ዘረኝነትና የእኛ ምላሽናሙና
ዘረኝነት፤ የማን ችግር ነው?
በመንገድህ ላይ የሚኖሩትን የሁሉንም ስም ታውቃለህ? ጎሮቤታችንን ወይም በመንገዳችን ላይ የሚኖሩትን ሰዎች ለመውደድ ንቁዎች መሆን ከእኛ ይጠበቃል፡፡ ኢየሱስ “ባልንጀራ” የሚለውን ግልፅ ሲያደርግ ከመንደርና ከህንፃ መጋራት እንዲሁም ፈገግ ብሎና በእጅ ሰላምታ ከመለዋወጥ በእጅጉ የሚበልጥ ጉዳይ መሆኑን ያሳያል፡፡
የዘረኝነት ስሩ እኛን ባልመሰሉ ሰዎች ላይ የእግዚአብሔርን መልክ ማየት ሲሳነን የሚመጣ ነው፡፡ ምናልባት ይህ ከእኔ ጋር ምን ግንኙነት አለው ብለህ አስበህ ይሆናል፤ ሰዎች ኢየሱስን ስለ ታላቂቱ ትዕዛዝ ሲጠይቁት የመለሰላቸው በሁለት ትዕዛዛት ጠቅልሎ፤እግዚአብሔርንና ባልንጀራህን ውደድ በሚል ነበር፡፡ እኚህ ትዕዛዛት በእጅጉ የተያያዙ ናቸው፡፡ ሰዎችን ሳንወድ እግዚአብሔርን ልንወድ አንችልም፡፡ አንደ ሰው ኢየሱስን “ባልንጀራዬ ማን?” ብሎ በጠየቀው ጊዜ የመለሰለት የደጉ ሳምራዊዉን ታሪክ በማንሳት ነው፡፡ ይህ ታሪክ አይሁዳውያን የሆኑ የኢየሱስ ታዳሚዎችን ያስደነገጠ ነበር፤ ምክንያቱም በአይሁዳውያንና በሳምራውያን መካከል የቆየ ጠላትነት ነበርና፡፡ ምናልባት ከሌላ ዘር፣ ባህል፣ ወይም ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ አጥር ውጪ ካለ ሰው ጋር በግድ መቀራረብ ግራ ያጋባህ ይሆናል፡፡ ምናልባትም በታረክ ደረጃ ስለ ዘር ጥላቻም ጠንቅቀህ ታውቅ ይሆናል፡፡ ምናልባትም አስበህበትም ይሁን ባለማወቅ ልታስወግዳቸው የምትፈልጋቸው ሰዎች አሉ፡፡ እግዘአብሔር ግን ስለ ምላሽህ ምን እያለህ ይሆን? ቀጣዩ ርምጃህስ ምንድን ነው?
በኢየሱስ ምሳሌ መሰረት ከሁሉ ያነሰ ባልንጀራ ተደርጎ የሚቆጠረው ሰው ከሁሉ ይልቅ ትኩረት የሚሰጠው ነው፡፡ ኢየሱስ ትኩረት ሊያደርግ የፈለገው በእግዚአብሔር መንግስት ውስጥ ምንም ዓይነት ዘረኝነት፣ የብሔር ወይም የባህል ልዩነቶች አለመኖራቸውን ነው፡፡ የቆሰለው አይሁዳዊው በመንገድ ወድቆ በነበረ ጊዜ ሳምራዊው የአከባቢው ሰው አልነበረም፡፡ በፍፁም አያውቀውም ነበር ወይም ጎረቤቱም አልነበረም፡፡ ሳምራዊው ባልንጀራነት ድንበርን የሚሻገር መሆኑን አስመስክሯል፡፡
ከምንወዳቸው፣ ከቢጤዎቻችን ወይም ደግሞ ከምናውቃቸው ጋር ጥሩ ባልንጀራ መሆን ቀላል ነው፡፡ ነገር ግን በኢየሱስ ትርጉም ለባልንጀርነት መመሳሰል፣ ቤተሰባዊነት እና መዋደድ ምክንያቶች አይደሉም፡፡
በቤተ ክርስቲያን ባሉ ማህበረሰብ ውስጥም እግዚአብሔርንና ሌሎችን እንወድ ዘንድ የኢየሱስ ምሳሌነት ትዕዛዝ ተሰጥቶናል፡፡ ጳውሎስ ለቆሮንጦስ አማኞች የክርስቶስ አካል የሆነችው ዓለም ዓቀፏ ቤተ-ክርስቲያን የተፈጠረችበትን ምክንያት ሲያብራራ፤ በአካሉ ምን ዓይነት ክፍፍል ፈፅሞ ሊኖር እንዳልተገባው ነገር ግን እያንዳንዱ ብልት አንዱ ለሌላው ግድ ሊሰኝ እንደሚገባው ነው፡፡ አንዱ ብልት ሲሰቃይ ብልቶች ሁሉ አብረው እንደሚሰቃዩ፤ አንዱም ብልት ሲከብር ሌላውም አብሮ ይደሰታል፡፡ አንተ ባለህበት ማህበረሰብ ውስጥ ወይም በዙሪያህ ባሉ ጓደኞችህ መካከል “ዘረኝነት የእኔም ችግር ነው” ብለው ቢሉህ ምን ሊለወጥ እንደሚችል አስብ፡፡
ተግዳሮቶችን አልፎ ከእኛ የሚለዩትን ሰዎች መውደድ እንደሚቻል ራሱ ኢየሱስ ምሳሌ ሆኖልናል፡፡ ሰማይን ትቶ ከቀራጮ ጋር ሲመገብ፣ ከአሳ አጥማጆች ጋር ሲወዳጅ፣ ለለምፃሞች ሲናገርና ለኃጢአተኞች ፀጋውን ሲገልጥ አይተናል፡፡ ዘረኝነት የእኛም ችግር ስለሆነ የኢየሱስ ትእዛዛት የሆነውን በማክበር ይኸውም እግዚአብሔርንና ሰዎችን በመውደድ ልንፈታው የምንችለው ችግር መሆኑን ለማስተዋል በእውነት ማሰላሰል ውስጥ ለመስጠም ጊዜ ውሰድ። በጸጋ፣ በፍቅርና በአክብሮት በሁሉም አይነት ጎረቤቶች ህይወት ለመገለጥ እያንዳንዱን እድል እንጠቀም።
ስለዚህ እቅድ
እንደ ክርስቲያን በዙሪያችን ባለው ዓለም ያለውን የዘረኝነት ውጤትና የእኛን ምላሽ መመልከት እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡ ይህ ጊዜውን የጠበቀ እጅግ አስደሳች የአራት ቀናት ዕቅድ የዘረኝነትን ስር እንዲሁም በዚህ ዓለም በእግዚአብሔር የመዋጀትና የተሃድሶ ስራ ውስጥ እንድንጫወት የተጠራንበትን ጉዳይ ይዳስሳል፡፡ ይህ ዕቀድ የተዘጋጀው በዩቨርዥን ነው፡፡
More
ይህንን እቅድ ስላቀረበልን Sidhara Udalagama ን ልናመሰግን እንወዳለን። ለበለጠ መረጃ፣እባክዎ የሚከተለውን ይጎብኙ፡ https://www.linkedin.com/in/sidhara-udalagama-b89b32210/?originalSubdomain=au