በእግዚአብሔር ዓላማዎች መጓዝናሙና
ዓላማ ምንድነው?
ዓላማ ማለት እግዚአብሔር አንተ እንድታከናውነው የሰጠህ ስራ ወይም በምድር ላይ አንተ እንድትፈታው የተፈለገ ችግር ተብሎ ሊተረጎም ይችላል፡፡ አንተ እግዚአብሔር አስቀድሞ ያዘጋጀውን መልካሙን ስራ ለማድረግ በክርስቶስ ኢየሱስ የተፈጠርህ ነህ፡፡
በእርግጠኛነት የአንድን ምርት ዓላማ ለመረዳት ከፈለግህ አምራቹን መጠየቅ አለብህ፡፡ ለዚህም ነው የፈጠራ ባለቤቶች ስለፈጠሩት ፈጠራ የሚገልፅ ወይም የሚያብራራ መመሪያ አተገባበር የሚያዘጋጁት፡፡ እግዚአብሔር የእኛ ፈጣሪና አምራች ነው፤ ለህይወታችን ያለው መመሪያ ደግሞ ቃሉ ነው፡፡ ብዙ ጊዜ ዓላማችንን ለመረዳት ከፈጣሪያችን ውጪ በሆኑ ነገሮች ሁሉ ላይ ስናማትር እንገኛለን፡፡
ስለዚህ ዓላማህን በሚገባ ለማወቅ የመጀመሪያው እርምጃ በክርስቶስ ኢየሱስ በኩል ከእግዚአብሔር ጋር ህብረት ማድረግና ቃሉን ማሰላሰል ነው፡፡ በማህበራዊ ሚዲያ የምታያቸውን የሰዎችን ህይወት ማጥናት አግዚአብሔር በአንተ ህይወት ወዳለው ጥሪ አንዳች አያቀርብህም፡፡ ስለዚህ ዓላማ ያለውን ትክክለኛውን መንገድ ልታገኝ የምትችለው የእግዚአብሔር ቃል የመመሪያ መጽሐፍህ ሲሆን ብቻ ነው፡፡
አንድ ነገር ማስተዋል የግድ ይላል ይኸውም የነገር ዓላማ የተፀነሰው ከፍጥረት ወዲህ ሳይሆን ከፍጥረት ጅማሮ ማዶ ነው፡፡ ያ ማለት እግዚአብሔር አንተን ከመፍጠሩ በፊት ለአንተ ዓላማ ነበረው፡፡ ለኤርሚያስ ሲናገር “በሆድ ሳልሰራ አውቄሃለሁ፤ ከማኅፀንም ሳትወጣ ቀድሼሃለሁ፤ ለአህዛብም ነብይ አድርጌሃለሁ” አለው፡፡ በህይወት ጎዳናህ ላይ መሰናክል ሲገጥምህ አንድ ነገርን ማሰብ አስፈላጊ ነው፡፡ ይኸውም ከመፈጠርህ በፊት እግዚአብሔር እንደሚያውቅህና ለትልቅ ዓላማ እንዳዘጋጀህ!
የሰይጣን ዋንኛ ትኩረቱ ይህን ዓላማ መስረቅ ነው፡፡ ያንተን ውስንነትህን እና ድካምህን በመጠቀም ግብህን የማትመታ፤ የማትጠቅም እንደሆንህ እንዲሰማህ ያደርግሃል፡፡ እንደነዚህ አይነት ፍላፃዎች በሚወረወሩብህ ጊዜ የእግዚአብሔርን የእውነት ቃል አውጅ፡፡ እግዚአብሔር አንተን ማን ብሎ ጠርቶሃል? ከዚህ የተለየ ማንም ሌላ እንዲነግርህ አትፍቀድለት፡፡
ኤርሚያስ በህይወቱ ላይ ከሚያየው ተጨባጭ እዉነት ተነስቶ እግዚአብሔርን ላለማገልገል ምክንያት መደርደር ጀመረ፡፡ በእርግጥ ጥሩ ተናጋሪ አልነበረም፡፡ በእድሜውም አልበሰለም ነበር፡፡ እግዚአብሔር ግን ኤርሚያስ የደረደራቸውን ምክንያቶች ውድቅ በማድረግ ሃይልን ሰጥቶ አስታጥቆታል፡፡
ወደ ጥሪዬ ትኩረት ማድረግ ስጀምር የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪ ነበርኩኝ፡፡ ከዓለማዊ ትምህርቴ ጋር ትግል ላይ የነበርኩኝና በብዙ መምህራኖቼ በህይወቴ ፈፅሞ ስኬት እንደማይሆንልኝ ይነገረኝ ነበር፡፡ በዚህ ዓይነት የህመምና የሀፍረት ስሜት ውስጥ ስናጥ ሳለሁ እግዚአብሔር እንድነሳና ሲፈጥረኝ ላሳካው ለሚፈልገው ዓላማ እንደነቃ ነገረኝ፡፡ ሰዎች ሲጠሩኝ ውድቀት ይሉኝ ነበር፤ እግዚአብሔር ግን አንድ ነገር ግልፅ አደረገልኝ ይኸውም ራሴን እግዚአብሔር ባላለኝ ስም እንዳልጠራው፡፡
ምን ይሆን ምክንያት የምታደርገው? በማንኛውም ቦታ፣ በየትኛውም ዕድሜ ወይም የኑሮ ደረጃ ሁን እግዚአብሔር መንግስቱን እንድትሰራለት ሊጠቀምብህ ይችላል፡፡ በዲያቢሎስ ሽንገላ በፍፁም አትወናበድ፡፡ ራስህን ዝቅ አድርገህ አጥይ፡፡ ራስህን አትወስነው፡፡ እንዲሁም እግዚአብሔርን አትወስነው፡፡ ለራስህ አሁን እግዚአብሔር ሊጠቀምብኝ በሚችልበት ዕድሜ ላይ አልደረስኩም ብለህ አትንገረው፡፡ በህይወትህ ላይ የእግዚአብሔርን ዓላማ በቶሎ መረዳት እጅግ በጣም ማትረፍ ነው፡፡ ዛሬም ሆነ ነገ ልታውቅ የሚገባህ ነገር እግዚአብሔር የበቁትን አይጠራም፤ የተጠሩትን ያበቃል እንጂ!
ቅዱሳት መጻሕፍት
ስለዚህ እቅድ
ልክ ከኤርሚያስና ከዳዊት ህይወት እንደምትመለከተው ሁሉ ዓላማህን ለመኖር፣ እግዚአብሔርን ባለህ ነገርና ባለህበት ቦታ ለማገልገል ታናሽ አይደለህም፡፡ ለዓላማህ መዘጋጀት ማለት ምን ማለት እንደሆነ እና ዓላማህን ሊያጠፉት ከሚያደፍጡ መጠበቅን ተማር፤ እንዲሁም ለአንድ ነገር ተዘጋጅ ይኽውም ትርጉም ያለውን ህይወት እና ዓለምን ሊባርክ የሚችለውን እግዚአብሔርን የሚያከብረውን ህይወት ለመኖር፡፡
More
ይህንን እቅድ ስላቀረበልን Mount Zion Faith Ministry ን ልናመሰግን እንወዳለን። ለበለጠ መረጃ፣እባክዎ የሚከተለውን ይጎብኙ፡ https://mountzionfilm.org/