የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

በእግዚአብሔር ዓላማዎች መጓዝናሙና

በእግዚአብሔር ዓላማዎች መጓዝ

ቀን {{ቀን}} ከ6

የማን ዓላማ?

እንደ አንድ ወጣት በሀገሬ ላይ የተወጣለት ሲኒማቶግራፈር የመሆን ህልም ነበረኝ፡፡ ከህልሜ ጋር እንድገናኝ ያለማቋረጥ መፅሐፍቶችን አነብና የተለያዩ አጋዥ ትምህርቶችን እመለከት ነበር፡፡ ከእግዚአብሔር ጋር ያለኝ ግንኙነት እየጠነከረ ሲሄድ፣ የእኔ ቅዠት ተጨባጭ እንዳልሆነና ምንም ነገር እንዳልሰበሰብኩ ተገነዘብኩ ምክንያቱም ይህ ሁሉ የእኔ ሀሳብ ስለነበር። ፍፁም ስለ ኢየሱስ አልነበረም፡፡ ልክ ግን ህልሜን ለእርሱ ሳስረክበው አውነተኛውን ግብ ማጣጣም ጀመርኩኝ፡፡ የምታሳድደውት ምኞት የቱንም ያህል ቆንጆ ቢሆን ኢየሱስ መሃከለኛው ካልሆነ የኋላ ኋላ አይፈጸምም።

በራዕይና በምኞት መካከል ሰፊ ልዩነት አለ፡፡ ራዕይ በእግዚአብሔር መንፈስ መሪነት የአንድ ሰው የወደፊት እይታ ነው። እግዚአብሔር ለህይወትህ ያለው እቅድ ነው። ምኞት ግን የራስህ የሆነ የወደፊት እይታ፤ መሆን የምትፈልገውም ዕቅድ ነው፡፡ ያንተ ጉዳይ ነው፡፡ እግዚአብሔር የራዕይ ምንጭ ነው፤ አንተ ግን የምኞትህ ምንጭ፡፡ የምኞትህ የጊዜና የስኬቱ ጉዳይ የሚወሰነው በአንተ ነው፤ የራዕይና የዓላማ የጊዜና የስኬቱ ጉዳይ የሚወሰነው ግን በእግዚአብሔር ነው፡፡ ምኞትህን በማሳካትህ ተስፋ ልታደርግ የምትችልበት ጉዳይ ቢኖር የራስ ደስታ ነው፤ ራዕይህን በማሳካት የሚመጣው እርካታ ግን ለአንተም በዙሪያህም ባሉት ሰዎች ላይ ተፅዕኖ አለው፡፡

በምኞት የሚነዱ ሰዎች ግባቸውን ለማሳካት ሌሎችን ሁሉ ሊገድሉ፣ ምናልባትም ሂትለር እንዳደረገው የሰውን ዘር ሁሉ ሊያጠፉ ይችላሉ፡፡ ራዕይ ግን ህይወት ሰጪ ነው፡፡ ራዕይ ባይኖር ህዝብ መረን ይሆናል ብሏል ጠቢቡ ሰለሞን፡፡ በ19ኛው ክፍለ ዘመን የነበረ ጆርጅ ሙለር የተባለ እንግሊዛዊ ሚሽነሪ ከእግዚአብሔር ለተቀበለው ራዕይ የኖረ፤ ምሳሌ የሚሆን ሰው ነበር፡፡ ወላጅ ላጡ ልጆች ደስታ ሊሰጥ ነበር ሲነሳ፡፡ ወላጅ ላጡ ልጆች ማሳደጊያውን ለመጀመር ሁሉን እርግፍ አድርጎ በመተው እግዚአብሄርን ለእያንዳንዱ ዝርዝር ጉዳዮች አቅርቦቱን ተማምኗል፡፡ ዓላማው ለእግዚአብሔር ክብርና ለሌሎች በረከት እንጂ ለራሱ የግል ፍላጉቱ ጥቅም አይደለም፡፡

ወደ ዳዊት ታሪክ እንመለስና ሳሙኤል ዳዊትን የንግስናን ቅባት ሲቀባው ያ ጊዜ በዳዊት ህይወት የእግዚአብሔርን ዓላማ ማሳያ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ ለቀጣይ አስራ አምስት ዓመታት ግን በዳዊት ህይወት ላይ ምንም አልተገለጠም፡፡ በእነዚያ የመጠበቅ ዓመታት ውስጥ ዳዊት ጎልያድን ገጥሟል፣ በሳኦል ሲሰደድ ነበር፣ በበረሃ ተደብቋል፣ በመንከራተት ኖሯል እንዲሁም ብዙ ጦርነቶችን ተዋግቷል፡፡ ሁሉን አሸንፎ ለመኖር ግን ትኩረቱን በራዕዩ ላይ ማተኮር ነበረበት፡፡ ዳዊት ከበግ እረኝነት ወደ ንግስናው ለመምጣት በብርቱ ተፈትኗል፡፡

በእግዚአብሔር ዓላማ ውስጥ ስትጓዝ እግዚአንሔር ያለህና ያለህበት ሁኔታ ላይጣጣም ይችላል፡፡ ግን እግዚአንሔር ቸል ብሎህ አይደለም፡፡ በህይወትህ ላይ እግዚአንሔር የገባልህ ተስፋ የተረሱ አይደሉም፡፡ ይልቅ ከእረኝነት ወደ ንጉስነት ሊለውጥህ እየሰራብህ ነወ፡፡

እግዚአብሔር ምን ተስፋ ሰጥቶሃል? ዓላማህ ምንድነው? በምንም ሁኔታ ውስጥ እለፍ እግዚአብሔር ለወደፊት የሰጠህን ራዕይ ግን ልብ በል፡፡ እግዚአብሔር ለህይወትህ ያለው ዓላማ ይፈፀማል፡፡

ቅዱሳት መጻሕፍት

ቀን 2ቀን 4

ስለዚህ እቅድ

በእግዚአብሔር ዓላማዎች መጓዝ

ልክ ከኤርሚያስና ከዳዊት ህይወት እንደምትመለከተው ሁሉ ዓላማህን ለመኖር፣ እግዚአብሔርን ባለህ ነገርና ባለህበት ቦታ ለማገልገል ታናሽ አይደለህም፡፡ ለዓላማህ መዘጋጀት ማለት ምን ማለት እንደሆነ እና ዓላማህን ሊያጠፉት ከሚያደፍጡ መጠበቅን ተማር፤ እንዲሁም ለአንድ ነገር ተዘጋጅ ይኽውም ትርጉም ያለውን ህይወት እና ዓለምን ሊባርክ የሚችለውን እግዚአብሔርን የሚያከብረውን ህይወት ለመኖር፡፡

More

ይህንን እቅድ ስላቀረበልን Mount Zion Faith Ministry ን ልናመሰግን እንወዳለን። ለበለጠ መረጃ፣እባክዎ የሚከተለውን ይጎብኙ፡ https://mountzionfilm.org/