የእግዚአብሔር ቃል ወደ እኔ መጣ፤ እንዲህም አለኝ፤
“በማሕፀን ሳልሠራህ ዐወቅሁህ፤
ከመወለድህ በፊት ለየሁህ፤
ለሕዝቦችም ነቢይ እንድትሆን ሾምሁህ።”
እኔም፣ “ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፤ እንዴት እንደምናገር አላውቅም፤ ገና ሕፃን ልጅ ነኝና” አልሁ።
እግዚአብሔር ግን እንዲህ አለኝ፤ “ ‘ገና ሕፃን ልጅ ነኝ’ አትበል፤ ወደምልክህ ሁሉ ሄደህ፣ ያዘዝሁህን ሁሉ ትናገራለህ፤ እኔ አድንህ ዘንድ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራቸው” ይላል እግዚአብሔር።