ኢዩኤል 2:1-17

ኢዩኤል 2:1-17 - በጽዮን መለከትን ንፉ፤
በቅዱሱ ተራራዬም የማስጠንቀቂያውን ድምፅ አሰሙ።

በምድሪቱ የሚኖሩ ሁሉ ይንቀጥቀጡ፤
የእግዚአብሔር ቀን ቀርቧልና፤
እርሱም በደጅ ነው።
ይህም የጨለማና የጭጋግ ቀን፣
የደመናና የድቅድቅ ጨለማ ቀን ነው።
የንጋት ብርሃን በተራሮች ላይ እንደሚወጣ፣
ኀያልና ብዙ ሰራዊት ይመጣል፤
ከጥንት እንዲህ ዐይነት ከቶ አልነበረም፤
በሚመጡትም ዘመናት እንዲህ ዐይነት ከቶ አይሆንም።

በፊታቸው፣ እሳት ይባላል፤
በኋላቸውም ነበልባል ይለበልባል፤
በፊታቸው ምድሪቱ እንደ ዔድን ገነት ናት፤
በኋላቸውም የሚቀረው ባዶ ምድረ በዳ ነው፤
ምንም አያመልጣቸውም።
መልካቸው እንደ ፈረስ መልክ ነው፤
እንደ ጦር ፈረስም ይጋልባሉ።
ገለባ እንደሚበላ እንደሚንጣጣ እሳት፣
ለጦርነት እንደ ተዘጋጀ ኀያል ሰራዊት፣
የሠረገሎችን ድምፅ የሚመስል ድምፅ እያሰሙ፣
በተራሮች ጫፍ ላይ ይዘልላሉ።

በእነርሱ ፊት ሕዝቦች ይርዳሉ፤
የሁሉም ፊት ይገረጣል።
እንደ ተዋጊዎች ድንገት አደጋ ይጥላሉ፤
እንደ ወታደሮችም ቅጥርን ይዘልላሉ፤
ከመንገዳቸውም ሳይወጡ፣
አቅጣጫ ይዘው ይጓዛሉ።
እርስ በርሳቸው አይገፋፉም፤
እያንዳንዱ መሥመሩን ጠብቆ ይሄዳል፤
መሥመራቸውን ሳይለቁ፣
መከላከያውን ሰብረው ያልፋሉ።
ከተማዪቱን ይወርራሉ፤
በቅጥሩም ላይ ይዘልላሉ፤
በቤቶች ላይ ዘልለው ይወጣሉ፤
እንደ ሌባም በመስኮት ይገባሉ።

ምድር በፊታቸው ትንቀጠቀጣለች፤
ሰማይም ይናወጣል፤
ፀሓይና ጨረቃ ይጨልማሉ፤
ከዋክብትም ከእንግዲህ ወዲያ አያበሩም።
በሰራዊቱ ፊት፣
እግዚአብሔር ያንጐደጕዳል፤
የሰራዊቱ ብዛት ስፍር ቍጥር የለውም፤
ትእዛዙንም የሚያደርግ እርሱ ኀያል ነው፤
የእግዚአብሔር ቀን ታላቅ፣
እጅግም የሚያስፈራ ነው፤
ማንስ ሊቋቋመው ይችላል?

“አሁንም ቢሆን፣
በጾም፣ በልቅሶና በሐዘን፣
በፍጹም ልባችሁ ወደ እኔ ተመለሱ” ይላል እግዚአብሔር።

ልባችሁን እንጂ፣
ልብሳችሁን አትቅደዱ፤
ወደ አምላካችሁ ወደ እግዚአብሔር ተመለሱ፤
እርሱ መሓሪና ርኅሩኅ፣
ቍጣው የዘገየና ፍቅሩ የበዛ፣
ክፉ ነገር ከማምጣትም የሚታገሥ ነውና።
በምሕረቱ ተመልሶ፣
ለአምላካችሁ ለእግዚአብሔር የሚሆነውን፣
የእህል ቍርባንና የመጠጥ ቍርባን እንዲተርፋችሁ፣
በረከቱን ይሰጣችሁ እንደ ሆነ ማን ያውቃል?

በጽዮን መለከትን ንፉ፤
ቅዱስ ጾምን ዐውጁ፤
የተቀደሰን ጉባኤ ጥሩ።
ሕዝቡን ሰብስቡ፤
ጉባኤውን ቀድሱ፤
ሽማግሌዎችን በአንድነት አቅርቡ፤
ሕፃናትን ሰብስቡ፤
ጡት የሚጠቡትንም አታስቀሩ፤
ሙሽራው እልፍኙን ይተው፣
ሙሽሪትም የጫጕላ ቤቷን ትተው።
በእግዚአብሔር ፊት የሚያገለግሉ ካህናት፣
በመሠዊያውና በቤተ መቅደሱ አደባባይ መካከል ሆነው ያልቅሱ፤
እንዲህም ይበሉ፤ “እግዚአብሔር ሆይ፤ ሕዝብህን አድን፤
ርስትህን በአሕዛብ መካከል መተረቻ፣
መሣቂያና መሣለቂያም አታድርግ፤
ለምንስ በሕዝቦች መካከል፣
‘አምላካቸው ወዴት ነው?’ ይበሉን።”

