የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኢሳይያስ 55:6-13

ኢሳይያስ 55:6-13 - እግዚአብሔር በሚገኝበት ጊዜ ፈልጉት፤
ቀርቦም ሳለ ጥሩት።
ክፉ ሰው መንገዱን፣
በደለኛም ሐሳቡን ይተው።
ወደ እግዚአብሔር ይመለስ፤ እርሱም ምሕረት ያደርግለታል፤
ወደ አምላካችን ይመለስ፤ ይቅርታው ብዙ ነውና።

“ሐሳቤ እንደ ሐሳባችሁ፣
መንገዴ እንደ መንገዳችሁ አይደለምና”
ይላል እግዚአብሔር።

“ሰማያት ከምድር ከፍ እንደሚሉ፣
መንገዴ ከመንገዳችሁ፣
ሐሳቤም ከሐሳባችሁ እንዲሁ ከፍ ያለ ነው።
ዝናምና በረዶ ከሰማይ ወርዶ፣
ምድርን በማራስ፣
እንድታበቅልና እንድታፈራ
ለዘሪው ዘር፣
ለበላተኛም እንጀራ እንድትሰጥ ሳያደርግ፣
ወደ ላይ እንደማይመለስ ሁሉ፣
ከአፌ የሚወጣውም ቃሌ፣
በከንቱ ወደ እኔ አይመለስም፤
ነገር ግን የምሻውን ያከናውናል፤
የተላከበትንም ዐላማ ይፈጽማል።
በደስታ ትወጣላችሁ፤
በሰላምም ትሸኛላችሁ፤
ተራሮችና ኰረብቶች፣
በፊታችሁ በእልልታ ይዘምራሉ፤
የሜዳ ዛፎች ሁሉ፣
ያጨበጭባሉ።
በእሾኽ ፈንታ የጥድ ዛፍ፣
በኵርንችት ፈንታ ባርሰነት ይበቅላል።
ይህም የእግዚአብሔር መታሰቢያ፣
ሊጠፋ የማይችል፣
የዘላለም ምልክት ይሆናል።”

እግዚአብሔር በሚገኝበት ጊዜ ፈልጉት፤ ቀርቦም ሳለ ጥሩት። ክፉ ሰው መንገዱን፣ በደለኛም ሐሳቡን ይተው። ወደ እግዚአብሔር ይመለስ፤ እርሱም ምሕረት ያደርግለታል፤ ወደ አምላካችን ይመለስ፤ ይቅርታው ብዙ ነውና። “ሐሳቤ እንደ ሐሳባችሁ፣ መንገዴ እንደ መንገዳችሁ አይደለምና” ይላል እግዚአብሔር። “ሰማያት ከምድር ከፍ እንደሚሉ፣ መንገዴ ከመንገዳችሁ፣ ሐሳቤም ከሐሳባችሁ እንዲሁ ከፍ ያለ ነው። ዝናምና በረዶ ከሰማይ ወርዶ፣ ምድርን በማራስ፣ እንድታበቅልና እንድታፈራ ለዘሪው ዘር፣ ለበላተኛም እንጀራ እንድትሰጥ ሳያደርግ፣ ወደ ላይ እንደማይመለስ ሁሉ፣ ከአፌ የሚወጣውም ቃሌ፣ በከንቱ ወደ እኔ አይመለስም፤ ነገር ግን የምሻውን ያከናውናል፤ የተላከበትንም ዐላማ ይፈጽማል። በደስታ ትወጣላችሁ፤ በሰላምም ትሸኛላችሁ፤ ተራሮችና ኰረብቶች፣ በፊታችሁ በእልልታ ይዘምራሉ፤ የሜዳ ዛፎች ሁሉ፣ ያጨበጭባሉ። በእሾኽ ፈንታ የጥድ ዛፍ፣ በኵርንችት ፈንታ ባርሰነት ይበቅላል። ይህም የእግዚአብሔር መታሰቢያ፣ ሊጠፋ የማይችል፣ የዘላለም ምልክት ይሆናል።”

ኢሳይያስ 55:6-13