ምሳሌ 15:16-33

ምሳሌ 15:16-33 - እግዚአብሔርን ከመፍራት ጋራ ያለ ጥቂት ነገር፣
ሁከት ካለበት ትልቅ ሀብት ይበልጣል።

ፍቅር ባለበት ጐመን መብላት፣
ጥላቻ ባለበት የሰባ ፍሪዳ ከመብላት ይሻላል።

ግልፍተኛ ሰው ጠብ ያነሣሣል፤
ታጋሽ ሰው ግን ጠብን ያበርዳል።

የሰነፍ መንገድ በእሾኽ የታጠረች ናት፤
የቅኖች መንገድ ግን የተጠረገ አውራ ጐዳና ነው።

ጠቢብ ልጅ አባቱን ደስ ያሰኛል፤
ሞኝ ሰው ግን እናቱን ይንቃል።

ልበ ቢስ ሰው ቂልነት ያስደስተዋል፤
አስተዋይ ሰው ግን ቀጥተኛውን መንገድ ይከተላል።

ምክር ሲጓደል ዕቅድ ይፋለሳል፤
በብዙ አማካሪዎች ግን ይሳካል።

ሰው ተገቢ መልስ በመስጠት ደስታን ያገኛል፤
በወቅቱም የተሰጠ ቃል ምንኛ መልካም ነው!

ወደ ሲኦል ከመውረድ እንዲድን፣
የሕይወት መንገድ ጠቢቡን ሰው ወደ ላይ ትመራዋለች።

እግዚአብሔር የትዕቢተኛውን ቤት ያፈርሰዋል፤
የመበለቲቱን ዳር ድንበር ግን እንዳይደፈር ይጠብቃል።

እግዚአብሔር የክፉውን ሰው ሐሳብ ይጸየፋል፤
የንጹሓን ሐሳብ ግን ደስ ያሠኘዋል።

ስስታም ሰው በቤተ ሰቡ ላይ ችግር ያመጣል፤
ጕቦን የሚጠላ ግን በሕይወት ይኖራል።

የጻድቅ ሰው ልብ የሚሰጠውን መልስ ያመዛዝናል፤
የክፉ ሰው አፍ ግን ክፋትን ያጐርፋል።

እግዚአብሔር ከክፉዎች ሩቅ ነው፤
የጻድቃንን ጸሎት ግን ይሰማል።

ብሩህ ገጽታ ልብን ደስ ያሰኛል፤
መልካም ዜናም ዐጥንትን ያለመልማል።

ሕይወት ሰጪ የሆነውን ተግሣጽ የሚሰማ፣
በጠቢባን መካከል ይኖራል።

ተግሣጽን የሚንቅ ራሱን ይንቃል፤
ዕርምትን የሚቀበል ግን ማስተዋልን ያገኛል።

እግዚአብሔርን መፍራት ጥበብን መማር ነው፤
ትሕትናም ክብርን ትቀድማለች።

እግዚአብሔርን ከመፍራት ጋራ ያለ ጥቂት ነገር፣ ሁከት ካለበት ትልቅ ሀብት ይበልጣል። ፍቅር ባለበት ጐመን መብላት፣ ጥላቻ ባለበት የሰባ ፍሪዳ ከመብላት ይሻላል። ግልፍተኛ ሰው ጠብ ያነሣሣል፤ ታጋሽ ሰው ግን ጠብን ያበርዳል። የሰነፍ መንገድ በእሾኽ የታጠረች ናት፤ የቅኖች መንገድ ግን የተጠረገ አውራ ጐዳና ነው። ጠቢብ ልጅ አባቱን ደስ ያሰኛል፤ ሞኝ ሰው ግን እናቱን ይንቃል። ልበ ቢስ ሰው ቂልነት ያስደስተዋል፤ አስተዋይ ሰው ግን ቀጥተኛውን መንገድ ይከተላል። ምክር ሲጓደል ዕቅድ ይፋለሳል፤ በብዙ አማካሪዎች ግን ይሳካል። ሰው ተገቢ መልስ በመስጠት ደስታን ያገኛል፤ በወቅቱም የተሰጠ ቃል ምንኛ መልካም ነው! ወደ ሲኦል ከመውረድ እንዲድን፣ የሕይወት መንገድ ጠቢቡን ሰው ወደ ላይ ትመራዋለች። እግዚአብሔር የትዕቢተኛውን ቤት ያፈርሰዋል፤ የመበለቲቱን ዳር ድንበር ግን እንዳይደፈር ይጠብቃል። እግዚአብሔር የክፉውን ሰው ሐሳብ ይጸየፋል፤ የንጹሓን ሐሳብ ግን ደስ ያሠኘዋል። ስስታም ሰው በቤተ ሰቡ ላይ ችግር ያመጣል፤ ጕቦን የሚጠላ ግን በሕይወት ይኖራል። የጻድቅ ሰው ልብ የሚሰጠውን መልስ ያመዛዝናል፤ የክፉ ሰው አፍ ግን ክፋትን ያጐርፋል። እግዚአብሔር ከክፉዎች ሩቅ ነው፤ የጻድቃንን ጸሎት ግን ይሰማል። ብሩህ ገጽታ ልብን ደስ ያሰኛል፤ መልካም ዜናም ዐጥንትን ያለመልማል። ሕይወት ሰጪ የሆነውን ተግሣጽ የሚሰማ፣ በጠቢባን መካከል ይኖራል። ተግሣጽን የሚንቅ ራሱን ይንቃል፤ ዕርምትን የሚቀበል ግን ማስተዋልን ያገኛል። እግዚአብሔርን መፍራት ጥበብን መማር ነው፤ ትሕትናም ክብርን ትቀድማለች።

ምሳሌ 15:16-33