የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ሮሜ 6:16-22

ሮሜ 6:16-22 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

ለም​ት​ታ​ዘ​ዙ​ለት፥ እሺ ለም​ት​ሉ​ትም እና​ንተ አገ​ል​ጋ​ዮች እንደ ሆና​ችሁ አታ​ው​ቁ​ምን? ለተ​ባ​በ​ራ​ች​ሁ​ለ​ትስ ራሳ​ች​ሁን እንደ አስ​ገ​ዛ​ችሁ አታ​ው​ቁ​ምን? ኀጢ​አ​ት​ንም እሺ ብት​ሉ​አት፥ ተባ​ብ​ራ​ች​ሁም ብት​በ​ድሉ እና​ንት ለሞት ተገ​ዢ​ዎች ትሆ​ና​ላ​ችሁ፤ ጽድ​ቅ​ንም እሺ ብት​ሉ​አት ለበጎ ሥራም ብት​ተ​ባ​በሩ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አገ​ል​ጋ​ዮች ናችሁ። የኀ​ጢ​አት ተገ​ዦች ስት​ሆኑ ምሳ​ሌ​ነቱ ለተ​ሰ​ጣ​ችሁ ለም​ት​ማ​ሩት ትም​ህ​ርት ታዝ​ዛ​ች​ኋ​ልና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመ​ስ​ገን። አሁን ግን ከኀ​ጢ​አት ነጻ ሁና​ችሁ ለጽ​ድቅ ተገ​ዝ​ታ​ች​ኋል። ስለ ሰው​ነ​ታ​ችሁ ድካም በሰው ልማድ እነ​ግ​ራ​ች​ኋ​ለሁ፤ ዕወቁ፤ ቀድሞ ሰው​ነ​ታ​ች​ሁን ለኀ​ጢ​አ​ትና ለር​ኵ​ሰት፥ ለዐ​መ​ፃም እንደ አስ​ገ​ዛ​ችሁ፥ እን​ዲሁ አሁ​ንም ሰው​ነ​ታ​ች​ሁን ለጽ​ድ​ቅና ለቅ​ድ​ስና አስ​ገዙ። ለኀ​ጢ​አት ትገዙ በነ​በ​ረ​በት ጊዜ ከጽ​ድቅ ነፃ ነበ​ራ​ች​ሁና። በዚ​ያን ጊዜ ሥራ​ች​ሁም እነሆ፥ ዛሬ ታፍ​ሩ​በ​ታ​ላ​ችሁ፤ መጨ​ረ​ሻው ሞት ነውና። ዛሬ ግን ከኀ​ጢ​አት ነጻ ወጣ​ችሁ፤ ራሳ​ች​ሁ​ንም ለጽ​ድቅ አስ​ገ​ዛ​ችሁ፤ ለቅ​ድ​ስ​ናም ፍሬን አፈ​ራ​ችሁ፤ ፍጻ​ሜው ግን የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወት ነው።

ሮሜ 6:16-22 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

ለመታዘዝ ባሪያዎች እንድትሆኑ ራሳችሁን ለምታቀርቡለት፥ ለእርሱ ለምትታዘዙለት ባሪያዎች እንደ ሆናችሁ አታውቁምን? ወይም ለሞት የኃጢአት ባሪያዎች ወይም ለጽድቅ የመታዘዝ ባሪያዎች ናችሁ። ነገር ግን አስቀድማችሁ የኃጢአት ባሪያዎች ከሆናችሁ፥ ለተሰጣችሁለት ለትምህርት ዓይነት ከልባችሁ ስለ ታዘዛችሁ፥ ከኃጢአትም አርነት ወጥታችሁ ለጽድቅ ስለ ተገዛችሁ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን። ስለ ሥጋችሁ ድካም እንደ ሰው ልማድ እላለሁ። ብልቶቻችሁ ዓመፃ ሊያደርጉ ለርኵስነትና ለዓመፃ ባሪያዎች አድርጋችሁ እንዳቀረባችሁ፥ እንደዚሁ ብልቶቻችሁ ሊቀደሱ ለጽድቅ ባሪያዎች አድርጋችሁ አሁን አቅርቡ። የኃጢአት ባሪያዎች ሳላችሁ ከጽድቅ ነፃ ነበራችሁና። እንግዲህ ዛሬ ከምታፍሩበት ነገር ያን ጊዜ ምን ፍሬ ነበራችሁ? የዚህ ነገር መጨረሻው ሞት ነውና። አሁን ግን ከኃጢአት አርነት ወጥታችሁ ለእግዚአብሔርም ተገዝታችሁ፥ ልትቀደሱ ፍሬ አላችሁ፤ መጨረሻውም የዘላለም ሕይወት ነው።

