የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ዘረኝነትና የእኛ ምላሽናሙና

ዘረኝነትና የእኛ ምላሽ

ቀን {{ቀን}} ከ4

ሁሉምነገርበጣምከልክ ሲያልፍስ?

ዘረኝነትና መድልዎ ዜናውን ተፅዕኖ ካደረጉና ህብረተሰቡን ከተቆጣጠሩ ሁሉም ሊቋቋመው የማይችለው ስሜት ሊሰማው ይችላል፡፡ እኛ አስተውለንም ይሁን ሳናስተውል መፍታት እንደማንችለው የሚሰማንን ችግር በመግታት ራሳችንን እንከላከላለን፣ በዚህም ለአንዳንድ ሰዎች የዕለት ተዕለት እውነታ ለሆነው ለስሜት መቃወስ ምክንያት እንሆናለን። ከሌሎች ዘንድ በሚመጣ ስቃይ ስንፈተን እንዴት ምላሽ እንሰጥ ዘንድ እንደሚጠራን ወደ ኢየሱስ እንቅረብ፡፡

በደጉ ሳምራዊ ምሳሌ ውስጥ ካህኑና ሌዋዊው ሁለቱም ሀይማኖታዊ ስርዓቶችን ለመፈፀም የሚተጉ እንደሆኑ ተነግሮን ያንን በመንገድ ወድቆ የነበረውን አይሁዳዊ ሲመለከቱ ግን አገለሉት፡፡ ምናልባት አንተም በግልፅ፤ ሆን ብለህ ምቾት የማይሰጥህን ሰው ፊት ነስተህ ወደ ሌላኛው መንገድ አቋርጠህ የሄድክባቸው ጊዜያት አሉ፡፡ ማናችንም የምናይ ግን የማንመለከት እንዲሁም የምንሰማ ነገር ግን የማናዳምጥ ዓይነት ክህደት ውስጥ አምኖ ከመኖር ውጪ ምንም ምርጫ የለንም፡፡

የዚህች ዓለም ፍላጎቶች ልክ የላቸውም፡፡ ተግዳሮቶቹ በየጊዜው እያደጉ ስለሆነ ምናልባት አንተ ምንም የምሰጠው ነገር የለኝም ብለህ ይሰማህ ይሆናል ወይም ደግሞ ከየት መጀመር እንዳለብህም አታውቅ ይሆናል፡፡ ምናልባት የመጀመሪያ ርምጃ ማድረግ የሚገባህ የልብህ መደንደን እንዴት እንደጨመረ ወይም በማህበረሰብህ ውስጥ ችግርን ስታይ ቸልተኛ እየሆንክ ስለመሆንህ ማመን ነው፡፡ በመቀጠል ማስታወስ የሚገባን ደግሞ ምንም እንኳን በፍትሃዊነት ማጣት ዙሪያ የሚያጋጥሙን ተግዳሮቶች በጣም ብዙ ቢሆኑም፣ ኢየሱስ ባልንጀሮቻችንን እንደ ራሳችን እንድንወድ እንዳዘዘንና ያንንም እንዴት መፈፀም እንደምንችል ደጉ ሳምራዊን እንደ ምሳሌ ያቀርባል። ሳምራዊው በርህራሄ ተሞልቶ ቆመ፤ ለተደበደበውም ሰው ራራለት፡፡ ምናልባት ከመሮጥ ቆም ብለን በብዙ ህመም ላሉት በርህራሄ የምንዘረጋላቸው ጊዜው አሁን ሊሆን ይችላል፡፡ እስቲ ምንም ዓይነት ቅድመ ግምት ወይም ፍርድ ሳንሰጥ በመከራ ውስጥ ላሉት ሰዎች ቆም እንበልላቸውና መከራቸውን እንካፈል፡፡ በተጨባጭ፣ይህማለትበቀንመርሐግብርዎውስጥሰፋያሉህዳጎችንመሳልማለትሊሆንይችላል፣ስለዚህትንሽበዝግታመሄድይችላሉ፣እናለማየት፣ለማቆምእናለመግባትጊዜይስጡ። ይህ ማለት በተግባር ስናየው የቀን የውሎ ዕቅድህን ሰፋ አድርገህ መወጠን ሲሆን ይህ ደግሞ ቀስ በቀስ በመዘርጋት ለማየት፣ ለመቆም እን ለመግባት ያስችላል፡፡

በወንጌላት ሁሉ ኢየሱስ ሁልጊዜ በብዙ ርህራሄ የምስራቹን ሲሰብክ እና የታመሙትን ሲፈውስ እናነባለን፡፡ በየዕለት ጉዞህ ኢየሱስ ከአንተ ጋር ነው፡፡ በዓይነ-ህሊናህ ኢየሱስ አንተ ከምታወራቸው ልዩ ልዩ ሰዎች ጋር ሊያወራ የሚችለውን፣ አብረህ የምትቀመጣቸውን ሰዎች ወይም የምታልፋቸውን ሰዎች እንዴት እንደሚገናኝ አስብ፡፡ ርህራሄ ተግባርን ይወልዳል፡፡ ርኁሩኅ ልብ የእግዚአብሔርን ልብ ያንፀባርቃል፤ ስለዚህም ሁሉጊዜ ልባቸው ወደ ተሰበሩ በማቅናት ልባቸውን ይፈውሳል፡፡ የደጉንሳምራዊምሳሌመከተልከባድናቅዱስሥራነው ሆኖም ግንየሚያመጣውተሃድሶናደስታትልቅ ዋጋ አለው፡፡

በአሁናዊ ሁኔታህ የዘር መድሎን ስትመለከት በፍላጎት ስበት ላትሽመደመድ ትችላለህ፡፡ ይልቅ እግዚአብሔር ልብህን አለዝቦ ጥበብን፣ ብርታትንና እርሱን ለመከተል የሚመራህን ርኅራሄና የእርሱን ፍቅር ይስጥህ፡፡ ትንሹ የበጎነት ተግባር የሚያስገርም ታላቅ መሆኑን እንዲሁም ደጉ ሳምራዊ መሆን ለአንተም እንደሚቻል አስተውል፡፡

ቅዱሳት መጻሕፍት

ቀን 2ቀን 4

ስለዚህ እቅድ

ዘረኝነትና የእኛ ምላሽ

እንደ ክርስቲያን በዙሪያችን ባለው ዓለም ያለውን የዘረኝነት ውጤትና የእኛን ምላሽ መመልከት እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡ ይህ ጊዜውን የጠበቀ እጅግ አስደሳች የአራት ቀናት ዕቅድ የዘረኝነትን ስር እንዲሁም በዚህ ዓለም በእግዚአብሔር የመዋጀትና የተሃድሶ ስራ ውስጥ እንድንጫወት የተጠራንበትን ጉዳይ ይዳስሳል፡፡ ይህ ዕቀድ የተዘጋጀው በዩቨርዥን ነው፡፡

More

ይህንን እቅድ ስላቀረበልን Sidhara Udalagama ን ልናመሰግን እንወዳለን። ለበለጠ መረጃ፣እባክዎ የሚከተለውን ይጎብኙ፡ https://www.linkedin.com/in/sidhara-udalagama-b89b32210/?originalSubdomain=au