ሩት 4:1
ሩት 4:1 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
ቦዔዝ በከተማው በር አጠገብ ወደሚገኘው መሰብሰቢያ አደባባይ ሄዶ ተቀመጠ፤ ከዚህ በፊት ቦዔዝ ስለ እርሱ የተናገረው የአቤሜሌክ የቅርብ ዘመድ ወደዚያው ቦታ መጣ፤ ቦዔዝም በስሙ ጠርቶ “ወንድሜ ሆይ! ወደዚህ መጥተህ አጠገቤ ተቀመጥ” አለው። እርሱም ወደዚያ ሄዶ ተቀመጠ።
Share
ሩት 4 ያንብቡሩት 4:1 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ቦዓዝም ወደ ከተማይቱ በር አደባባይ ወጥቶ በዚያ ተቀመጠ። እነሆም፥ ቦዔዝ ስለ እርሱ ይናገር የነበረው የቅርብ ዘመድ ሲያልፍ ቦዔዝ፦ አንተ ቀርበህ በዚህ ተቀመጥ አለው። እርሱም ቀረብ ብሎ ተቀመጠ።
Share
ሩት 4 ያንብቡሩት 4:1 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ቦዔዝም ወደ ከተማዪቱ በር አደባባይ ወጥቶ ተቀመጠ፤ እርሱም የመቤዠት ቅድሚያ ያለው የቅርብ ዘመድ በመጣ ጊዜ፣ “ወዳጄ ሆይ፤ ወደዚህ ና፣ አጠገቤም ተቀመጥ” አለው፤ ስለዚህም ሰውየው ሄዶ ተቀመጠ።
Share
ሩት 4 ያንብቡ