ከባድ ጭንቀት
መከራንና ሥቃይን መቋቋም የሚቻለው እንዴት ነው?
ሐዋርያው ጳውሎስ ለአንባቢዎቹ “ወደ እግዚአብሔር መንግሥት በብዙ መከራ እንገባ ዘንድ ያስፈልገናል” (የሐዋርያት ሥራ 14:22) ይላል። የሐዋርያት ሥራን ማንበብ ወይም በዓለም ዙሪያ ካሉ ክርስቲያኖችን ምስክርነት መስማት፣ የዚህን ቃል እውነት አረጋግጠዋል። አማኞች ተቃውሞ እና ስደት ይደርስባቸዋል። ምናልባት እርሶም መከራ አጋጥሞት ይሆናል። በዚህ የንባብ እቅድ ውስጥ፣ ልናበረታታዎት እና በመከራን እንዴት መቋቋም እንደሚቻል ማስተማር እንፈልጋለን።
እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ነው፦ ከፍርሃት፣ ከጭንቀትና ከግራ መጋባት ጋር መጋፈጥ
በዚህ የ6 ቀን ጥናት ውስጥ ፍርሃት፣ ግራ መጋባትና ጭንቀትን ለማስወገድ በሕይወታችን ውስጥ የእግዚአብሔር መኖር ምን ያህል ማድረግ እንደሚችል እናያለን። ከእግዚአብሔር ጋር ጊዜ በማሳለፍና ከቃሉ በመማር እነዚህን ተግዳሮቶች እንዴት ማሸነፍ እንደምንችል፣ ትኩረታችንን እንዴት እንደምናስተካክልና አስተሳሰባችንን እንደምንለውጥ እናያለን።
ራስን መጠራጠር እና ጭንቀትን ማሸነፍ
"እንግሊዛዊቷ ሲንዲ ሴምበር በውድድሯ ወቅት እንቅፋት የሆነባትን ጥርጣሬን እና ጭንቀትን እንዴት እንዳሸነፈች ታካፍላለች። ሲንዲ አትሌቶች ትኩረታቸውን ከፍርሃት ወደ እምነት እንዲቀይሩ እና በእግዚአብሔር ላይ ተስፋ እንድያድርጉ ተረዳቸዋለች ። ይህ እቅድ ጭንቀትን በእምነት ለመተካት ቀላል እና ተግባራዊ መንገዶችን ይሰጣል። በስፖርት እና በህይወት ውስጥ ሰላም እና መተማመንን እንድታገኝ ያግዝሃል። ከመወዳደርዎ በፊት እና በኋላ የሚጠቀሙበት የውድድር ተከታታይ አካል ነው። "