በእግዚአብሔር ዓላማዎች መጓዝናሙና
ታናሽ አይደለህም
ምናልባት እግዚአብሔር ለህይወትህ ወዳየልህ ለመዘርጋት በጣም ታናሽ ነኝ ብለህ ልታስብ ትችላለህ፡፡ የዳዊትን ሕይወት የሚገልጸው ይህ ዘገባ ነፋስን በጀልባዎቻችሁ ላይ እንዲያንቀሳቅስ ፍቀዱለት።
እግዚአብሔር ለሳሙኤል ንጉስ ሳኦልን በእስራኤል ላይ ንጉስ በማድረጉ እንደተፀፀተ ይነግረዋል፡፡ እግዚአብሔርም ሳሙኤልን ወደ እሰይ ቤት ይልከዋል፤ ምክንያቱም በእስራኤል ላይ ንጉስ ይሆን ዘንድ ከእሰይ ልጆች አንዱን መርጦ ነበርና፡፡ ሳሙኤል ፈፅመው ቀጣይ ንጉስ በሚመስሉ በእሰይ የመጀመሪያ ልጆች በጣም ተማርኮ ነበር፡፡ እግዚአብሔር ግን ሳሙኤልን “ፊቱን የቁመቱንም ዘለግታ አትይ፤ ሰው እንዲያይ እግዚአብሔር አያይምና ናቅሁት፤ ሰው ፊትን ያያል እግዚአብሔር ግን ልብን ያያል አለው፡፡” እግዚአብሔርም ይህንኑ መልዕክት በሳሙኤል ፊት ለተሰለፉት ለተቀሩት የእሰይ ልጆች ደገመው፡፡
በመጨረሻ ሳሙኤል አሰይን የቀረ ሌላ ልጆች ካሉት ጠየቀው፡፡ እሰይም “ታናሹ ገና ቀርቷል፤ በጎችንም ይጠብቃል አለ፡፡” ሳሙኤልም አሰይን “እርሱ እስኪመጣ ድረስ አንቀመጥም ልከህ አስመጣው” አለው፡፡ ዳዊት ይደርሳል፤ ሌላው ታሪክ ነው፡፡
ሳሙኤል የእስራኤል ንጉስ የሚሆን ምን ዓይነት እንደሆነና ዕድሜው ስንት መሆን እንዳለበት በቀደመ ዕውቀቱ በአዕምሮው ላይ ስዕል አድርጎ እንዳለ በግልፅ እናያለን፡፡ ግን የእግዚአብሔር መስፈርቶች የተለዩ ናቸው፡፡ ምናልባት አንተም ይህን መሰል ስዕልና እግዚአብሔርን ለማገልገል ዝግጁ ያደርገኛል ብለህ በአእምሮህ ላይ ያኖርከው የጊዜ ሰሌዳ ይኖር ይሆናል፡፡ የ13 ዓመት ልጅ ሳለሁ እንደ እኔ ያለ ልጅ ለእግዚአብሔር ሊያደርገው የሚችለው ምንም ነገር እንደሌለ ለራሴ መናገሬን አስታውሳለሁ። ስለዚህም እስከ ዩኒቨርሲቲ እጠብቃለሁ፡፡ የእግዚአብሔር መልስ ለምክንያቴ የነበረው ግን “ለምን አሁን አትጀምርም” የሚል ነበር፡፡ በርግጠኝነት አገልግሎት ለመጀመር ምን መወሰድ እንዳለበትም አላውቅም፡፡ ዳዊትም ሲቀባ ንጉስ ለመሆን ምን መሟላት እንዳለበትም አያውቅም ነበር፡፡ የመጨረሻ ልጅ ነበር፡፡ ለቅባት በሳሙኤል ፊት በተሰለፉበት ስብሰባ ላይ ማንም አልጋበዘውም ነበር ምክንያቱም አባቱ እሰይ በጣም ታናሽና ከቁጥር የማይገባ እረኛ አድርጎት ቆጥሮት ነበርና፡፡ አውነቱ ግን አግዚአብሔር በራሳቸው ጥንካሬ በሚታመኑት ሳይሆን በእርሱ ብቻ የሚደገፉትን ሰዎች ይሻል፡፡ ሐዋሪያው ጳውሎስ የእግዚአብሔር ፀጋ ለእኛ በቂ እንደሆነና ኃይሉም በድካማችን እንደሚበረታ ይናገራል፡፡
ዳዊት በእግዚአብሔር የመመረጡ ምክንያት እግዚአብሔር የሚፈልገው ዓይነት ልብ ስለነበረው ነው፡፡ አንተ በእግዚአብሔር ዓላማ ውስጥ ለመጓዝ ታናሽ አይደለህምና ተበረታታ፤ የፍፅምናን ሀሳብ የምታሟላ መስሎ ባይሰማህም እግዚአብሔር ግን ሊጠቀምብህ ይችላል፡፡ እግዚአብሔርን በማያከብር ጎዳና ላለመሄድ እምቢ ማለትህ ሞኝነት አለመሆኑን አስታውስ! ይልቁንም የእግዚአብሔርን መመሪዎች በመታዘዝህ ወደ ዓላማህ የሚያንደረድርህ ነው፡፡ ባመንከው ጉዳይ ላይ ሌሎች ሲያላግጡብህ የዳዊትም ቤተሰቦች ከቁጥር እንዳላስገቡትና ኋላም በፍፃሜው በብዙ አክብሮት በፊቱ መሆናቸውን አትርሳ፡፡ በርታ! መሰረት በሆነው በኢየሱስ ላይ በመቆም የዓላማ ጉዞ ጀምረሃል፡፡
ስለዚህ እቅድ
ልክ ከኤርሚያስና ከዳዊት ህይወት እንደምትመለከተው ሁሉ ዓላማህን ለመኖር፣ እግዚአብሔርን ባለህ ነገርና ባለህበት ቦታ ለማገልገል ታናሽ አይደለህም፡፡ ለዓላማህ መዘጋጀት ማለት ምን ማለት እንደሆነ እና ዓላማህን ሊያጠፉት ከሚያደፍጡ መጠበቅን ተማር፤ እንዲሁም ለአንድ ነገር ተዘጋጅ ይኽውም ትርጉም ያለውን ህይወት እና ዓለምን ሊባርክ የሚችለውን እግዚአብሔርን የሚያከብረውን ህይወት ለመኖር፡፡
More
ይህንን እቅድ ስላቀረበልን Mount Zion Faith Ministry ን ልናመሰግን እንወዳለን። ለበለጠ መረጃ፣እባክዎ የሚከተለውን ይጎብኙ፡ https://mountzionfilm.org/