የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ሚክያስ 5:1-9

ሚክያስ 5:1-9 - አንቺ የጭፍሮች ከተማ ሆይ፤
ጭፍሮችሽን አሰልፊ፤
ከበባ ተደርጎብናልና።
የእስራኤልን ገዥ፣
ጕንጩን በበትር ይመቱታል።

“አንቺ ግን፣ ቤተ ልሔም ኤፍራታ ሆይ፤
ከይሁዳ ነገዶች መካከል ትንሿ ብትሆኚም፣
አመጣጡ ከጥንት፣
ከቀድሞ ዘመን የሆነ፣
የእስራኤል ገዥ፣
ከአንቺ ይወጣልኛል።”

ስለዚህ ወላዲቱ አምጣ እስክትገላገል ድረስ፣
እስራኤል ትተዋለች፤
የተቀሩት ወንድሞቹም፣
ተመልሰው ከእስራኤላውያን ጋር ይቀላቀላሉ።

በእግዚአብሔር ኀይል፣
በአምላኩ በእግዚአብሔር ስም ታላቅነት፣
ጸንቶ ይቆማል፤ መንጋውንም ይጠብቃል።
በዚያን ጊዜ ኀያልነቱ እስከ ምድር ዳርቻ ስለሚደርስ፣
ተደላድለው ይኖራሉ።
እርሱም ሰላማቸው ይሆናል።

አሦራዊ ምድራችንን ሲወርር፣
ምሽጎቻችንንም ጥሶ ሲገባ፣
ሰባት እረኞችን፣
እንዲያውም ስምንት አለቆችን እናስነሣበታለን።
የአሦርን ምድር በሰይፍ፣
የናምሩድን ምድር በተመዘዘ ሰይፍ ይገዛሉ፤
አሦራዊው ምድራችንን ሲወርር፣
ዳር ድንበራችንን ሲደፍር፣
እርሱ ነጻ ያወጣናል።

የያዕቆብ ትሩፍ፣
በብዙ አሕዛብ መካከል
ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደሚወርድ ጠል፣
በሣር ላይ እንደሚጥል ካፊያ፣
ሰውን እንደማይጠብቅ፣
የሰውንም ልጆች ተስፋ እንደማያደርግ ሰው ይሆናል።
በዱር አራዊት መካከል እንዳለ አንበሳ፣
በእግሩ እየጨፈላለቀ እንደሚሄድ፣
የሰበረውን ማንም ሊነጥቀው እንደማይችል፣
በበግ መንጋ መካከል እንዳለ፣
እንደ ደቦል አንበሳ ሁሉ፣
የያዕቆብም ትሩፍ፣ በአሕዛብ ዘንድ፣ በብዙም ሕዝብ መካከል እንደዚሁ ይሆናል።
እጅህ በጠላቶችህ ላይ በድል አድራጊነት ከፍ ከፍ ትላለች፤
ጠላቶችህም ሁሉ ይጠፋሉ።

አንቺ የጭፍሮች ከተማ ሆይ፤ ጭፍሮችሽን አሰልፊ፤ ከበባ ተደርጎብናልና። የእስራኤልን ገዥ፣ ጕንጩን በበትር ይመቱታል። “አንቺ ግን፣ ቤተ ልሔም ኤፍራታ ሆይ፤ ከይሁዳ ነገዶች መካከል ትንሿ ብትሆኚም፣ አመጣጡ ከጥንት፣ ከቀድሞ ዘመን የሆነ፣ የእስራኤል ገዥ፣ ከአንቺ ይወጣልኛል።” ስለዚህ ወላዲቱ አምጣ እስክትገላገል ድረስ፣ እስራኤል ትተዋለች፤ የተቀሩት ወንድሞቹም፣ ተመልሰው ከእስራኤላውያን ጋር ይቀላቀላሉ። በእግዚአብሔር ኀይል፣ በአምላኩ በእግዚአብሔር ስም ታላቅነት፣ ጸንቶ ይቆማል፤ መንጋውንም ይጠብቃል። በዚያን ጊዜ ኀያልነቱ እስከ ምድር ዳርቻ ስለሚደርስ፣ ተደላድለው ይኖራሉ። እርሱም ሰላማቸው ይሆናል። አሦራዊ ምድራችንን ሲወርር፣ ምሽጎቻችንንም ጥሶ ሲገባ፣ ሰባት እረኞችን፣ እንዲያውም ስምንት አለቆችን እናስነሣበታለን። የአሦርን ምድር በሰይፍ፣ የናምሩድን ምድር በተመዘዘ ሰይፍ ይገዛሉ፤ አሦራዊው ምድራችንን ሲወርር፣ ዳር ድንበራችንን ሲደፍር፣ እርሱ ነጻ ያወጣናል። የያዕቆብ ትሩፍ፣ በብዙ አሕዛብ መካከል ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደሚወርድ ጠል፣ በሣር ላይ እንደሚጥል ካፊያ፣ ሰውን እንደማይጠብቅ፣ የሰውንም ልጆች ተስፋ እንደማያደርግ ሰው ይሆናል። በዱር አራዊት መካከል እንዳለ አንበሳ፣ በእግሩ እየጨፈላለቀ እንደሚሄድ፣ የሰበረውን ማንም ሊነጥቀው እንደማይችል፣ በበግ መንጋ መካከል እንዳለ፣ እንደ ደቦል አንበሳ ሁሉ፣ የያዕቆብም ትሩፍ፣ በአሕዛብ ዘንድ፣ በብዙም ሕዝብ መካከል እንደዚሁ ይሆናል። እጅህ በጠላቶችህ ላይ በድል አድራጊነት ከፍ ከፍ ትላለች፤ ጠላቶችህም ሁሉ ይጠፋሉ።

ሚክያስ 5:1-9