የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ክርስቶስ የእኛ አሸናፊናሙና

ክርስቶስ የእኛ አሸናፊ

ቀን {{ቀን}} ከ5

መታደግ

መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ 68 ህዝቡን ለማዳን የተገለጠውን የእግዚአብሔርን ኃይል የሚያከብር የምስጋና ዝማሬ ነው፡፡ በመዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ 68፡7-10 መዝሙረኛው በግጥሙ በብሉይ ኪዳን እግዚአብሔር ህዝቡን ከግብፅ ቀንበር ነፃ ያወጣበትን ኃይሉን ይገልፃል፡፡ ይህንን ንፅፅር በዛሬው የክርስትና ኑሮአችን በአዲስ ኪዳን ውስጥ በብዙ ቦታ እንመለከታለን፡፡ ለምሳሌ ኤፌሶን ምዕራፍ 2፡1-5 የሚያሳስበን በአዲስ ኪዳን ያሉ የእግዚአብሔር ህዝብ ማለትም እንደ አንተና እንደ እኔ ያሉ ክርስቲያኖች ከሀጢአትና ከመንፈሳዊ ሞት ቀንበር ነፃ መውጣታችንን ነው፡፡

በእምነታችን ክርስቶስ በመስቀል ላይ የሰራልንን የወንጌልን እውነት ስንቀበል ለሀጢአታችን የእግዚአብሔርን ይቅርታ እንቀበላለን፤ መንፈስ ቅዱስም በእኛ ዘንድ ሊኖር ይመጣል፡፡ ይህ ሲሆን ከሀጢአት ፍርድ ነፃ እንሆናለን፤ በየቀኑም ከሀጢአት ኃይል ነፃ እንሆናለን፤ እንዲሁም አንድ ቀን በአዲሲቷ ዓለም የእግዚአብሔርን የዘለዓለም መንግስት ሊመሰርት ሲመለስ ያኔ ሀጢአት ከሚገኝበት ፈፅመን ነፃ እንሆናለን፡፡

መንፈስ ቅዱስ በውስጣችን ሲኖር ኃይል ይሰጠናል፣ ይመራናል፣ እግዚአብሔርን የሚያስደስት ኑሮ ለመኖር አቅጣጫ ያሳየናል፡፡ እንደ ክርስቲያን ሀጢአት ልንሰራ አንችልም ማለት አይደለም፤ ልንሰራ እንችላለን ግን በቀላሉ ግን ማድረግ አንፈልግም፡፡ በክርስቲያንና ክርስቲያን ባልሆኑት መካከል ያለው ልዩነት ክርስቲያን ሀጢአት የማያውቅ ፍፁም ነው ማለት ሳይሆን ክርስቲያን ሀጢአት ሲሰራ ግን በጣም ይፀፀታል፡፡

በ1ኛዮሐንስ 1፡8-10 ሐዋሪያው ዮሐንስ የሚያሳስበን ነገር ክርስቶስ ስለ ሰራናቸው ወይም ወደፊት ስለምንፈፅመውም ማንኛውም ሀጢአት ሞቷል፤ ሀጢአት እንዳደረግን ወይም ደግሞ እንደወደቅን መንፈስ ቅዱስ ሲወቅሰን ሀጢአታችንን መናዘዝ እና በእምነት በክርስቶስ የእኛ የሆነውን ይቅርታ መቀበል አለብን፡፡

በመዝሙረ ዳዊት 68 እግዚአብሔር እኛን የሚጠብቀን ከሀጢአትና ከመንፈሳዊ ሞት በእርሱ ነፃ አውጪነት መሆኑን የወንጌሉ አውነት ያስረዳናል፡፡ ፡፡

ቀን 1ቀን 3

ስለዚህ እቅድ

ክርስቶስ የእኛ አሸናፊ

በአሸናፊው በክርስቶስ በኩል እግዚአብሔር ለዘለዓለም ከሀጢአትና ከሞት ነፃ አውጥቶ ጠብቆናል፤ አሁንም በዚህ በወደቀ ዓለም ይጠብቀናል፤ አንድ ቀንም ወደ ራሱ በደህና ያደርሰናል፡፡

More

ይህንን እቅድ ስላቀረበልን Returning to the Gospel - East Africa ን ልናመሰግን እንወዳለን። ለበለጠ መረጃ፣እባክዎ የሚከተለውን ይጎብኙ፡ https://returningtothegospel.com/