ክርስቶስ የእኛ አሸናፊናሙና
ማቅረብ
በመዝሙረ ዳዊት 68:15–18መዝሙረኛው ህዝቡን በደህና ወደ እግዚአብሔር ተራራ በሚያደርሰው በእግዚአብሔር ኃይል ሲደሰት እናያለን፡፡ እንደ ክርስቲያን በወንጌል ውስጥ አንተና እኔ ወደ ዘላለማዊ ቤታችን በደህና የሚያደርሰን የፀና ተስፋ ተሰጥቶናል፡፡
በምዕራፉ ያለው ቁጥር 18 የሚያመለክተው ወደ ላይ ስላረገው ምርኮኞችንም በባቡሩ ከፊት እየመራ ስላለው ነው፡፡ ሐዋሪያው ጳውሎስ በኤፌሶን 4፡8 ላይ እየነገረን ያለው መዝሙረ ዳዊት 68:18 ስለ ክርስቶስ ኢየሱስና ከሞት በመነሳቱ የፈፀመውን የእርሱ መለኮታዊ ድል ይገልፃል እያለን ነው፡፡
ዕብራውያን 12:2የሚመክረን የእምነታችንን ራስና ፍፁም አድራጊ ኢየሱስ ላይ ዓይናችንን እንድናደርግ ነው፡፡ ራስና ፍፁም አድራጊ የሚለውን የግሪኩ ትርጉም በሚገርም ሁኔታ አሸናፊ ወይም ድል አድራጊ ይለዋል፡፡ በሌላ አገላለፅ ኢየሱስ ስለ እኛ ሀጢአትና ሞት በመስቀሉ ጦር ሜዳ ላይ ፍፁም ድል ተቀዳጅቷል፡፡ በሌላ አባባል ደግሞ ክርስቶስ መለኮታዊ አሸናፊያችን ነው!
በዚያ የወንጌል እውነት ምክንያት 1ኛ ቆሮንጦስ 6:14 የሚያስረግጥልን ያው ክርስቶስን ያስነሳው ኃይል ዛሬም በህይወታችን ያለውን ኃጢአት ሊያሸንፈው እንደሚችል አውቀን ማረፍ፤ እንዲሁም አንድ ቀን ደግሞ እንደሚያስነሳንና በእግዚአብሔር አብ ዘላለማዊ መገኘት ፊት እንደሚያቀርበን ነው፡፡
ክርስቲያኖች በዚህ ህይወት በምንም ሁኔታ ምንም ቢገጥመን የፀና የወንጌል ዋስትና አለን፤ ይኸውም አግዚአብሔር አንድ ቀን ወደ ዘላለማዊ ቤት ወደ እርሱ በደህና ያደርሰናል፡፡
ቅዱሳት መጻሕፍት
ስለዚህ እቅድ
በአሸናፊው በክርስቶስ በኩል እግዚአብሔር ለዘለዓለም ከሀጢአትና ከሞት ነፃ አውጥቶ ጠብቆናል፤ አሁንም በዚህ በወደቀ ዓለም ይጠብቀናል፤ አንድ ቀንም ወደ ራሱ በደህና ያደርሰናል፡፡
More
ይህንን እቅድ ስላቀረበልን Returning to the Gospel - East Africa ን ልናመሰግን እንወዳለን። ለበለጠ መረጃ፣እባክዎ የሚከተለውን ይጎብኙ፡ https://returningtothegospel.com/