አንዱ በለጋስነት ይሰጣል፤ ሆኖም ይበልጥ ያገኛል፤
ሌላው ያለ መጠን ይሰስታል፤ ግን ይደኸያል።
ለጋስ ይበለጽጋል፤
ሌሎችን የሚያረካም ራሱ ይረካል።
በድብቅ እህል የሚያከማቸውን ሕዝብ ይረግመዋል፤
አውጥቶ የሚሸጥ ግን በረከት ይጐናጸፋል።
በጎ ነገርን ተግቶ የሚሻ በጎ ነገር ይጠብቀዋል፤
ክፉ ነገር የሚፈልገውን ግን ክፉ ያገኘዋል።
በሀብቱ የሚታመን ሁሉ ይወድቃል፤
ጻድቃን ግን እንደ አረንጓዴ ቅጠል ይለመልማሉ።