የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ሮሜ 6:4-11

ሮሜ 6:4-11 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

በሞ​ቱም እን​መ​ስ​ለው ዘንድ ከእ​ርሱ ጋር በጥ​ም​ቀት ተቀ​በ​ርን፤ እርሱ ክር​ስ​ቶስ በአ​ባቱ ጌት​ነት ከሙ​ታን እንደ ተነሣ እኛም እንደ እርሱ በሐ​ዲስ ሕይ​ወት እን​ኖ​ራ​ለን። በሞቱ ከመ​ሰ​ል​ነ​ውም በት​ን​ሣ​ኤው እን​መ​ስ​ለ​ዋ​ለን። ነገር ግን የኀ​ጢ​አ​ትን ሥጋ ይሽር ዘንድ ከእ​ርሱ ጋር የተ​ሰ​ቀ​ለው አሮ​ጌው ሰው​ነ​ታ​ችን እንደ ሆነ ይህን እና​ው​ቃ​ለን፤ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲያ ዳግ​መና ለኀ​ጢ​አት እን​ገዛ ዘንድ አን​መ​ለ​ስም። የሞ​ተስ ከኀ​ጢ​አት ነጻ ወጥ​ቶ​አል። ከክ​ር​ስ​ቶስ ጋር ከሞ​ት​ንም ከእ​ርሱ ጋር በሕ​ይ​ወት እን​ደ​ም​ን​ኖር እና​ም​ና​ለን። ክር​ስ​ቶስ ከሙ​ታን ተለ​ይቶ እንደ ተነሣ፥ ዳግ​መ​ኛም እን​ደ​ማ​ይ​ሞት፥ እን​ግ​ዲህ ወዲ​ህም ሞት እን​ደ​ማ​ይ​ገ​ዛው እና​ው​ቃ​ለን። የሞተ አንድ ጊዜ ሞተ፤ በሞ​ቱም ኀጢ​አ​ትን ሻራት፤ የተ​ነ​ሣም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተነሣ። እን​ዲሁ እና​ን​ተም ራሳ​ች​ሁን ለኀ​ጢ​አት ምው​ታን አድ​ርጉ፤ በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕያ​ዋን ሁኑ።

ሮሜ 6:4-11 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

እንግዲህ ክርስቶስ በአብ ክብር ከሙታን እንደ ተነሣ እንዲሁ እኛም በአዲስ ሕይወት እንድንመላለስ፥ ከሞቱ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ በጥምቀት ከእርሱ ጋር ተቀበርን። ሞቱንም በሚመስል ሞት ከእርሱ ጋር ከተባበርን ትንሣኤውን በሚመስል ትንሣኤ ደግሞ ከእርሱ ጋር እንተባበራለን፤ ከእንግዲህስ ወዲያ ለኃጢአት እንዳንገዛ የኃጢአት ሥጋ ይሻር ዘንድ አሮጌው ሰዋችን ከእርሱ ጋር እንደ ተሰቀለ እናውቃለን፤ የሞተስ ከኃጢአቱ ጸድቋልና። ነገር ግን ከክርስቶስ ጋር ከሞትን ከእርሱ ጋር ደግሞ በሕይወት እንድንኖር እናምናለን፤ ክርስቶስ ከሙታን ተነሥቶ ወደ ፊት እንዳይሞት ሞትም ወደ ፊት እንዳይገዛው እናውቃለንና። መሞትን አንድ ጊዜ ፈጽሞ ለኃጢአት ሞቶአልና፤ በሕይወት መኖርን ግን ለእግዚአብሔር ይኖራል። እንዲሁም እናንተ ደግሞ ለኃጢአት እንደ ሞታችሁ፥ ግን በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን ሆናችሁ ለእግዚአብሔር ሕያዋን እንደ ሆናችሁ ራሳችሁን ቍኦጠሩ።

ሮሜ 6:4-11 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

በጥምቀት ከእርሱ ጋር በተቀበርን ጊዜ የእርሱም ሞት ተካፋዮች ሆነናል፤ ስለዚህ ክርስቶስ በአብ ክብር ከሞት እንደ ተነሣ እኛም በአዲስ ሕይወት እንኖራለን። በሞቱ ከእርሱ ጋር እንዲህ አንድ ከሆንን እንዲሁ በትንሣኤው ከእርሱ ጋር አንድ እንሆናለን። ኃጢአተኛው ሰውነታችን እንዲወገድና የኃጢአት ባሪያዎች መሆናችን እንዲቀር አሮጌው ሰውነታችን ከክርስቶስ ጋር መሰቀሉን እናውቃለን። የሞተ ሰው ለኃጢአት ከመገዛት ነጻ ነው። እንግዲህ ከክርስቶስ ጋር ከሞትን ከእርሱ ጋር በሕይወት እንደምንኖር እናምናለን፤ ክርስቶስ ከሞት በመነሣቱ ምክንያት ዳግመኛ እንደማይሞትና ሞትም በእርሱ ላይ ሥልጣን እንደሌለው እናውቃለን። እርሱ በሞተ ጊዜ ኃጢአት በእርሱ ላይ ሥልጣን እንዳይኖረው በማያዳግም ሁኔታ አንድ ጊዜ ሞቶአል፤ አሁንም በሕይወት ሲኖር ለእግዚአብሔር ይኖራል። እንግዲህ እናንተ የመሞት ያኽል ከኃጢአት እንደ ተለያችሁና በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት ግን ለእግዚአብሔር በሕይወት እንደምትኖሩ አስቡ።

ሮሜ 6:4-11 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

ስለዚህ በአብ ክብር ክርስቶስ ከሙታን እንደ ተነሣ እንዲሁ እኛም በአዲስ ሕይወት እንድንኖር፥ በጥምቀት አማካኝነት በሞት ከእርሱ ጋር ተቀብረናል። የእርሱን በሚመስል ሞት ከእርሱ ጋር አንድ ከሆንን እንዲሁም ደግሞ በትንሣኤው ከእርሱ ጋር አንድ እንሆናለን፤ ከእንግዲህስ ወዲያ ለኃጢአት ባርያዎች እንዳንሆን የኃጢአት ሰውነት እንዲሻር አሮጌው ማንነታችን ከእርሱ ጋር እንደ ተሰቀለ እናውቃለን። የሞተስ ከኃጢአት ነጻ ወጥቶአልና። ነገር ግን ከክርስቶስ ጋር ከሞትን ከእርሱ ጋር ደግሞ እንደምንኖር እናምናለን። ክርስቶስ ከሙታን ተነሥቷል፥ ዳግመኛም እንደማይሞት እናውቃለንና፤ ሞት ከእንግዲህ እርሱን አይገዛውም። በእርሱ ሞቷልና፥ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለኃጢአት ሞቷል፤ መኖርን ግን ለእግዚአብሔር ይኖራል። እንዲሁም ደግሞ እናንተ በአንድ በኩል በእርግጥ ለኃጢአት እንደ ሞታችሁ፥ በሌላ በኩል ግን በክርስቶስ ኢየሱስ ለእግዚአብሔር ሕያዋን እንደ ሆናችሁ ራሳችሁን ቁጠሩ።