ሮሜ 6:16-22 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

ለአንድ ሰው አገልጋዮች ሆናችሁ ለመታዘዝ ራሳችሁን ስታቀርቡ ለዚያ ለምትታዘዙለት ሰው አገልጋዮች መሆናችሁን ታውቃላችሁ፤ እንዲሁም ለኃጢአት ብትታዘዙ ሞትን ለሚያመጣባችሁ ኃጢአት አገልጋዮች ትሆናላችሁ፤ ለእግዚአብሔር ብትታዘዙ ግን ጽድቅን ታገኛላችሁ። እናንተ አስቀድሞ የኃጢአት ባሪያዎች ነበራችሁ፤ አሁን ግን ለተቀበላችሁት ትምህርት ከልብ በመታዘዛችሁ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን። ከኃጢአት ባርነት ነጻ ወጥታችሁ የጽድቅ አገልጋዮች ሆናችኋል። እኔ እንዲህ ለሰው በሚገባ ቋንቋ የምናገረው ከአስተሳሰባችሁ ደካማነት የተነሣ ነው። አስቀድሞ የሰውነት ክፍሎቻችሁን የርኲሰትና የዐመፅ አገልጋዮች አድርጋችሁ እንዳቀረባችሁ ሁሉ እንዲሁም አሁን የሰውነት ክፍሎቻችሁ እንዲቀደሱ የጽድቅ አገልጋዮች አድርጋችሁ አቅርቡ። የኃጢአት ባሪያዎች በነበራችሁበት ጊዜ ጽድቅ የማድረግ ግዴታ አይሰማችሁም ነበር። ታዲያ፥ በዚያን ጊዜ ምን ጥቅም አገኛችሁ? አሁን ከሚያሳፍራችሁ ነገር በቀር ምንም ጥቅም አላገኛችሁም፤ የዚህም ነገር መጨረሻ ሞት ነው። አሁን ግን ከኃጢአት ባርነት ነጻ ወጥታችሁ የእግዚአብሔር አገልጋዮች በመሆናችሁ ቅድስናን ታገኛላችሁ፤ የቅድስናም መጨረሻ የዘለዓለም ሕይወት ነው።

ሮሜ 6:16-22 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

እራሳችሁን የመታዘዝ ባርያዎች አድርጋችሁ ለምታቀርቡለት፥ ለምትታዘዙት ለእርሱ ሞትን ለሚያመጣው ለኃጢአት ወይም ጽድቅን ለሚያመጣው ለመታዘዝ ባርያዎች እንደ ሆናችሁ አታውቁምን? አስቀድማችሁ የኃጢአት ባርያዎች የነበራችሁ፥ ነገር ግን ለተሰጣችሁለት የትምህርት ዓይነት ከልባችሁ በመታዘዛችሁ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን። ከኃጢአትም ነፃ ወጥታችሁ ለጽድቅ ባርያዎች ሆናችኋል። ከሥጋችሁ ደካማነት የተነሣ እንደ ሰው አነጋገር እናገራለሁ። የሰውነታችሁን ክፍሎች ሕገ ወጥነትን ለሚያመጣ ለርኩሰትና ለሕገ ወጥነት ባርያዎች አድርጋችሁ እንዳቀረባችሁ፥ ስለዚህ አሁን የሰውነታችሁን ክፍሎች ቅድስና ለሚያመጣ ለጽድቅ ባርያዎች አድርጋችሁ አቅርቡ። የኃጢአት ባርያዎች በነበራችሁበት ጊዜ ከጽድቅ ነፃ ነበራችሁ። ታዲያ አሁን ከምታፍሩበት ነገር ሌላ ያንጊዜ ምን ፍሬ ነበራችሁ? የእነዚህ ነገሮች መጨረሻ ሞት ነውና። አሁን ግን ከኃጢአት ነፃ ወጥታችሁ ለእግዚአብሔርም ባርያዎች ሆናችኋል፥ ፍሬያችሁም ቅድስና ነው፤ መጨረሻውም የዘለዓለም ሕይወት ነው።