ክርስቶስ የመጨረሻችን ንግስት አስቴርናሙና

ክርስቶስ የመጨረሻችን ንግስት አስቴር

ቀን {{ቀን}} ከ3

ለእኛ የክርስቶስ ጣልቃ-ገብነት

ልክ አስቴር ራሷን የእነርሱ ወገን እንደሆነች በመግለጥ ብቻ ልትረዳ እንደቻለች ኢየሱስም እንደ እኛ ሰው ሆኗል፤ በዚህም በመስቀል ላይ የእኛን ኃጢአት ሊከፍልና እርሱ በእኛ ቦታ ሊሆን ወገናችን መሆኑን ገልጧል፡፡ አይሁዳውያን እግዚአብሔር ከጥፋት ሲያድናቸው ደስ እንዳላቸው ሁሉ እኛም በትንሳኤው ኃይል በነፃነት እንድንኖር ኢየሱስ ጣልቃ ስለገባልን እጅግ ደስ ሊለን ይገባል፡፡

ቀሪዎቹ የአስቴር ምዕራፎች በሚመስጥ ሁኔታ አስደናቂ ክስተቶች የተሞሉባቸው ናቸው፡፡ በአስቴር ምዕራፍ 5 ላይ አይሁዳዊቷ ንግስት ያለ ንጉሱ ቅድመ ፈቃድ በድፍረት ስለ ህዝቧ ስትል ጣልቃ ስትገባ እናያለን፡፡ እርሱም በሚያስገርም ተአምር ተቀብሏት ባዘጋጀችው ግብዣ ላይም ታደመ፡፡ በዚያም የሀማን ዕቅድ አጋልጣ ንጉሱም ስለ ህዝቧ ምህረት እንዲያደርግ ለመነች፡፡ ሀማ ተሰቀለ፡፡ አርጤክሲስም የሀማን ሀብት ለአስቴር ሰጥቶ ሀማን እጅግ ከፍ ከፍ ያደረገበትን ሞገሱንና ስልጣኑን ደግሞ ለመርደኪዮስ ሰጠው፡፡

አይሁዳውያንን ለማጥፋት የታተመውን የሀማን አዋጅ ለመሻር ለንጉሱ ህጉ ይከለክለዋል፤ ስለዚህም አሁንም የሞት ስጋት ይዟቸዋል፡፡ ነገር ግን በመርደኪዮስ በኩል ሁለተኛ አዋጭ በማፅደቅ አይሁድ በሚችለው ሁሉ እንዲዋጋ ሆነ፡፡ መለኮታዊ ዕድለኝነት ሆኖ አይሁዳውያን ባለ ድል ሆኑ፤ ስለዚህም ያልተበረዘ በዓል አከበሩ፡፡ ከዚህ የተነሳ ብዙ አህዛብ አይሁዳውያን ሆኑ፤ ልክ በህይወታችን አስደናቂው የእርሱ ጣልቃ ገብነት ሲሆን እግዚአብሔርን የሚጠሉት ወደ ኢየሱስ እንደሚለወጡ፡፡

አሁንም ይህ ሁሉ የሚያስተጋባው ወንጌልን ነው፡፡ ኢየሱስ የኖረው በታላቁ ቤተ መንግስት በሰማይ ሲሆን ነገር ግን በፈቃዱ ክብሩን ትቶ በእኛ ፈንታ በምድር ላይ ስለ እኛ በፍቃዱ ጣልቃ ገባ። ከዚህ የሚበልጠው ነገር ኢየሱስ አሰቴር ራሷን አደጋ ውስጥ ከትታ እንዳደረገቸው አይደለም ያደረገው፡፡ እርሱ ህይወቱን ነው ዋጋ የከፈለበት፡፡ አስቴር “ብሞትም ልሙት” ነው ያለችው፡፡ ኢየሱስ ግን በሚገባ ያለው “በምሞት ጊዜ እሞታለሁ” ነው፡፡ አስቴር ራሷን አደጋ ላይ የጣለችው ስለ ህዝቧ ሞገስ ለማግኘት ነው፡፡ ኢየሱስም ህይወቱን የሰጠን እኛ ያለመሸማቀቅ በነፃነት በንጉሱ ፊት በማንኛውም ጊዜ እንድንቀርብ ነው፡፡

ጠቅለል ያለው የአስቴር መፅሐፍ ታሪክ፤ ስለ ስደት፣ የዘር ጥፋት ስጋት፣ መዋጀት፣ በመጨረሻም ከስደት ስለ መመለስ ሲሆን ከዘፍጥረት እስከ ራዕይ ያለውን ታላቅ ማብራሪያ ማሳያ በመሆን በ4 ደረጃዎች ማለትም በፍጥረት፣ ውድቀት፣ መዋጀት እና አዲስ ፍጥረት በሚሉት ተገልጧል፡፡ ልክ አይሁዳውያን ከዘር ጥፋት በአስቴር ጣልቃ ገብነት እንደተዋጁትና ከስደትም ወደ እየሩሳሌም እንደተመለሱ ሁሉ እኛም ከአስቴር በተሻለውና እውነተኛ በሆነው በክርስቶስ ኢየሱስ በኩል ተዋጅተናል፡፡ ዛሬ ላይ በዚህች በተጣለች ዓለም ላይ ምንም ያህል አስቸጋሪ የክርስትና ስደት ቢበዛብንም አንድ ቀን ግን ዕምባ ፈፅሞ በሌለበት፣ ህመም ፈፅሞ በሌለበት፣ በሽታ በማይታሰብባት፣ ሞት ፈፅሞ በሌለበት በአዲሲቷ እየሩሳሌም በደስታ እንቦርቃለን፡፡ በምንም ሁኔታ ውስጥ እለፍ ይህ የክብር ወንጌል እውነት ግን እምነትና ብርታት ይጨምርልህ፡፡

ቀን 2

ስለዚህ እቅድ

ክርስቶስ የመጨረሻችን ንግስት አስቴር

የአስቴር መጽሐፍ የእግዚአብሔር ህዝብ ከዘር ወይም ከጅምላ ጥፋት ራሱን ሊከላከል እንኳን አቅም እንደሌለው በግልፅ ያሳያል፡፡ ራሷን አደጋ ውስጥ ጥላ ስለ ህዝቡ በንጉሱ ፊት ለመቆም ከህዝቡ ጋር በመሆን ራሷን ለየች:: ይህ የሶስት ቀናት የንባብ ዕቅድ የአስቴርን የጥንካሬና ፍቅር ታሪክ የሚዳስስና የክርስቶስን ታሪክ የሚያንፀባርቅ ሲሆን ይኸውም እርሱ እንደ እኛ ተቆጠሮ፣ ስለ እኛ መካከለኛ ሆኖ እና እኛ ራሳችንን ማዳን በማንችልበት ሁኔታ አዳነን፡፡

More

ይህንን እቅድ ስላቀረበልን Returning to the Gospel - East Africa ን ልናመሰግን እንወዳለን። ለበለጠ መረጃ፣እባክዎ የሚከተለውን ይጎብኙ፡ https://returningtothegospel.com/