በየእለቱ ከእግዚአብሔር መስማትናሙና
መንፈስ መኖሪያ ነህ
በመንፈሱ በውስጥ ሰውነታችሁ በኃይል እንድትጠነክሩ ክርስቶስም በልባችሁ በእምነት እንድኖር እንደክብሩ ባለጠግነት መጠን ይስጣችሁ፡፡ ኤፌ. 3:17
ዳግመኛ የተወለድክ ሰው ከሆንክ፣ በእርግጠኝነት ኢየሱስ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል በአንተ ውስጥ ይኖራል፡፡ ዋናው ጥያቄ የሚሆነው እግዚአብሔር በውስጥህ ተመችቶታል ወይ ነው፡፡ ከአንተ ጋር በቤት እንዳለ ይሰማዋል ወይ ነው፡፡ ምንም እንኳ የእግዚአብሔር መንፈስ በአንተ ውስጥ ከአንተ ጋር ብኖርም እንዲሁ ሌሎች ነገሮችም አብሮ ይኖራሉ፡፡ እንደነ ፍርሃት፣ ንዴት፣ ቅንዓት፣ ወይም ማጉረምረም ክርክር ወ.ዘ.ተ፡፡
እግዚአብሔር አንድ ጊዜ እርሱ የምኖርበት ልብ ውስጥ ማጉረምረም፣ ክርክር፣ ብጥብጥ ተወስኖ መኖር ምን ያክል እንደሚያስቸግር የሆነ ምልከታ ሰጠኝ፡፡ እንበልና የጓደኛህ ቤት ስትሄድ ጓደኛህ እንኳን መጣህ! ግባ፡፡ ሻይ ላፍላልህ ገብተህ ትንሽ እረፍ እንደቤትህ ይሰማህ፡፡ ከዚያ ያንተ ጓደኛ በባሏ ላይ መጮህ ጀመረች ሁለታቸውም እርስ በርሳቸው በታላቅ ድምፅ መጯጯህና መደባደብ እያለ በፊትህ ከጅምሩ እንዲህ ያለ ጥብ ባለበት መሆን ጥሩ ስሜት ይሰማል; ያዝናናል; እረፍት ይሰጣል ወይ;
ለእግዚአብሔር መንፈስ የሚመች ማረፊያ ቤት ለመሆን ከፈለግን የእግዚአብሔርን መገኘት የሚያዘናጉንና እርሱን የሚሳዝኑትን ነገሮች መተው ወይም ማቆም አለብን፡፡ ማማረርን፣ ሁከት ከውስጥ እረፍት ማጣትን ክፉን ማሰላሰል ይቅር አለማለትን ከውስጣችን ማቆምና መተው አለብን፡፡ በዚያ ፋንታ በውስጣችን የምስጋና እና እግዚአብሔርን የማክበር መንፈስ መኖሩን ማረጋገጥ፡፡ አፋችን በምሥጋና መሞላት አለበት፡፡ ስንነቃ በየቀኑ ‹‹ጌታ እንደምን አደርክ›› ማለት መለማመድ አለብን፡፡ በቤትህ እንዳለህ ይሰማ በእኔ ውስጥ ማለት አለብን፡፡
በየጊዜው ምን በልባችን ውስጥ እንደገባና ከልባችን ውስጥ እንደወጣ ቁጥጥር ማድረግ አለብን፡፡ ምክንያቱም የእግዚአብሔር የማደሪያ ቦታ ስለሆነ ጥበቃ ይፈልጋል፡፡ ውስጣችንን ስንመረምር ቅዱስና እግዚአብሔር የመረጠው ቤቱ መሆኑን ማረጋገጥ አለብን፡፡ እርሱ እንዲመቸው እናስገባውና በእኛ ውስጥ ይመቸው፡፡
ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡- ለጌታ መንፈስ ማደሪያነት ምቹ መሆንን እርግጠኛ ሁን
ቅዱሳት መጻሕፍት
ስለዚህ እቅድ
ይህ አምልኳዊ አገልግሎት ከእግዚአብሄር ጋር አብዛኛውን ጊዜዎን እንዲጠቀሙ እና ከእግዚአብሔር ጋር የበለጠ የግል ጊዜን በማሳለፍ ግንኙነቶችዎን እንዲያሳድጉ እርስዎን ለማነሳሳት እና ለማበረታታት የሚያስችሉ ማስታወሻዎችን ይሰጣል።
More
ይህንን እቅድ ስላቀረቡ Joyce Meyer Ministries ማመስገን እንፈልጋለን። ለበለጠ መረጃ እባክዎን ይህንን ይጎብኙ: https://tv.joycemeyer.org/amharic/