲህ እመላለሳለሁ።
ምስክርነትህን በነገሥታት ፊት እናገራለሁ፤
ይህን በማድረግም ዕፍረት አይሰማኝም።
እኔ እወድደዋለሁና፣
በትእዛዝህ ደስ ይለኛል።
እጆቼን ወደምወዳቸው ትእዛዞችህ አነሣለሁ፤
ሥርዐትህንም አሰላስላለሁ።

ለአገልጋይህ የገባኸውን ቃል ዐስብ፤
በዚያ ተስፋ ሰጥተኸዋልና።
ቃልህ ሕያው ያደርገኛልና፣
ይህች በመከራዬ መጽናኛዬ ናት።
እብሪተኞች እጅግ ተሣለቁብኝ፤
እኔ ግን ከሕግህ ንቅንቅ አልልም።
እግዚአብሔር ሆይ፤ ከጥንት የነበረውን ድንጋጌህን አሰብሁ፤ በዚህም ተጽናናሁ።
ሕግህን ከተዉ ክፉዎች የተነሣ፣
ቍጣ ወረረኝ።
በእንግድነቴ አገር፣
ሥርዐትህ መዝሙሬ ናት።
እግዚአብሔር ሆይ፤ ስምህን በሌሊት ዐስባለሁ፤
ሕግህንም እጠብቃለሁ።
ሥርዐትህን እከተላለሁ፤
ይህችም ተግባሬ ሆነች።

