በእግዚአብሔር ዓላማዎች መጓዝናሙና
ዝግጅት መገለጥን ይወልዳል
እንደ አባት የሁለት ዓመት ህፃን ልጄ እንደ ኒላ ያሉ ነገሮችን እንደትይዝ አልፈቅድላትም ምክንያቱም ለዛ ዝግጁ ስላልሆነች፡፡ ደህንነቷን እጠብቃለሁ ስለዚህም በአሻንጉሊት እንድትጫወት እመርጣለሁ፡፡ እግዚአብሔር አባታችን እንደመሆኑ ልንይዘው ብቁ ካልሆንበት ነገሮች ይጠብቀናል፡፡ እግዚአብሔር እንደሚያቀርበው ስለምናውቀው ዋጋ ያለውን ወይም ጠቃሚ ነገር ልንለምን እንችላለን፣ ነገር ግን በረከቶቹን ለመቀበል ሙሉ በሙሉ እስክንበቃ ድረስ ያዝ ሊያደርግብን ይችላል። እኛ ከተዓምራቱ ኋላ ልንሆን እንችላለን፤ እግዚአብሔር ግን ከዝግጅታችን ጀርባ ነው፡፡
ይህ የዝግጅት መርህ በዳዊት ህይወት ላይ በግልፅ ይታያል፡፡ ዳዊት ግዙፉንና ፅኑ ጦረኛ የነበረውን ጎልያድን አሸንፏል ምክንያቱም የአባቱን በግ በመጠበቅ ሳለ፤ ማንም በማያየው ጊዜ በአንበሳና በድብ ላይ እየተለማመደ ነበር፡፡
ሁላችንም በውስጣችን ያለው ተስጥኦና ዓላማ በፍጥነት እንዲታይልን እንሻለን፤ ነገር ግን መዘጋጀትን ያስከፍለናል፡፡ በአብዛኛው ዝግጅት የሚደረገው በስውር ቦታ፣ እኛን ማንም ሊያየንና ስኬታችንን ማንም በማያስተውለው ሁኔታ ነው፡፡ ማንም ግን ባያይህ እግዚአብሔር ያይሃል፡፡ እጅህን ሰልፍ ያስተምራል፡፡ ለምትሰራቸው ታላላቅ ስራዎች ማንም ሰው ባያደንቅህ በፍፁም አትዘን፡፡ እግዚአብሔር ዝግጅቱን በአንተ ላይ እስኪያጠናቅቅ ድረስ በፍፁም በችኮላ በሰዎች ለመታየት አትሞክር፡፡
ጌታ ዳዊትን የአባቱን በጎች እንዲያግድ በማድረግ እያዘጋጀው ነበር፡፡ በዚህም ምክንያት የእስራኤልን በጎች ለመጠበቅ እግዚአብሔር ታማኝ አድርጎ ቆጠረው፡፡ በጥቂቱ ታምኖ ነበርና በብዙ ለመታመን ዝግጁ ነበር፡፡
ብዙ ሰዎች ለመገለጫቸው እና ጥሰው ለመሄዳቸው ምቹ መድረክ ሊሆኑ ከሚችሉት ፈቀቅ ይላሉ፣ ምክንያቱም ዓይኖቻቸው በትላልቅ ግቦች ወይም እድሎች ላይ ያተኮሩ ስለሆነ ጉልህ በሮች ሊከፍቱ የሚችሉትን ትናንሽ ሀላፊነቶችን ቸል ይላሉ። እነዚያ ትንንሽ የቤት ስራዎች በዓላማህ ውስጥ ያሉ ዓለምን እንድታይ የሚያበቃህ ዝግጅት ነው፡፡ ዳዊት የአባቱን በግ ቢንቅና ቸል ቢል ኖሮ ዕድሉን ባገኘ ወቅት ለሳኦል የሚያቀርበውና የሚናገረው ማስረጃ አይኖርም ነበር ምክንያቱም በእነዚያ ትንንሽ የቤት ስራዎች በነበረው ድልና ታማኝነት ነበር ሳኦል ለትልቅ ኀላፊነት እንዲሸከም ታማኝ አድርጎ የቆጠረው፡፡
ሰዎች በተለይም በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ ከስራና ከኃላፊነት የሚሸሹበት ብዙ ምክንያቶች አሉ፡፡ አንዳንዶች ትኩረት እንዳጡ ይሰማቸዋል፤ አንዳንዶች ጊዜያቸውን እያጠፉ እንዳሉ ይሰማቸዋል፤ አንዳንዶች በቤተክርስቲያን ውስጥ ማገልገል እምብዛም አትራፊ እንዳልሆነ ይሰማቸዋል፡፡ እነሱ የማያውቁት ነገር ቢኖር ማንም ሳያይህ ወይም ሳያሞግስህ ሁሉንም ነገርህን ስትሰጥ ለወደፊት መገለጥህ እያመቻቸህ ነው።
ስለዚህ በእልፍኝህ ተጠመድ፡፡ ዕውቅናን፣ ዝናንና ገንዘብን በፍፁም አትሻ፡፡ ዋጋንና ዓላማን ተከተል፡፡ ከእግዚአብሔር አንዳች ለመቀበል ስትል አታገልግል ይልቅ ሁለንተናህን ልትሰጠው አገልግል፡፡ በስውር የምታደርገውን የሚያይ እግዚአብሔርም በአደባባይ ይከፍልሃልና፡፡
ቅዱሳት መጻሕፍት
ስለዚህ እቅድ
ልክ ከኤርሚያስና ከዳዊት ህይወት እንደምትመለከተው ሁሉ ዓላማህን ለመኖር፣ እግዚአብሔርን ባለህ ነገርና ባለህበት ቦታ ለማገልገል ታናሽ አይደለህም፡፡ ለዓላማህ መዘጋጀት ማለት ምን ማለት እንደሆነ እና ዓላማህን ሊያጠፉት ከሚያደፍጡ መጠበቅን ተማር፤ እንዲሁም ለአንድ ነገር ተዘጋጅ ይኽውም ትርጉም ያለውን ህይወት እና ዓለምን ሊባርክ የሚችለውን እግዚአብሔርን የሚያከብረውን ህይወት ለመኖር፡፡
More
ይህንን እቅድ ስላቀረበልን Mount Zion Faith Ministry ን ልናመሰግን እንወዳለን። ለበለጠ መረጃ፣እባክዎ የሚከተለውን ይጎብኙ፡ https://mountzionfilm.org/