እግዚአብሔር መሓሪና ይቅር ባይ፣
ለቍጣ የዘገየ፣ ፍቅሩም የበዛ ነው።
እርሱ ሁልጊዜ በደልን አይከታተልም፤
ለዘላለምም አይቈጣም።
እንደ ኀጢአታችን አልመለሰልንም፤
እንደ በደላችንም አልከፈለንም።
ሰማይ ከምድር ከፍ እንደሚል፣
እንዲሁ ለሚፈሩት ምሕረቱ ታላቅ ናት።
ምሥራቅ ከምዕራብ እንደሚርቅ፣
መተላለፋችንን በዚያው መጠን ከእኛ አስወገደ።
አባት ለልጆቹ እንደሚራራ፣
እግዚአብሔር ለሚፈሩት እንዲሁ ይራራል።