ምሳሌ 10:16-32

ምሳሌ 10:16-32 - የጻድቃን ደመወዝ ሕይወት ታስገኝላቸዋለች፤
የክፉዎች ትርፍ ግን ቅጣትን ታመጣባቸዋለች።

ተግሣጽን ነቅቶ የሚጠብቅ የሕይወትን መንገድ ያሳያል፤
ዕርምትን የማይቀበል ግን ሌሎችን ወደ ስሕተት ይመራል።

ጥላቻውን የሚሸሽግ ሐሰተኛ አንደበት ያለው ነው፤
ሐሜትን የሚዘራ ሁሉ ሞኝ ነው።

ከቃላት ብዛት ኀጢአት አይታጣም፤
አንደበቱን የሚገታ ግን ጠቢብ ነው።

የጻድቅ አንደበት የነጠረ ብር ነው፤
የክፉ ሰው ልብ ግን ርባና የለውም።

የጻድቃን ከንፈሮች ብዙዎችን ያንጻሉ፤
ቂሎች ግን በልበ ቢስነት ይሞታሉ።

የእግዚአብሔር በረከት ብልጽግናን ታመጣለች፤
መከራንም አያክልባትም።

ሞኝ ሰው በክፉ ተግባር ይደሰታል፤
አስተዋይ ሰው ግን በጥበብ ደስ ይለዋል።

ክፉ ሰው የፈራው ይደርስበታል፤
ጻድቅ የሚመኘው ይፈጸምለታል።

ዐውሎ ነፋስ ሲነሣ ክፉዎች ተጠራርገው ይወሰዳሉ፤
ጻድቃን ግን ለዘላለም ጸንተው ይኖራሉ።

ሖምጣጤ ጥርስን፣ ጢስ ዐይንን እንደሚጐዳ፣
ሰነፍም ለሚልኩት እንዲሁ ነው።

እግዚአብሔርን መፍራት ዕድሜን ያረዝማል፤
የክፉዎች ዕድሜ ግን በዐጭር ይቀጫል።

የጻድቃን አለኝታ ደስታ ነው፤
የክፉዎች ተስፋ ግን ከንቱ ሆኖ ይቀራል።

የእግዚአብሔር መንገድ ለጻድቃን መጠጊያ፣
ክፉ ለሚያደርጉ ግን መጥፊያቸው ነው።

ጻድቃን ፈጽሞ አይነቀሉም፤
ክፉዎች ግን በምድር አይኖሩም።

የጻድቃን አንደበት ጥበብን ያፈልቃል፤
ጠማማ ምላስ ግን ትቈረጣለች።

የጻድቃን ከንፈሮች ተገቢውን ነገር ያውቃሉ፤
የክፉዎች አንደበት ግን የሚያውቀው ጠማማውን ብቻ ነው።

የጻድቃን ደመወዝ ሕይወት ታስገኝላቸዋለች፤ የክፉዎች ትርፍ ግን ቅጣትን ታመጣባቸዋለች። ተግሣጽን ነቅቶ የሚጠብቅ የሕይወትን መንገድ ያሳያል፤ ዕርምትን የማይቀበል ግን ሌሎችን ወደ ስሕተት ይመራል። ጥላቻውን የሚሸሽግ ሐሰተኛ አንደበት ያለው ነው፤ ሐሜትን የሚዘራ ሁሉ ሞኝ ነው። ከቃላት ብዛት ኀጢአት አይታጣም፤ አንደበቱን የሚገታ ግን ጠቢብ ነው። የጻድቅ አንደበት የነጠረ ብር ነው፤ የክፉ ሰው ልብ ግን ርባና የለውም። የጻድቃን ከንፈሮች ብዙዎችን ያንጻሉ፤ ቂሎች ግን በልበ ቢስነት ይሞታሉ። የእግዚአብሔር በረከት ብልጽግናን ታመጣለች፤ መከራንም አያክልባትም። ሞኝ ሰው በክፉ ተግባር ይደሰታል፤ አስተዋይ ሰው ግን በጥበብ ደስ ይለዋል። ክፉ ሰው የፈራው ይደርስበታል፤ ጻድቅ የሚመኘው ይፈጸምለታል። ዐውሎ ነፋስ ሲነሣ ክፉዎች ተጠራርገው ይወሰዳሉ፤ ጻድቃን ግን ለዘላለም ጸንተው ይኖራሉ። ሖምጣጤ ጥርስን፣ ጢስ ዐይንን እንደሚጐዳ፣ ሰነፍም ለሚልኩት እንዲሁ ነው። እግዚአብሔርን መፍራት ዕድሜን ያረዝማል፤ የክፉዎች ዕድሜ ግን በዐጭር ይቀጫል። የጻድቃን አለኝታ ደስታ ነው፤ የክፉዎች ተስፋ ግን ከንቱ ሆኖ ይቀራል። የእግዚአብሔር መንገድ ለጻድቃን መጠጊያ፣ ክፉ ለሚያደርጉ ግን መጥፊያቸው ነው። ጻድቃን ፈጽሞ አይነቀሉም፤ ክፉዎች ግን በምድር አይኖሩም። የጻድቃን አንደበት ጥበብን ያፈልቃል፤ ጠማማ ምላስ ግን ትቈረጣለች። የጻድቃን ከንፈሮች ተገቢውን ነገር ያውቃሉ፤ የክፉዎች አንደበት ግን የሚያውቀው ጠማማውን ብቻ ነው።

ምሳሌ 10:16-32