በዚህም ተራራ ላይ፣
በሕዝብ ሁሉ ላይ የተጣለውን መጋረጃ፣
በመንግሥታት ላይ የተዘረጋውን መሸፈኛ ያጠፋል፤
ሞትንም ለዘላለም ይውጣል።
ጌታ እግዚአብሔር
ከፊት ሁሉ እንባን ያብሳል፤
የሕዝቡንም ውርደት
ከምድር ሁሉ ያስወግዳል፤
እግዚአብሔር ተናግሯልና።
በዚያን ቀን እንዲህ ይባላል፤
“እነሆ፤ አምላካችን ይህ ነው፤
በእርሱ ታመንን፤ እርሱም አዳነን፤
እግዚአብሔር ይህ ነው፤ በእርሱ ታመንን፤
በማዳኑም ደስ ይበለን፤ ሐሤትም እናድርግ።”