ክርስቶስ የእኛ አሸናፊናሙና
መጠበቅ
መዝሙረ ዳዊት 68:11–14 በድጋሜ በጠላቶቻቸው መሀል የነበሩትን የብሉይ ኪዳን ህዝብ የእግዚአብሔር ኃይል እንዴት እንደጠበቃቸው በግጥሙ ይዘረዝራል፡፡ አንተና እኔም ዛሬ ላይ እንዳለ ክርስቲያን በዚህች በወደቀች ዓለም በኩል ወደ ዘላለም በምናደርገው የከበረ ጉዞ በየቀኑ በመንፈስ የምንጠበቅ የአዲስ ኪዳን ሰዎች ነን፡፡
ሶስቱ በክርስትና ጉዞአችን የሚገጥሙን አደገኛ ጠላቶቻችን ስጋ፣ ዓለም እና ሰይጣን ናቸው፡፡ እኚህ ጠላቶች ሀጢአት እንድንሰራ፣ ለእግዚአብሔር እንዳንታዘዝ እና በዚህች በተጣለች ዓለም ልንቀይራቸው በማንችላቸው በሚገጥሙን ተግዳሮቶች ተስፋ እንድንቆርጥ አድፍጠው ይፈታተኑናል፡፡
በዮሐንስ ወንጌል 16:33 ከመስቀል ጉዞው ዋዜማ ኢየሱስ ለወዳጆቹ እርሱ ዓለምን እንዳሸነፈ አረጋግጧል፡፡ እዚህ ጋር በመስቀል ላይ የነበረው የእርሱ ስራ ዓለምን ያሸነፈበት ወሳኝ ድል መሆኑን እያወጀ ነው፡፡
በሉቃስ22:42 በጌቴሴማኔ የአትክልት ስፍራ፤ ኢየሱስ በከፍተኛ ጣር ውስጥ ሆኖ የእርሱ ሳይሆን የአባቱ ፈቃድ እንዲፈፀም ፀለየ፡፡ ኢየሱስ በመስቀል ላይ የነበረው የእርሱ ስራ ስጋን ያሸነፈበት ወሳኝ ድል መሆኑን እያወጀ ነው፡፡
በመጨረሻም በዮሐንስ 12:31 አሁንም ከመስቀል ጉዞው ዋዜማ ላይ ኢየሱስ የዚህን ዓለም ልዑል ሰይጣንን እንደሚያባርረው ተስፋ ገብቷል፡፡ በመስቀል ላይ የነበረው የእርሱ ስራ ሰይጣንንም ያሸነፈበት ወሳኝ ድል መሆኑን እያወጀ ነው፡፡
ስለዚህ እነዚህን አዋጆች በማድረግ በመስቀል ላይ የነበረው የእርሱ ስራ ዓለምን፣ ስጋንና ሰይጣንን ያሸነፈበት ወሳኝ ድል መሆኑን ኢየሱስ እያሳወቀን ነው፡፡ ወንጌልን በእምነት በህይወታችን የግላችን ስናደርገው እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ በእያንዳንዳችን የክርስትና ህይወት ዓለምን፣ ስጋንና ራሱ ሰይጣንን ለማሸነፍ የክርስቶስን የድል ህይወት እንድንለማመድ ኃይል ሊሰጠን በውስጣችን ይኖራል፡፡ ያ ማለት ሁልጊዜ የኃጢአት ፈተናዎችንን በድል እንቋቋማለን፤ በማንኛውም ጊዜ በዙሪያችን ያሉትን አምላክ የለሽ ዓለም እሴቶችን እንቃወማለን፤ እንዲሁም ሁሉጊዜ በሀሰቱ እግዚአብሔርን እንዳንታመን የሚጥረውን የሰይጣንን ውሸት እንቃወማለን፤ በዓለም ላይ፣ በስጋ ላይ እና በሰይጣንም ላይ የክርስቶስን ድል በኃይል እንለማመዳለን ማለት ነው፡፡
በዚህች በወደቀች ዓለም በኩል በምናደርገው የክርስትና ጉዞአችን እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ጠላቶቻችን በሆኑት በስጋ ላይ፣ በዓለም ላይ እና በሰይጣን ላይ የክርስቶስን የድል ህይወት እንድንለማመድ ኃይል እየሰጠን ይጠብቀናል፡፡
ቅዱሳት መጻሕፍት
ስለዚህ እቅድ
በአሸናፊው በክርስቶስ በኩል እግዚአብሔር ለዘለዓለም ከሀጢአትና ከሞት ነፃ አውጥቶ ጠብቆናል፤ አሁንም በዚህ በወደቀ ዓለም ይጠብቀናል፤ አንድ ቀንም ወደ ራሱ በደህና ያደርሰናል፡፡
More
ይህንን እቅድ ስላቀረበልን Returning to the Gospel - East Africa ን ልናመሰግን እንወዳለን። ለበለጠ መረጃ፣እባክዎ የሚከተለውን ይጎብኙ፡ https://returningtothegospel.com/