መንገዳቸው ነቀፋ የሌለበት፣ በእግዚአብሔርም ሕግ የሚሄዱ የተባረኩ ናቸው። ምስክርነቱን የሚጠብቁ፣ በፍጹምም ልብ የሚሹት የተባረኩ ናቸው፤ ዐመፅን አያደርጉም፤ ነገር ግን በመንገዱ ይሄዳሉ። ጠንቅቀን እንጠብቃት ዘንድ፣ አንተ ሥርዐትን አዝዘሃል። ሥርዐትህን እጠብቅ ዘንድ፣ ምነው መንገዴ ጽኑ በሆነልኝ ኖሮ! ወደ ትእዛዞችህ ስመለከት፣ በዚያን ጊዜ አላፍርም። የጽድቅ ፍርድህን ስማር፣ በቅን ልብ ምስጋና አቀርብልሃለሁ። ሥርዐትህን እጠብቃለሁ፤ ፈጽመህ አትተወኝ። ጕልማሳ መንገዱን እንዴት ያነጻል? በቃልህ መሠረት በመኖር ነው። በሙሉ ልቤ ፈለግሁህ፤ ከትእዛዞችህ ፈቀቅ እንዳልል አድርገኝ። አንተን እንዳልበድል፣ ቃልህን በልቤ ሰወርሁ። እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ ቡሩክ ነህ፤ ሥርዐትህን አስተምረኝ። ከአንደበትህ የሚወጣውን ደንብ ሁሉ፣ በከንፈሬ እናገራለሁ። ሰው በሀብቱ ብዛት ደስ እንደሚለው፣ ምስክርነትህን በመከተል ደስ ይለኛል። ድንጋጌህን አሰላስላለሁ፤ ልቤን በመንገድህ ላይ ጥያለሁ። በሥርዐትህ ደስ ይለኛል፤ ቃልህንም አልዘነጋም። ሕያው እንድሆን፣ ቃልህንም እንድጠብቅ፣ ለአገልጋይህ መልካም አድርግ። ከሕግህ ድንቅ ነገርን እንዳይ፣ ዐይኖቼን ክፈት። እኔ በምድር ላይ መጻተኛ ነኝ፤ ትእዛዞችህን ከእኔ አትሰውር። ዘወትር ደንብህን በመናፈቅ፣ ነፍሴ እጅግ ዛለች። ከትእዛዞችህ የሳቱትን፣ እብሪተኞችንና ርጉሞችን ትገሥጻለህ። ምስክርነትህን ጠብቄአለሁና፣ ስድብንና ንቀትን ከእኔ አርቅ። ገዦች ተቀምጠው ቢዶልቱብኝ እንኳ፣ አገልጋይህ ሥርዐትህን ያሰላስላል። ምስክርነትህ ለእኔ ደስታዬ ነው፤ መካሪዬም ነው። ነፍሴ ከዐፈር ተጣበቀች፤ እንደ ቃልህ መልሰህ ሕያው አድርገኝ። ስለ መንገዴ ገልጬ ነገርሁህ፤ አንተም መለስህልኝ፤ ሥርዐትህን አስተምረኝ። የድንጋጌህን መንገድ እንዳስተውል አድርገኝ፤ እኔም ድንቅ ሥራህን አሰላስላለሁ። ነፍሴ በሐዘን ተዝለፈለፈች፤ እንደ ቃልህ አበርታኝ። የሽንገላን መንገድ ከእኔ አርቅ፤ ሕግህን በጸጋህ ስጠኝ። የእውነትን መንገድ መርጫለሁ፤ ሕግህንም ፊት ለፊቴ አድርጌአለሁ። እግዚአብሔር ሆይ፤ ከምስክርነትህ ጋር ተጣብቄአለሁ፤ አሳልፈህ ለውርደት አትስጠኝ። ልቤን አስፍተህልኛልና፣ በትእዛዞችህ መንገድ እሮጣለሁ። እግዚአብሔር ሆይ፤ የሥርዐትህን መንገድ አስተምረኝ፤ እኔም እስከ መጨረሻው እጠብቀዋለሁ። ሕግህን እንድጠብቅ፣ በፍጹም ልቤም እንድታዘዘው፣ ማስተዋልን ስጠኝ። በእርሷ ደስ ይለኛልና፣ በትእዛዝህ መንገድ ምራኝ። ከራስ ጥቅም ይልቅ፣ ልቤን ወደ ምስክርነትህ አዘንብል። ከንቱ ነገር ከማየት ዐይኖቼን መልስ፤ በራስህ መንገድ እንደ ገና ሕያው አድርገኝ። ትፈራ ዘንድ፣ ለአገልጋይህ የገባኸውን ቃል ፈጽም። የምፈራውን መዋረድ ከእኔ አርቅ፤ ደንብህ መልካም ነውና። እነሆ፤ ድንጋጌህን ናፈቅሁ፤ በጽድቅህ ሕያው አድርገኝ። እግዚአብሔር ሆይ፤ ምሕረትህ ወደ እኔ ይምጣ፤ ማዳንህም እንደ ቃልህ ይላክልኝ። በቃልህ ታምኛለሁና፣ ለሚሰድቡኝ መልስ እሰጣለሁ። ሕግህን ተስፋ አድርጌአለሁና፣ የእውነትን ቃል ከአፌ ፈጽመህ አታርቅ። ከዘላለም እስከ ዘላለም፣ ሕግህን ዘወትር እጠብቃለሁ። ሥርዐትህን እሻለሁና፣ እንደ ልቤ ወዲያ ወዲህ እመላለሳለሁ። ምስክርነትህን በነገሥታት ፊት እናገራለሁ፤ ይህን በማድረግም ዕፍረት አይሰማኝም። እኔ እወድደዋለሁና፣ በትእዛዝህ ደስ ይለኛል። እጆቼን ወደምወዳቸው ትእዛዞችህ አነሣለሁ፤ ሥርዐትህንም አሰላስላለሁ። ለአገልጋይህ የገባኸውን ቃል ዐስብ፤ በዚያ ተስፋ ሰጥተኸዋልና። ቃልህ ሕያው ያደርገኛልና፣ ይህች በመከራዬ መጽናኛዬ ናት። እብሪተኞች እጅግ ተሣለቁብኝ፤ እኔ ግን ከሕግህ ንቅንቅ አልልም። እግዚአብሔር ሆይ፤ ከጥንት የነበረውን ድንጋጌህን አሰብሁ፤ በዚህም ተጽናናሁ። ሕግህን ከተዉ ክፉዎች የተነሣ፣ ቍጣ ወረረኝ። በእንግድነቴ አገር፣ ሥርዐትህ መዝሙሬ ናት። እግዚአብሔር ሆይ፤ ስምህን በሌሊት ዐስባለሁ፤ ሕግህንም እጠብቃለሁ። ሥርዐትህን እከተላለሁ፤ ይህችም ተግባሬ ሆነች።

መዝሙር 119:1-56