በየእለቱ ከእግዚአብሔር መስማትናሙና

 በየእለቱ ከእግዚአብሔር መስማት

ቀን {{ቀን}} ከ14

ሁልጊዜ ከአንተ ጋር ነው

ጻድቃንም በእውነት ስምህን ያመስግናሉ፤ ቀኖችም በፊጽህ ይኖራሉ፡፡ መዝ 140፡13

የመንፈስ ቅዱስ በእኛ ውስጥ መኖር የሚያረጋግጠው የእርሱ ሁልጊዜ ከእኛ ጋር መሆንና እኛ ስንጠይቀው ሊናገረንና ሊረዳን እንደሆነ ማረጋገጫ ነው፡፡ በመንፈሣዊ ሕይወት ባደግን ቁጥር የተለያዩ ፈተናዎች ውስጥ እናልፋለን፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስን የሰጠን ለመቋቋም እንድንችልና ትክክለኛ ምርጫ እንድናደርግና ከመሳሳት እንድንጠበቅ ነው፡፡

ማንም የሰው ልጅ ፍጹም ስላልሆነ ስህተት ብንሰራም ነገር ግን የእግዚአብሔር ምህረት ሁሌ በኢየሱስ ክርስቶስ ከእኛ ጋር ነው፡፡ እርሱም ይህንን ምህረት ለመቀበል እንድንችል ያበረታታንና ወደ ሬት ጉዞአችንን ለመቀጠል ያስችለናል፡፡ እንዲሁም ልባችንን በሠላም በነፃነት ሆነን የእግዚአብሔርን ድምፅ በማጣራት ለመስማት ያስችለናል፡፡

እያንዳንዱን ስህተታችንን ተከታትለን እራሳችንን እየኮነንና የተሸነፍናትን ስሜት ስናስተናግድ እራሳችንን እናደክማለን፡፡ የእኛን ኃይል በመጥፎ ማንነታችን ከመሙላት ይልቅ ያንን ኃይላችንን ልባችን ከዚያ ወደ ተሻለ ብርታትና ጥልቅ ሕብረት ገብቶ የእግዚአብሔርን ድምፅ በመስማት ላይ እንዲያተኩር ብናደርግ ውጤታማ ያደርገናል፡፡

የእርሱ መገኘትና የእርሱ ምህረት ሁልጊዜ በመንፈስ ቅዱስ በኩል ለእኛ ቀርበዋል፡፡ ዛሬ እግዚአብሔርን እንድትፈልግና የእርሱን ፍቅርና ምህረት እንድትቀበል አበረታታሃለሁ፡፡ የእርሱ እጆች ተዘርግተው ጊዜ ከአንተ ጋር ለመውሰድ እየጠበቀ ነው፡፡

ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡- መንፈስ ቅዱስ ለአንተ ቅርብ እንደሆነ አስተውል፡፡

ቅዱሳት መጻሕፍት

ቀን 9ቀን 11

ስለዚህ እቅድ

 በየእለቱ ከእግዚአብሔር መስማት

ይህ አምልኳዊ አገልግሎት ከእግዚአብሄር ጋር አብዛኛውን ጊዜዎን እንዲጠቀሙ እና ከእግዚአብሔር ጋር የበለጠ የግል ጊዜን በማሳለፍ ግንኙነቶችዎን እንዲያሳድጉ እርስዎን ለማነሳሳት እና ለማበረታታት የሚያስችሉ ማስታወሻዎችን ይሰጣል።

More

ይህንን እቅድ ስላቀረቡ Joyce Meyer Ministries ማመስገን እንፈልጋለን። ለበለጠ መረጃ እባክዎን ይህንን ይጎብኙ: https://tv.joycemeyer.org/amharic/