ተስፋ
የፋሲካ ታሪክ
የሕይወትዎ የመጨረሻ ሳምንት መሆኑን ቢያውቁ ሳምንቱን እንዴት ያሳልፋሉ? ኢየሱስ በሰው አምሳል በምድር ላይ በነበረው የመጨረሻ ሳምንት በማይረሱ አፍታዎች ፣ በተፈፀሙ ትንቢቶች ፣ በጥልቅ ጸሎት ፣ በጥልቅ ውይይት ፣ በምሳሌያዊ ድርጊቶች እና ዓለምን በሚለውጡ ክስተቶች የተሞሉ ነበሩ፡፡ ከፋሲካ በፊት ባለው ሰኞ እንዲጀምር ተደርጎ የተዘጋጀው ይህ የላይፍ.ቸርች የመጽሐፍ ቅዱስ ዕቅድ የቅዱሱ ሳምንትን ታሪክ እንዲያውቁ ይመራዎታል።
ለዕለት ተዕለት ሕይወትዎ ተስፋ
ቀንዎን ከጆይስ ሜየር ተግባራዊ በሆነ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ይጀምሩ። ይህ ዕለታዊ ማበረታቻ ተስፋ እንዲኖርዎ ፣ አዕምሮዎን ማደስ እንዲችሉ እንዲሁም በየቀኑ በዓላማ መኖር እንዲችሉ ያግዛል!
በየእለቱ ከእግዚአብሔር መስማት
ይህ አምልኳዊ አገልግሎት ከእግዚአብሄር ጋር አብዛኛውን ጊዜዎን እንዲጠቀሙ እና ከእግዚአብሔር ጋር የበለጠ የግል ጊዜን በማሳለፍ ግንኙነቶችዎን እንዲያሳድጉ እርስዎን ለማነሳሳት እና ለማበረታታት የሚያስችሉ ማስታወሻዎችን ይሰጣል።
ክርስቶስ የመጨረሻችን ንግስት አስቴር
የአስቴር መጽሐፍ የእግዚአብሔር ህዝብ ከዘር ወይም ከጅምላ ጥፋት ራሱን ሊከላከል እንኳን አቅም እንደሌለው በግልፅ ያሳያል፡፡ ራሷን አደጋ ውስጥ ጥላ ስለ ህዝቡ በንጉሱ ፊት ለመቆም ከህዝቡ ጋር በመሆን ራሷን ለየች:: ይህ የሶስት ቀናት የንባብ ዕቅድ የአስቴርን የጥንካሬና ፍቅር ታሪክ የሚዳስስና የክርስቶስን ታሪክ የሚያንፀባርቅ ሲሆን ይኸውም እርሱ እንደ እኛ ተቆጠሮ፣ ስለ እኛ መካከለኛ ሆኖ እና እኛ ራሳችንን ማዳን በማንችልበት ሁኔታ አዳነን፡፡
ዘረኝነትና የእኛ ምላሽ
እንደ ክርስቲያን በዙሪያችን ባለው ዓለም ያለውን የዘረኝነት ውጤትና የእኛን ምላሽ መመልከት እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡ ይህ ጊዜውን የጠበቀ እጅግ አስደሳች የአራት ቀናት ዕቅድ የዘረኝነትን ስር እንዲሁም በዚህ ዓለም በእግዚአብሔር የመዋጀትና የተሃድሶ ስራ ውስጥ እንድንጫወት የተጠራንበትን ጉዳይ ይዳስሳል፡፡ ይህ ዕቀድ የተዘጋጀው በዩቨርዥን ነው፡፡
የሉቃስ ወንጌል፡-
ሉቃስ ስለ ኢየሱስ ሕይወት፣ ሞት እና ትንሳኤ የዓይን ምስክር የሆነ ዝርዝር ዘገባ ጽፏል። ይህ የምዕራፍ-ቀን ዕቅድ ተዓማኒነት ያለው፣ የዝግጅቶች ቅደም ተከተሎችን ያቀርባል፣ ነገር ግን ቸር ከሆነው አዳኝ ጋር ያስተዋውቀናል። የጠፉትን ለመፈለግ እና ለማዳን መጣ፣ እናም እኛንም ወደዛ የምህረት ተልእኮ ጠራን። ይህ እቅድ የተዘጋጀው በYouVersion ነው።
የዮሐንስ ወንጌል፡-
በዚህ የምዕራፍ-ቀን እቅድ ውስጥ፣ ሁሉን ቻይ የሆነውን እግዚአብሔርን ታገኛላችሁ - የሁሉ ነገር ፈጣሪ - በሰው መልክ፣ ለሁሉም ሰው መዳንን ለማምጣት የተወለደው በሁሉም ቦታ። ዮሐንስ የቅርብ ወዳጁን እና አዳኙን የኢየሱስን ተአምራት፣ ትምህርቶች እና የዕለት ተዕለት ግኝቶችን ተርኳል። አንተም ኢየሱስን እንድትከተል እና የዘላለም ህይወት ስጦታውን እንድትቀበል ተጋብዘሃል። ይህ እቅድ የተዘጋጀው በYouVersion ነው።
Haggai: ቀጣዩ ምን ይሆን?
ነገህን እየፈራህ ከሆነ ይህ የአምስት ቀናት እቅድ ለአንተ ነው፡፡ ምናልባት ልትቋቋመው የማትችለው አስቸጋሪ ሁኔታ ገጥሞህ ይሆናል፤ ነገር ግን በአንድ ነገር እርግጠኛ ሆነህ ኑር ይኸውም በአንተ ሕይወት የመጨረሻው ቃል ያለው እግዚአብሔር ነው፡፡ አግዚአብሐርን ማስቀደም፣ ህወትህን ከዓላማው ጋር ማጣጣም፤ በሚያጠነክርህና ቀጣዩ ምን እንደሆነ በሚያስቀጥልህ እውነት ላይ ማረፍን ተማር፡፡
ሐዲስ ኪዳንን ሙሉ በሙሉ ያንብቡ
ይህ እቅድ በአንድ አመት ግዜ ውስጥ ሐዲስ ኪዳንን ሙሉ ለሙሉ አንብበው እንዲጨርሱ ተደርጎ የተዘጋጀ ነው.