ምሳሌ 21:1-16

ምሳሌ 21:1-16 - የንጉሥ ልብ በእግዚአብሔር እጅ ነው፤
እርሱም እንደ ቦይ ውሃ ደስ ወዳሠኘው ይመራዋል።
ለሰው መንገዱ ሁሉ ቀና ይመስለዋል፤
እግዚአብሔር ግን ልብን ይመዝናል።

ከመሥዋዕት ይልቅ ጽድቅንና ፍትሕን ማድረግ፣
በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት አለው።

ትዕቢተኛ ዐይን፣ እብሪተኛ ልብ፣
የክፉዎችም መብራት ኀጢአት ናቸው።

የትጉህ ሰው ዕቅድ ወደ ትርፍ ያመራል፤
ችኰላም ወደ ድኽነት ያደርሳል።

በሐሰተኛ አንደበት የተገኘ ሀብት፣
በንኖ የሚጠፋ ተን፣ ለሞትም የሚያበቃ ወጥመድ ነው።

ክፉዎችን ዐመፃቸው ይጠራርጋቸዋል፤
ቅን ነገር ማድረግ አይወድዱምና።

የበደለኛ መንገድ ጠማማ ነው፤
የንጹሕ ሰው ጠባይ ግን ቀና ነው።

ከጨቅጫቃ ሚስት ጋራ በአንድ ቤት ከመኖር፣
በጣራ ማእዘን ላይ መኖር ይሻላል።

ክፉ ሰው ክፋትን አጥብቆ ይመኛል፤
ባልንጀራውም ከርሱ ዘንድ ርኅራኄን አያገኝም።

ፌዘኛ ሲቀጣ፣ አላዋቂ ጥበብን ያተርፋል፤
ጠቢብ ሰው ቢማር ዕውቀትን ያገኛል።

ጻድቁ የክፉዎችን ቤት ልብ ብሎ ይመለከታል፤
ክፉዎችንም ያጠፋቸዋል።

ሰው የድኾችን ጩኸት ላለመስማት ጆሮውን ቢዘጋ፣
እርሱም ይጮኻል፤ መልስም አያገኝም።

በስውር የተደረገ ስጦታ ቍጣን ያበርዳል፤
በጕያ የተሸሸገ እጅ መንሻም ታላቅ ቍጣን ጸጥ ያደርጋል።

ፍትሕ ሲሰፍን ጻድቁን ደስ ያሠኘዋል፤
ክፉ አድራጊዎችን ግን ያሸብራል።

የማስተዋልን መንገድ የሚስት ሰው፣
በሙታን ጉባኤ ያርፋል።

የንጉሥ ልብ በእግዚአብሔር እጅ ነው፤ እርሱም እንደ ቦይ ውሃ ደስ ወዳሠኘው ይመራዋል። ለሰው መንገዱ ሁሉ ቀና ይመስለዋል፤ እግዚአብሔር ግን ልብን ይመዝናል። ከመሥዋዕት ይልቅ ጽድቅንና ፍትሕን ማድረግ፣ በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት አለው። ትዕቢተኛ ዐይን፣ እብሪተኛ ልብ፣ የክፉዎችም መብራት ኀጢአት ናቸው። የትጉህ ሰው ዕቅድ ወደ ትርፍ ያመራል፤ ችኰላም ወደ ድኽነት ያደርሳል። በሐሰተኛ አንደበት የተገኘ ሀብት፣ በንኖ የሚጠፋ ተን፣ ለሞትም የሚያበቃ ወጥመድ ነው። ክፉዎችን ዐመፃቸው ይጠራርጋቸዋል፤ ቅን ነገር ማድረግ አይወድዱምና። የበደለኛ መንገድ ጠማማ ነው፤ የንጹሕ ሰው ጠባይ ግን ቀና ነው። ከጨቅጫቃ ሚስት ጋራ በአንድ ቤት ከመኖር፣ በጣራ ማእዘን ላይ መኖር ይሻላል። ክፉ ሰው ክፋትን አጥብቆ ይመኛል፤ ባልንጀራውም ከርሱ ዘንድ ርኅራኄን አያገኝም። ፌዘኛ ሲቀጣ፣ አላዋቂ ጥበብን ያተርፋል፤ ጠቢብ ሰው ቢማር ዕውቀትን ያገኛል። ጻድቁ የክፉዎችን ቤት ልብ ብሎ ይመለከታል፤ ክፉዎችንም ያጠፋቸዋል። ሰው የድኾችን ጩኸት ላለመስማት ጆሮውን ቢዘጋ፣ እርሱም ይጮኻል፤ መልስም አያገኝም። በስውር የተደረገ ስጦታ ቍጣን ያበርዳል፤ በጕያ የተሸሸገ እጅ መንሻም ታላቅ ቍጣን ጸጥ ያደርጋል። ፍትሕ ሲሰፍን ጻድቁን ደስ ያሠኘዋል፤ ክፉ አድራጊዎችን ግን ያሸብራል። የማስተዋልን መንገድ የሚስት ሰው፣ በሙታን ጉባኤ ያርፋል።

ምሳሌ 21:1-16