ክርስቶስ የመጨረሻችን ንግስት አስቴርናሙና

የእኛ አቅም ማጣት
አንድ ጊዜ እኔና ቤተሰቤ በባህር ዳርቻ ባለ ሪዞርት በዓልን አሳለፍን፡፡ ሪዞርቱ ለልጆቼ ደስታ የሚሆን የሚያስገርም መዋኛ ገንዳ ነበረው፡፡ እኔ መዋኘት አልችልም፤ ነገር ግን አንድ ቀን ጠዋት በማላውቀው አንድ እንግዳ ምክንያት ዘልዬ ለመግባት ወሰንኩኝ፡፡ ይህ ሞኝነት ነበር፡፡ ወዲያው ግን መስጠም ጀመርኩኝ፡፡ ይመስገነውና ከልጆቼ አንዱ ብቅ ጥልቅ ስል ቢያየኝ ወደ ውሃው ዘሎ ገብቶ አዳነኝ፡፡
ልክ እኔ እንደገጠመኝ እየሰጠመ ያለ ሰው የዋና ትምህርት በመዋኛው ገንዳ ጫፍ ላይ ዘና ብሎ ከቆመ ሰው መማር አይደለም የሚያስፈልገው፡፡ የተዋጠ ሰው፤ እየሰጠመ ያለ ሰው የሚፈልገው የሚሰጥመውን ሰው አለመቻል የሚያይ ሰው፤ ችግራቸውን ለይቶ እነሱን ወደ ደህንነት ስቦ ለማውጣት ጣልቃ የሚገባ ሰው ነው፡፡
ይህ ነው የአስቴር መጽሐፍ የሚያትተው፡፡ የአስቴር ታሪክ ከወንጌል ጋር ትይዩ ሆኖ በኢየሱስ በኩል ደግሞ ያለንን መንፈሳዊ ቤዛነት የሚያሳይ አስደናቂ ምስል ነው።
በመጀመሪያ መጽሐፉ የእኛን ተስፋ ቢስነት ፤ ከኃጢያትና ከሞት ራሳችንን ለማዳን የማንችል መሆናችንን በግልፅ የሚያሳይ ነው፡፡ ሁለተኛ ክርስቶስ በእኛ ሁኔታ ሊገኝ ሰው ሆኖ መምጣቱን ያስታውሰናል፡፡ ሦስተኛ ክርስቶስ በሞቱና ትንሳኤው አማካኝነት የዘላለም ህይወት አሸናፊ እንድንሆን ጣልቃ መግባቱን ያሳያል፡፡
በአስቴር መጽሐፍ የተከሰተው ክስተት ንጉስ አርጤክሲስ ነግሶ በነበረበት የወቅቱ ልዕለ-ሀያል ሀገር በሆነችው የፋርስ ግዛት ዋና ከተማ ውስጥ ነበር፡፡ በጊዜው ተሰደው ያሉት አይሁዳውያን በፋርስ ግዛት ሁሉ ተበትነው ነበር፡፡ በነገራችን ላይ በሚያስደንቅ ሁኔታ የእግዚአብሔር ስም አንድም ቦታ ያልተጠቀሰበት መጽሐፍ የአስቴር መጽሐፍ ነው፤ ፀሎትም እንዲሁ፡፡ ሆኖም ግን ታሪክን ለማቅናትና ህዝቡን ለመጠበቅ ከብሔራዊው ዝግጅት ጀርባ የማይካደውን ሉዓላዊ የእግዚአብሔርን ስራ በግልፅ እናያለን፡፡
አስቴር ከጅምሩ እስከ መጨረሻው ድረስ በጣም ልብ የሚነካ ታሪክ ያላት ናት፡፡ ንግስት አስጢን በምዕራፍ 1 ላይ ንጉሱ ለወንድ ነገስታት ባዘጋጀው ትልቅ ግብዣ ላይ ለመሳተፍ ፈቃደኛ ባለመሆኗ ከንግስትነቷ ተወግዳለች፡፡ በምዕራፍ 2 ላይ ደግሞ አስቴር የተባለች ወላጅ አልባ የመርደኪዮስ የአጎት ልጅንና መርደኪዮስ የተባለውን በዕድሜ የገፋ አሳዳጊ ዘመዷን እናገኛለን፡፡ እነርሱም ከመቶ ዓመታት በላይ በፋርስ ግዞተኛ ሆነው የሚኖሩ አይሁዳውያን ነበር፡፡ አስቴር የአስጢንን ቦታ ለመተካት በሚወዳደሩት ደናግል መሃል ለመወዳደር ተመረጠች፡፡ ከደናግሉም መሃል በንጉሱ ፊት ሞገስ ስላገኘች የንግስትነት ዘውዱን ጫነች፡፡ ቀጥሎ ደግሞ ሀማ የሚባል ሰው ምክትል ፕሬዘዳንት በማድረግ ሁሉም ሰው ለእርሱ ተደፍተው ይሰግዱለት ነበር፤ መርደኪዮስ ግን አልሰገደለትም ነበር፡፡ ሀማም ተቆጣ፡፡ ስለዚህም መርደኪዮስን ብቻ ሳይሆን በግዛቱ የሚገኙትን ድፍን የአይሁድን ዘር ለማጥፋት ወሰነ፡፡
በምዕራፍ 3 የአስቴር መጽሐፍ መጨረሻ ላይ አይሁዳውያን ለገጠማቸው ዕጣ ፈንታ ምንም ማድረግ የማይችሉ ነበሩ፡፡ እኛም በዘፍጥረት ምዕራፍ 3 ላይ ዕጣ ፈንታችን እንዲሁ ነበር፡፡ እኛ ሁላችን ከፍጥረታችን የእግዚአብሔር ክብር የጎደለንና ሞት የተገባን፤ መንፈሳዊ ሁኔታዎቻችንን በምንም መቀየር የማንችል ነበርን፡፡ የቤተ ክርስቲያን አገልግሎታችን አያድነንም፡፡ ጥምህርታችንም ሆነ ሙያችን እንዲሁ፡፡ በአስቴር ዘመን እንደነበሩት አይሁዳውያን ወደ እርሱ የምንገባበት፣ የሚታደገን እና ከእግዚአብሔር ጋር የሚያስታርቀን አዳኝ ያስፈልገናል፡፡ እግዚአብሔርን አመስግን፤ እርሱ መጥቷልና፡፡
ስለዚህ እቅድ

የአስቴር መጽሐፍ የእግዚአብሔር ህዝብ ከዘር ወይም ከጅምላ ጥፋት ራሱን ሊከላከል እንኳን አቅም እንደሌለው በግልፅ ያሳያል፡፡ ራሷን አደጋ ውስጥ ጥላ ስለ ህዝቡ በንጉሱ ፊት ለመቆም ከህዝቡ ጋር በመሆን ራሷን ለየች:: ይህ የሶስት ቀናት የንባብ ዕቅድ የአስቴርን የጥንካሬና ፍቅር ታሪክ የሚዳስስና የክርስቶስን ታሪክ የሚያንፀባርቅ ሲሆን ይኸውም እርሱ እንደ እኛ ተቆጠሮ፣ ስለ እኛ መካከለኛ ሆኖ እና እኛ ራሳችንን ማዳን በማንችልበት ሁኔታ አዳነን፡፡
More
ይህንን እቅድ ስላቀረበልን Returning to the Gospel - East Africa ን ልናመሰግን እንወዳለን። ለበለጠ መረጃ፣እባክዎ የሚከተለውን ይጎብኙ፡ https://returningtothegospel.com/