በየእለቱ ከእግዚአብሔር መስማትናሙና
እግዚአብሔር በችሎታችን (በተሰጥኦ) እና በስጦታችን በኩል ይናገራል
የሰው ልብ መንገዱን ያዘጋጃል፣ እግዚአብሔር ግን አካሄዱን ያቀናለታል፤ ምሣ 16:9
ብዙውን ጊዜ ሰዎች የሚደነቁትና ምን ለመሥራት እንዳለባቸው በሕይወታቸው ያስባሉ፡፡ የመኖሬ ዓላማ ምንድነው; እግዚአብሔር ለሕይወቴ እቅዱ ምንድን ነው; ለእንደዚህ ጥያቄዎች እግዚአብሔር መልስ የምሰጠው በተፈጥሮ ችሎታችንና ስጦታዎቻችን በኩል ነው፡፡ እሱ ዓላማችንን ለማድረግ በሰጠን ተሰጥኦና ልምዳችን እንድንረዳ ያደርጋል፡፡
የእግዚአብሔር ሥጦታ ተሰጥኦ ወይም እኛ በተለምዶ ‹‹ስጦታ›› የምንለው እኛ በቀላሉ የምናደርጋቸው፣ በተፈጥሮ የሚመጣ ነገር ነው፡፡ ለምሣሌ አንድ ታላቅ የኪነ ጥበብ ሰው እንዴት አድርገው ቅርጽና ቀለም እንደሚያዋህድ ያውቃል፣ እንዴት እንደሚያቀልም፣ ቅርፅ እንዴት እንደሚያወጣ፣ የሕንፃ ቅርጽ ማበጀት ይችልበታል፡፡ ብዙ የሙዚቃ ግጥም ፀሐፊዎች በአእምሮአቸው ውስጥ ይሰማሉ ከዚያ በቀላሉ ጣእመ ዝማሬውን (ዘፈኑን) ወይም ቃና በጣም ጥሩ ሙዚቃ ይጽፋሉ፡፡ አንዳንድ ሰዎች በተፈጥሮ ችሎታቸው የማደራጀትና የማስተዳደር ሌሎች ደግሞ በምክር ተሰጥኦ የተካኑ ናቸው፡፡ እንዲሁም ሰዎችን በተሰጦአቸውና በችሎታቸው እንዲሰማሩና ውጤታማ እንዲሆኑ መርዳት ሕይወታቸውንና ኅብረታቸውን ያሳምራል፡፡ የፈለገ ዓይነት ችሎታ ያለን ቢሆንም ታላቅ የሆነ እርካታና ደስታ የምናገኘው በተፈጥሮአችን ያለንን መልካም ነገር ስናደርግ ነው፡፡
በሕይወትህ ዓላማ ገልፅ ካልሆንክ፣ የሚቀናህን ነገር በማድረግ ከዚያ እግዚአብሔር ምርጫህን ልፋትና ጥረት በመባረክ እንዲያረጋግጥልህ ተመልከት፡፡ ያልተሰጠህን በማድረግና በመሞከር ጊዜህና ሕይወትህን ዝም ብለህ አታጥፋ፡፡ ሰዎች ዝም ብሎ ያለተሰጥኦቸው በሚሰራበት ጊዜ በጣም የሚያሳዝኑና በዙሪያቸው ያሉትም ያሳዝናሉ፡፡ ነገር ግን ሰዎች በተሰጥኦቸው ቦታ በአግባቡ በሚሆንበት ወቅት በሥራቸው ስኬታማ ለቀጠሩአቸውም በረከትና ክብር ለሚሠሩትም በረከት ናቸው፡፡
እኛ ስኬታማ በምንሆንበት ሥራ ላይ ስንሆን የእግዚአብሔርን ሕልውና (መገኘት) ወይም በጥረታችን ላይ የእግዚአብሔርን ኃይል እናይበታለን፡፡ በስጦታችን ውስጥ ሆነን ስንንቀሳቀስ ሥራችን ለእግዚአብሔር ክብር የሚያመጣና የሌሎችን ሕይወት የሚያገለግል ይሆናል፡፡ እግዚአብሔር በቅባቱ ሠላም እና ደስታ በመስጠት እኛ የእርሱን አላማ እያደረግን መሆኑን በዚያ እንድናውቅ ያደርጋል፡፡
ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡- መልካም የሆንክበትን ሥራ እሱ ለአንተ የእግዚአብሔር ሥጦታ ነው፡፡
ቅዱሳት መጻሕፍት
ስለዚህ እቅድ
ይህ አምልኳዊ አገልግሎት ከእግዚአብሄር ጋር አብዛኛውን ጊዜዎን እንዲጠቀሙ እና ከእግዚአብሔር ጋር የበለጠ የግል ጊዜን በማሳለፍ ግንኙነቶችዎን እንዲያሳድጉ እርስዎን ለማነሳሳት እና ለማበረታታት የሚያስችሉ ማስታወሻዎችን ይሰጣል።
More
ይህንን እቅድ ስላቀረቡ Joyce Meyer Ministries ማመስገን እንፈልጋለን። ለበለጠ መረጃ እባክዎን ይህንን ይጎብኙ: https://tv.joycemeyer.org/amharic/