በጽዮን መለከትን ንፉ፤ በቅዱሱ ተራራዬም የማስጠንቀቂያውን ድምፅ አሰሙ። በምድሪቱ የሚኖሩ ሁሉ ይንቀጥቀጡ፤ የእግዚአብሔር ቀን ቀርቧልና፤ እርሱም በደጅ ነው። ይህም የጨለማና የጭጋግ ቀን፣ የደመናና የድቅድቅ ጨለማ ቀን ነው። የንጋት ብርሃን በተራሮች ላይ እንደሚወጣ፣ ኀያልና ብዙ ሰራዊት ይመጣል፤ ከጥንት እንዲህ ዐይነት ከቶ አልነበረም፤ በሚመጡትም ዘመናት እንዲህ ዐይነት ከቶ አይሆንም። በፊታቸው፣ እሳት ይባላል፤ በኋላቸውም ነበልባል ይለበልባል፤ በፊታቸው ምድሪቱ እንደ ዔድን ገነት ናት፤ በኋላቸውም የሚቀረው ባዶ ምድረ በዳ ነው፤ ምንም አያመልጣቸውም። መልካቸው እንደ ፈረስ መልክ ነው፤ እንደ ጦር ፈረስም ይጋልባሉ። ገለባ እንደሚበላ እንደሚንጣጣ እሳት፣ ለጦርነት እንደ ተዘጋጀ ኀያል ሰራዊት፣ የሠረገሎችን ድምፅ የሚመስል ድምፅ እያሰሙ፣ በተራሮች ጫፍ ላይ ይዘልላሉ። በእነርሱ ፊት ሕዝቦች ይርዳሉ፤ የሁሉም ፊት ይገረጣል። እንደ ተዋጊዎች ድንገት አደጋ ይጥላሉ፤ እንደ ወታደሮችም ቅጥርን ይዘልላሉ፤ ከመንገዳቸውም ሳይወጡ፣ አቅጣጫ ይዘው ይጓዛሉ። እርስ በርሳቸው አይገፋፉም፤ እያንዳንዱ መሥመሩን ጠብቆ ይሄዳል፤ መሥመራቸውን ሳይለቁ፣ መከላከያውን ሰብረው ያልፋሉ። ከተማዪቱን ይወርራሉ፤ በቅጥሩም ላይ ይዘልላሉ፤ በቤቶች ላይ ዘልለው ይወጣሉ፤ እንደ ሌባም በመስኮት ይገባሉ። ምድር በፊታቸው ትንቀጠቀጣለች፤ ሰማይም ይናወጣል፤ ፀሓይና ጨረቃ ይጨልማሉ፤ ከዋክብትም ከእንግዲህ ወዲያ አያበሩም። በሰራዊቱ ፊት፣ እግዚአብሔር ያንጐደጕዳል፤ የሰራዊቱ ብዛት ስፍር ቍጥር የለውም፤ ትእዛዙንም የሚያደርግ እርሱ ኀያል ነው፤ የእግዚአብሔር ቀን ታላቅ፣ እጅግም የሚያስፈራ ነው፤ ማንስ ሊቋቋመው ይችላል? “አሁንም ቢሆን፣ በጾም፣ በልቅሶና በሐዘን፣ በፍጹም ልባችሁ ወደ እኔ ተመለሱ” ይላል እግዚአብሔር። ልባችሁን እንጂ፣ ልብሳችሁን አትቅደዱ፤ ወደ አምላካችሁ ወደ እግዚአብሔር ተመለሱ፤ እርሱ መሓሪና ርኅሩኅ፣ ቍጣው የዘገየና ፍቅሩ የበዛ፣ ክፉ ነገር ከማምጣትም የሚታገሥ ነውና። በምሕረቱ ተመልሶ፣ ለአምላካችሁ ለእግዚአብሔር የሚሆነውን፣ የእህል ቍርባንና የመጠጥ ቍርባን እንዲተርፋችሁ፣ በረከቱን ይሰጣችሁ እንደ ሆነ ማን ያውቃል? በጽዮን መለከትን ንፉ፤ ቅዱስ ጾምን ዐውጁ፤ የተቀደሰን ጉባኤ ጥሩ። ሕዝቡን ሰብስቡ፤ ጉባኤውን ቀድሱ፤ ሽማግሌዎችን በአንድነት አቅርቡ፤ ሕፃናትን ሰብስቡ፤ ጡት የሚጠቡትንም አታስቀሩ፤ ሙሽራው እልፍኙን ይተው፣ ሙሽሪትም የጫጕላ ቤቷን ትተው። በእግዚአብሔር ፊት የሚያገለግሉ ካህናት፣ በመሠዊያውና በቤተ መቅደሱ አደባባይ መካከል ሆነው ያልቅሱ፤ እንዲህም ይበሉ፤ “እግዚአብሔር ሆይ፤ ሕዝብህን አድን፤ ርስትህን በአሕዛብ መካከል መተረቻ፣ መሣቂያና መሣለቂያም አታድርግ፤ ለምንስ በሕዝቦች መካከል፣ ‘አምላካቸው ወዴት ነው?’ ይበሉን።”

ኢዩኤል 2:1-17